የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • 2 ዜና መዋዕል 10
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

2 ዜና መዋዕል የመጽሐፉ ይዘት

      • እስራኤላውያን በሮብዓም ላይ ዓመፁ (1-19)

2 ዜና መዋዕል 10:1

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢያሱ 20:7፤ 24:1፤ መሳ 9:1
  • +1ነገ 12:1-4

2 ዜና መዋዕል 10:2

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 11:28
  • +1ነገ 11:40

2 ዜና መዋዕል 10:4

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ጨቋኝ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ሳሙ 8:11-18፤ 1ነገ 4:7

2 ዜና መዋዕል 10:5

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 12:5-7

2 ዜና መዋዕል 10:8

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 12:8-11

2 ዜና መዋዕል 10:12

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 12:12-15

2 ዜና መዋዕል 10:15

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 11:29-31
  • +ዘዳ 2:30፤ 2ሳሙ 17:14

2 ዜና መዋዕል 10:16

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ወደየድንኳናቸው።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 11:32
  • +1ነገ 12:16, 17

2 ዜና መዋዕል 10:17

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 11:35, 36

2 ዜና መዋዕል 10:18

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ሳሙ 20:24፤ 1ነገ 4:6
  • +1ነገ 12:18, 19

ተዛማጅ ሐሳብ

2 ዜና 10:1ኢያሱ 20:7፤ 24:1፤ መሳ 9:1
2 ዜና 10:11ነገ 12:1-4
2 ዜና 10:21ነገ 11:28
2 ዜና 10:21ነገ 11:40
2 ዜና 10:41ሳሙ 8:11-18፤ 1ነገ 4:7
2 ዜና 10:51ነገ 12:5-7
2 ዜና 10:81ነገ 12:8-11
2 ዜና 10:121ነገ 12:12-15
2 ዜና 10:151ነገ 11:29-31
2 ዜና 10:15ዘዳ 2:30፤ 2ሳሙ 17:14
2 ዜና 10:161ነገ 11:32
2 ዜና 10:161ነገ 12:16, 17
2 ዜና 10:171ነገ 11:35, 36
2 ዜና 10:182ሳሙ 20:24፤ 1ነገ 4:6
2 ዜና 10:181ነገ 12:18, 19
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
2 ዜና መዋዕል 10:1-19

ሁለተኛ ዜና መዋዕል

10 እስራኤላውያን በሙሉ ሮብዓምን ለማንገሥ ወደ ሴኬም+ መጥተው ስለነበር እሱም ወደ ሴኬም ሄደ።+ 2 የናባጥ ልጅ ኢዮርብዓም+ ይህን እንደሰማ (ምክንያቱም በወቅቱ ኢዮርብዓም ከንጉሥ ሰለሞን ሸሽቶ በግብፅ ይኖር ነበር)፣+ ከግብፅ ተመልሶ መጣ። 3 ከዚያም ሰዎች ልከው አስጠሩት፤ ኢዮርብዓምና መላው እስራኤልም መጥተው ሮብዓምን እንዲህ አሉት፦ 4 “አባትህ ቀንበራችንን አክብዶብን ነበር።+ አንተ ግን አባትህ የሰጠንን አስቸጋሪ ሥራና በላያችን የጫነብንን ከባድ* ቀንበር የምታቀልልን ከሆነ እናገለግልሃለን።”

5 በዚህ ጊዜ “ከሦስት ቀን በኋላ ተመልሳችሁ ኑ” አላቸው። በመሆኑም ሕዝቡ ሄደ።+ 6 ከዚያም ንጉሥ ሮብዓም አባቱ ሰለሞን በሕይወት በነበረበት ጊዜ ሲያገለግሉት የነበሩትን ሽማግሌዎች “ለዚህ ሕዝብ ምን ምላሽ እንድሰጥ ትመክሩኛላችሁ?” በማለት ምክር ጠየቀ። 7 እነሱም “ለዚህ ሕዝብ ጥሩ ብትሆንና ደስ ብታሰኛቸው እንዲሁም መልካም ምላሽ ብትሰጣቸው ምንጊዜም አገልጋዮችህ ይሆናሉ” በማለት መለሱለት።

8 ሆኖም ሮብዓም ሽማግሌዎቹ የሰጡትን ምክር ትቶ አብሮ አደጎቹ ከነበሩትና አሁን የእሱ አገልጋዮች ከሆኑት ወጣቶች ጋር ተማከረ።+ 9 እሱም እንዲህ ሲል ጠየቃቸው፦ “‘አባትህ የጫነብንን ቀንበር አቅልልልን’ ለሚለኝ ለዚህ ሕዝብ ምን ምላሽ እንድንሰጥ ትመክሩኛላችሁ?” 10 አብሮ አደጎቹ የሆኑት ወጣቶችም እንዲህ አሉት፦ “‘አባትህ ቀንበራችንን አክብዶብን ነበር፤ አንተ ግን ቀንበራችንን አቅልልልን’ ለሚልህ ሕዝብ እንዲህ በለው፦ ‘ትንሿ ጣቴ ከአባቴ ወገብ ትወፍራለች። 11 አባቴ ከባድ ቀንበር ጭኖባችሁ ነበር፤ እኔ ግን ቀንበራችሁን የባሰ አከብደዋለሁ። አባቴ በአለንጋ ገርፏችሁ ነበር፤ እኔ ግን በእሾህ አለንጋ እገርፋችኋለሁ።’”

12 ኢዮርብዓምና መላው ሕዝብ ንጉሡ “በሦስተኛው ቀን ተመልሳችሁ ኑ” ባላቸው መሠረት በሦስተኛው ቀን ወደ ሮብዓም መጡ።+ 13 ይሁንና ንጉሡ መጥፎ ምላሽ ሰጣቸው። በዚህ መንገድ ንጉሥ ሮብዓም ሽማግሌዎቹ የሰጡትን ምክር ሳይቀበል ቀረ። 14 ወጣቶቹ በሰጡት ምክር መሠረት “ቀንበራችሁን አከብደዋለሁ፤ ከቀድሞውም የከፋ አደርገዋለሁ። አባቴ በአለንጋ ገርፏችሁ ነበር፤ እኔ ግን በእሾህ አለንጋ እገርፋችኋለሁ” አላቸው። 15 በመሆኑም ንጉሡ ሕዝቡን ሳይሰማ ቀረ፤ ይህም የሆነው ይሖዋ በሴሎናዊው በአኪያህ+ አማካኝነት ለናባጥ ልጅ ለኢዮርብዓም የተናገረው ቃል ይፈጸም ዘንድ እውነተኛው አምላክ እነዚህ ነገሮች በዚህ መንገድ እንዲከናወኑ ስላደረገ ነው።+

16 እስራኤላውያን ሁሉ ንጉሡ ሊሰማቸው ፈቃደኛ አለመሆኑን ሲያዩ ንጉሡን እንዲህ አሉት፦ “ከዳዊት ምን ድርሻ አለን? ከእሴይ ልጅ ምንም ርስት የለንም። እስራኤል ሆይ፣ እያንዳንድህ ወደ አማልክትህ ተመለስ! ዳዊት ሆይ፣ እንግዲህ የገዛ ቤትህን ጠብቅ!”+ ከዚያም እስራኤላውያን ሁሉ ወደየቤታቸው* ተመለሱ።+

17 ይሁንና ሮብዓም በይሁዳ ከተሞች በሚኖሩት እስራኤላውያን ላይ መግዛቱን ቀጠለ።+

18 ከዚያም ንጉሥ ሮብዓም የግዳጅ ሥራ እንዲሠሩ የተመለመሉት ሰዎች አለቃ የነበረውን ሃዶራምን+ ላከው፤ ሆኖም እስራኤላውያን በድንጋይ ወግረው ገደሉት። ንጉሥ ሮብዓም ግን እንደ ምንም ብሎ ሠረገላው ላይ በመውጣት ወደ ኢየሩሳሌም ሸሸ።+ 19 እስራኤላውያንም እስከዚህ ቀን ድረስ በዳዊት ቤት ላይ እንዳመፁ ናቸው።

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ