የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • 2 ዜና መዋዕል 11
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

2 ዜና መዋዕል የመጽሐፉ ይዘት

      • የሮብዓም አገዛዝ (1-12)

      • ታማኝ የሆኑ ሌዋውያን ወደ ይሁዳ መጡ (13-17)

      • የሮብዓም ቤተሰብ (18-23)

2 ዜና መዋዕል 11:1

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “የተመረጡ ተዋጊዎች።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 49:27፤ 2ዜና 14:8
  • +1ነገ 12:21-24

2 ዜና መዋዕል 11:2

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 12:15

2 ዜና መዋዕል 11:4

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 11:31፤ 2ዜና 10:15

2 ዜና መዋዕል 11:6

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 35:19፤ ማቴ 2:1
  • +አሞጽ 1:1

2 ዜና መዋዕል 11:7

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 28:18
  • +1ሳሙ 22:1

2 ዜና መዋዕል 11:8

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ዜና 18:1
  • +1ሳሙ 23:14

2 ዜና መዋዕል 11:9

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 32:9
  • +ኢያሱ 10:10፤ ኤር 34:7

2 ዜና መዋዕል 11:10

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “አጠናከረ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢያሱ 19:42, 48
  • +ኢያሱ 14:14, 15፤ 2ሳሙ 2:1

2 ዜና መዋዕል 11:14

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 12:31, 32
  • +ዘኁ 35:2, 3

2 ዜና መዋዕል 11:15

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ለፍየሎችና።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 17:7
  • +1ነገ 12:26, 28
  • +1ነገ 13:33

2 ዜና መዋዕል 11:16

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 12:11፤ 1ዜና 22:1፤ 2ዜና 15:8, 9፤ 30:10, 11

2 ዜና መዋዕል 11:18

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ሳሙ 16:6፤ 17:13

2 ዜና መዋዕል 11:20

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ሳሙ 13:1፤ 18:33
  • +1ነገ 15:1፤ 2ዜና 12:16፤ ማቴ 1:7

2 ዜና መዋዕል 11:21

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 17:17

2 ዜና መዋዕል 11:23

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ወደተመሸጉት ከተሞች ሁሉ በተናቸው።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 11:5, 11

ተዛማጅ ሐሳብ

2 ዜና 11:1ዘፍ 49:27፤ 2ዜና 14:8
2 ዜና 11:11ነገ 12:21-24
2 ዜና 11:22ዜና 12:15
2 ዜና 11:41ነገ 11:31፤ 2ዜና 10:15
2 ዜና 11:6ዘፍ 35:19፤ ማቴ 2:1
2 ዜና 11:6አሞጽ 1:1
2 ዜና 11:72ዜና 28:18
2 ዜና 11:71ሳሙ 22:1
2 ዜና 11:81ዜና 18:1
2 ዜና 11:81ሳሙ 23:14
2 ዜና 11:92ዜና 32:9
2 ዜና 11:9ኢያሱ 10:10፤ ኤር 34:7
2 ዜና 11:10ኢያሱ 19:42, 48
2 ዜና 11:10ኢያሱ 14:14, 15፤ 2ሳሙ 2:1
2 ዜና 11:141ነገ 12:31, 32
2 ዜና 11:14ዘኁ 35:2, 3
2 ዜና 11:15ዘሌ 17:7
2 ዜና 11:151ነገ 12:26, 28
2 ዜና 11:151ነገ 13:33
2 ዜና 11:16ዘዳ 12:11፤ 1ዜና 22:1፤ 2ዜና 15:8, 9፤ 30:10, 11
2 ዜና 11:181ሳሙ 16:6፤ 17:13
2 ዜና 11:202ሳሙ 13:1፤ 18:33
2 ዜና 11:201ነገ 15:1፤ 2ዜና 12:16፤ ማቴ 1:7
2 ዜና 11:21ዘዳ 17:17
2 ዜና 11:232ዜና 11:5, 11
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
  • 23
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
2 ዜና መዋዕል 11:1-23

ሁለተኛ ዜና መዋዕል

11 ሮብዓም ኢየሩሳሌም በደረሰ ጊዜ ከእስራኤል ጋር ተዋግተው መንግሥቱን ለሮብዓም እንዲያስመልሱ ከይሁዳ ቤትና ከቢንያም ነገድ+ የተውጣጡ 180,000 የሠለጠኑ ተዋጊዎች* ወዲያውኑ ሰበሰበ።+ 2 ከዚያም የይሖዋ ቃል የእውነተኛው አምላክ ሰው ወደሆነው ወደ ሸማያህ+ እንዲህ ሲል መጣ፦ 3 “ለይሁዳ ንጉሥ ለሰለሞን ልጅ ለሮብዓም እንዲሁም በይሁዳና በቢንያም ላሉት እስራኤላውያን ሁሉ እንዲህ ብለህ ተናገር፦ 4 ‘ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ከወንድሞቻችሁ ጋር ለመዋጋት አትውጡ። ይህ እንዲሆን ያደረግኩት እኔ ስለሆንኩ እያንዳንዳችሁ ወደ ቤታችሁ ተመለሱ።”’”+ ስለዚህ የይሖዋን ቃል ሰምተው ተመለሱ፤ በኢዮርብዓምም ላይ አልዘመቱም።

5 ሮብዓም መኖሪያውን በኢየሩሳሌም አድርጎ በይሁዳ የተመሸጉ ከተሞችን ገነባ። 6 ቤተልሔምን፣+ ኤጣምን፣ ተቆአን፣+ 7 ቤትጹርን፣ ሶኮን፣+ አዱላምን፣+ 8 ጌትን፣+ ማሬሻህን፣ ዚፍን፣+ 9 አዶራይምን፣ ለኪሶን፣+ አዜቃን፣+ 10 ጾራን፣ አይሎንንና+ ኬብሮንን+ ገነባ፤* እነዚህ በይሁዳና በቢንያም የነበሩ የተመሸጉ ከተሞች ናቸው። 11 በተጨማሪም የተመሸጉትን ከተሞች አጠናከረ፤ በከተሞቹም ላይ አዛዦችን ሾመ፤ በእነዚህ ከተሞች ምግብ፣ ዘይትና የወይን ጠጅ አከማቸ፤ 12 በከተሞቹም ሁሉ ትላልቅ ጋሻዎችና ጦር አስቀመጠ፤ ከተሞቹንም እጅግ አጠናከራቸው። ይሁዳንና ቢንያምንም መግዛቱን ቀጠለ።

13 በመላው እስራኤል ያሉት ካህናትና ሌዋውያንም የነበሩበትን ክልል በሙሉ ለቀው በመሄድ ከእሱ ጎን ቆሙ። 14 ሌዋውያኑ የይሖዋ ካህናት ሆነው እንዳያገለግሉ ኢዮርብዓምና ልጆቹ አባረዋቸው ስለነበር+ የግጦሽ መሬታቸውንና ርስታቸውን+ ትተው ወደ ይሁዳና ወደ ኢየሩሳሌም መጥተው ነበር። 15 በዚህ ጊዜ ኢዮርብዓም ከፍ ላሉት የማምለኪያ ቦታዎች፣ ፍየል ለሚመስሉት አጋንንትና*+ ለሠራቸው የጥጃ ምስሎች+ የራሱን ካህናት ሾመ።+ 16 የእስራኤልን አምላክ ይሖዋን ለመፈለግ ከልባቸው ቆርጠው የተነሱ ከሁሉም የእስራኤል ነገዶች የተውጣጡ ሰዎች ለአባቶቻቸው አምላክ ለይሖዋ መሥዋዕት ለማቅረብ ካህናቱንና ሌዋውያኑን ተከትለው ወደ ኢየሩሳሌም መጡ።+ 17 ለሦስት ዓመት በዳዊትና በሰለሞን መንገድ ይመላለሱ ስለነበር በእነዚህ ሦስት ዓመታት የይሁዳን መንግሥት አጠናከሩ፤ ደግሞም ለሰለሞን ልጅ ለሮብዓም ድጋፍ ሰጡ።

18 ከዚያም ሮብዓም የዳዊት ልጅ የሆነውን የየሪሞትን ሴት ልጅ ማሃላትን አገባ። ማሃላት የእሴይ ልጅ፣ የኤልያብ+ ሴት ልጅ የሆነችው የአቢሃይል ልጅ ነበረች። 19 ከጊዜ በኋላም የኡሽ፣ ሸማርያህ እና ዛሃም የተባሉ ወንዶች ልጆች ወለደችለት። 20 ከእሷ በኋላ የአቢሴሎም+ የልጅ ልጅ የሆነችውን ማአካን አገባ። እሷም አቢያህን፣+ አታይን፣ ዚዛን እና ሸሎሚትን ወለደችለት። 21 ሮብዓም የአቢሴሎም የልጅ ልጅ የሆነችውን ማአካን ከሌሎቹ ሚስቶቹና ቁባቶቹ ሁሉ+ አስበልጦ ይወዳት ነበር፤ እሱም 18 ሚስቶችና 60 ቁባቶች ነበሩት፤ ደግሞም 28 ወንዶች ልጆችና 60 ሴቶች ልጆች ወለደ። 22 ሮብዓምም የማአካን ልጅ አቢያህን ሊያነግሠው ስለፈለገ በወንድሞቹ ላይ ራስና መሪ አድርጎ ሾመው። 23 ይሁን እንጂ ማስተዋል የታከለበት እርምጃ በመውሰድ ከወንዶች ልጆቹ መካከል አንዳንዶቹን በይሁዳና በቢንያም ምድር ሁሉ ወደሚገኙት ወደተመሸጉት ከተሞች+ ሁሉ ላካቸው፤* የሚያስፈልጓቸውንም ነገሮች በብዛት ሰጣቸው፤ ብዙ ሚስቶችም አጋባቸው።

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ