የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • 2 ዜና መዋዕል 3
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

2 ዜና መዋዕል የመጽሐፉ ይዘት

      • ሰለሞን ቤተ መቅደሱን መገንባት ጀመረ (1-7)

      • ቅድስተ ቅዱሳኑ (8-14)

      • ሁለቱ የመዳብ ዓምዶች (15-17)

2 ዜና መዋዕል 3:1

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ሳሙ 24:25፤ 1ዜና 21:18
  • +ዘፍ 22:2, 14
  • +2ሳሙ 24:18፤ 1ዜና 21:22
  • +1ነገ 6:1, 37

2 ዜና መዋዕል 3:3

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    በመደበኛው መለኪያ መሠረት አንድ ክንድ 44.5 ሴንቲ ሜትር ነው፤ አንዳንዶች ግን “የቀድሞው መለኪያ” 51.8 ሴንቲ ሜትር የሚሆነውን ረጅሙን ክንድ እንደሚያመለክት ይሰማቸዋል። ከተጨማሪው መረጃ ላይ ለ14ን ተመልከት።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 6:2

2 ዜና መዋዕል 3:4

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    የመለኪያው ምንነት በእርግጠኝነት አይታወቅም።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 6:3

2 ዜና መዋዕል 3:5

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ታላቁን ቤት።” ቅድስቱን የሚያመለክት ሳይሆን አይቀርም።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 6:15, 22
  • +1ነገ 6:29
  • +1ነገ 6:21

2 ዜና መዋዕል 3:6

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ዜና 29:2, 8
  • +1ዜና 29:3, 4

2 ዜና መዋዕል 3:7

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 26:29
  • +ዘፀ 26:1፤ 1ነገ 6:29

2 ዜና መዋዕል 3:8

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ቤት።”

  • *

    አንድ ታላንት 34.2 ኪሎ ግራም ነው። ከተጨማሪው መረጃ ላይ ለ14ን ተመልከት።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 26:33፤ 1ነገ 8:6፤ ዕብ 9:24
  • +1ነገ 6:20

2 ዜና መዋዕል 3:9

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    አንድ ሰቅል 11.4 ግራም ነው። ከተጨማሪው መረጃ ላይ ለ14ን ተመልከት።

2 ዜና መዋዕል 3:10

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ቤት።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 6:23-28

2 ዜና መዋዕል 3:11

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 8:6፤ 1ዜና 28:18

2 ዜና መዋዕል 3:13

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወደ ቅድስቱ ማለት ነው።

2 ዜና መዋዕል 3:14

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማቴ 27:51፤ ዕብ 10:19, 20
  • +ዘፀ 26:31, 33

2 ዜና መዋዕል 3:15

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 25:13
  • +1ነገ 7:15-22፤ 2ነገ 25:17፤ 2ዜና 4:11-13፤ ኤር 52:22, 23

2 ዜና መዋዕል 3:17

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “በደቡብ።”

  • *

    ወይም “በሰሜን።”

  • *

    “እሱ [ማለትም ይሖዋ] አጽንቶ ይመሥርት” የሚል ትርጉም አለው።

  • *

    “በብርታት” ማለት ሳይሆን አይቀርም።

ተዛማጅ ሐሳብ

2 ዜና 3:12ሳሙ 24:25፤ 1ዜና 21:18
2 ዜና 3:1ዘፍ 22:2, 14
2 ዜና 3:12ሳሙ 24:18፤ 1ዜና 21:22
2 ዜና 3:11ነገ 6:1, 37
2 ዜና 3:31ነገ 6:2
2 ዜና 3:41ነገ 6:3
2 ዜና 3:51ነገ 6:15, 22
2 ዜና 3:51ነገ 6:29
2 ዜና 3:51ነገ 6:21
2 ዜና 3:61ዜና 29:2, 8
2 ዜና 3:61ዜና 29:3, 4
2 ዜና 3:7ዘፀ 26:29
2 ዜና 3:7ዘፀ 26:1፤ 1ነገ 6:29
2 ዜና 3:8ዘፀ 26:33፤ 1ነገ 8:6፤ ዕብ 9:24
2 ዜና 3:81ነገ 6:20
2 ዜና 3:101ነገ 6:23-28
2 ዜና 3:111ነገ 8:6፤ 1ዜና 28:18
2 ዜና 3:14ማቴ 27:51፤ ዕብ 10:19, 20
2 ዜና 3:14ዘፀ 26:31, 33
2 ዜና 3:152ነገ 25:13
2 ዜና 3:151ነገ 7:15-22፤ 2ነገ 25:17፤ 2ዜና 4:11-13፤ ኤር 52:22, 23
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
2 ዜና መዋዕል 3:1-17

ሁለተኛ ዜና መዋዕል

3 ከዚያም ሰለሞን በኢየሩሳሌም፣ ይሖዋ ለአባቱ ለዳዊት በተገለጠበት+ በሞሪያ ተራራ+ ይኸውም ዳዊት በኢያቡሳዊው በኦርናን+ አውድማ ላይ ባዘጋጀው ቦታ የይሖዋን ቤት መሥራት ጀመረ።+ 2 በነገሠ በአራተኛው ዓመት፣ በሁለተኛው ወር፣ በሁለተኛው ቀን የግንባታውን ሥራ ጀመረ። 3 ሰለሞን የእውነተኛውን አምላክ ቤት ለመሥራት የጣለው መሠረት በቀድሞው መለኪያ* ርዝመቱ 60 ክንድ፣ ወርዱም 20 ክንድ ነበር።+ 4 ከቤቱ ፊት ያለው በረንዳ ርዝመቱ 20 ክንድ ሲሆን ይህም ከቤቱ ወርድ ጋር እኩል ነው፤ ከፍታው ደግሞ 120* ነው፤ ውስጡንም በንጹሕ ወርቅ ለበጠው።+ 5 ዋናውን ክፍል* በጥድ እንጨት አልብሶ በጥሩ ወርቅ ለበጠው፤+ ከዚያም በዘንባባ ዛፍ ምስሎችና+ በሰንሰለቶች+ አስጌጠው። 6 በተጨማሪም ቤቱን ባማሩና በከበሩ ድንጋዮች ለበጠው፤+ የተጠቀመበትም ወርቅ+ ከፓርዋይም የመጣ ነበር። 7 እሱም ቤቱን፣ ወራጆቹን፣ ደፎቹን፣ ግድግዳዎቹንና በሮቹን በወርቅ ለበጣቸው፤+ በግድግዳዎቹም ላይ የኪሩቦችን ምስል ቀረጸ።+

8 ከዚያም የቅድስተ ቅዱሳኑን ክፍል* ሠራ፤+ ርዝመቱ ከቤቱ ወርድ ጋር እኩል የነበረ ሲሆን 20 ክንድ ነበር፤ ወርዱም 20 ክንድ ነበር። ከዚያም 600 ታላንት* በሚሆን ጥሩ ወርቅ ለበጠው።+ 9 ለምስማሮቹ የዋለው ወርቅ 50 ሰቅል* ይመዝን ነበር፤ ሰገነት ላይ ያሉትንም ክፍሎች በወርቅ ለበጣቸው።

10 ከዚያም በቅድስተ ቅዱሳኑ ክፍል* ውስጥ ሁለት የኪሩቦች ቅርጽ ሠርቶ በወርቅ ለበጣቸው።+ 11 የኪሩቦቹ ክንፎች+ አጠቃላይ ርዝመት 20 ክንድ ነበር፤ የመጀመሪያው ኪሩብ አንደኛው ክንፍ አምስት ክንድ ርዝመት ያለው ሲሆን የቤቱን ግድግዳ ይነካ ነበር፤ ሌላኛው ክንፉም አምስት ክንድ ርዝመት ያለው ሲሆን የሁለተኛውን ኪሩብ ክንፍ ይነካ ነበር። 12 የሁለተኛውም ኪሩብ አንደኛው ክንፍ አምስት ክንድ ርዝመት ያለው ሲሆን በአንጻሩ ያለውን የቤቱን ግድግዳ ይነካ ነበር፤ ሌላኛው ክንፉም አምስት ክንድ ርዝመት ያለው ሲሆን የመጀመሪያውን ኪሩብ ክንፍ ይነካ ነበር። 13 የተዘረጉት የእነዚህ ኪሩቦች ክንፎች 20 ክንድ ነበሩ፤ ኪሩቦቹም ፊታቸውን ወደ ውስጥ* አዙረው በእግራቸው ቆመው ነበር።

14 በተጨማሪም ከሰማያዊ ክር፣ ከሐምራዊ ሱፍ፣ ከደማቅ ቀይ ክርና ጥራት ካለው ጨርቅ መጋረጃ+ ሠርቶ የኪሩቦችን ምስል ጠለፈበት።+

15 ከቤቱ ፊት ለፊትም 35 ክንድ ርዝመት ያላቸው ሁለት ዓምዶችን+ ሠራ፤ በእያንዳንዱ ዓምድ ላይ ያለው የዓምድ ራስ አምስት ክንድ ነበር።+ 16 እንደ ሐብል ያሉ ሰንሰለቶች ሠርቶም በዓምዶቹ አናት ላይ አደረጋቸው፤ እንዲሁም 100 የሮማን ፍሬዎችን ሠርቶ ከሰንሰለቶቹ ጋር አያያዛቸው። 17 ዓምዶቹንም አንዱን በቀኝ* ሌላውን በግራ* አድርጎ በቤተ መቅደሱ ፊት ለፊት አቆማቸው፤ በስተ ቀኝ ያለውን ያኪን፣* በስተ ግራ ያለውን ደግሞ ቦዔዝ* ብሎ ሰየማቸው።

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ