የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • 2 ዜና መዋዕል 30
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

2 ዜና መዋዕል የመጽሐፉ ይዘት

      • ሕዝቅያስ የፋሲካን በዓል አከበረ (1-27)

2 ዜና መዋዕል 30:1

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “የማለፍን በዓል።” የቃላት መፍቻውን ተመልከት።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 12:43፤ ዘሌ 23:5፤ ዘዳ 16:2፤ 2ዜና 35:1
  • +2ዜና 11:14, 16
  • +2ዜና 34:1, 6, 7

2 ዜና መዋዕል 30:2

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘኁ 9:10, 11

2 ዜና መዋዕል 30:3

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 29:34
  • +ዘፀ 12:18

2 ዜና መዋዕል 30:5

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መሳ 18:29
  • +2ዜና 35:18

2 ዜና መዋዕል 30:6

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ሯጮቹ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 15:29፤ 1ዜና 5:26፤ 2ዜና 28:20, 21

2 ዜና መዋዕል 30:7

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 29:8, 9

2 ዜና መዋዕል 30:8

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 32:9
  • +2ዜና 29:10
  • +ዘዳ 12:5, 6፤ መዝ 132:13

2 ዜና መዋዕል 30:9

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ቸርና።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 8:49, 50
  • +ዘዳ 30:1-3
  • +ዘፀ 34:6፤ መዝ 86:5፤ ሚክ 7:18
  • +2ዜና 15:2፤ ኢሳ 55:7፤ ያዕ 4:8

2 ዜና መዋዕል 30:10

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ሯጮቹ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 30:1
  • +2ዜና 36:15, 16

2 ዜና መዋዕል 30:11

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 11:14, 16

2 ዜና መዋዕል 30:13

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘኁ 9:10, 11
  • +ዘሌ 23:6

2 ዜና መዋዕል 30:14

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 18:22፤ 2ዜና 28:24

2 ዜና መዋዕል 30:16

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 1:5

2 ዜና መዋዕል 30:17

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 29:34

2 ዜና መዋዕል 30:18

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 30:1
  • +መዝ 86:5

2 ዜና መዋዕል 30:19

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘኁ 9:6, 10
  • +2ዜና 19:2, 3፤ ዕዝራ 7:10

2 ዜና መዋዕል 30:20

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ፈወሰ።”

2 ዜና መዋዕል 30:21

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 23:6
  • +ዘዳ 12:5, 7፤ ነህ 8:10
  • +2ዜና 29:25

2 ዜና መዋዕል 30:22

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ለልባቸው ተናገረ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 3:1
  • +ዘሌ 23:6

2 ዜና መዋዕል 30:23

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 8:65

2 ዜና መዋዕል 30:24

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 35:7, 8
  • +2ዜና 29:34

2 ዜና መዋዕል 30:25

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 30:11, 18
  • +ዘፀ 12:49

2 ዜና መዋዕል 30:26

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 8:65, 66

2 ዜና መዋዕል 30:27

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘኁ 6:23-26፤ ዘዳ 10:8

ተዛማጅ ሐሳብ

2 ዜና 30:1ዘፀ 12:43፤ ዘሌ 23:5፤ ዘዳ 16:2፤ 2ዜና 35:1
2 ዜና 30:12ዜና 11:14, 16
2 ዜና 30:12ዜና 34:1, 6, 7
2 ዜና 30:2ዘኁ 9:10, 11
2 ዜና 30:32ዜና 29:34
2 ዜና 30:3ዘፀ 12:18
2 ዜና 30:5መሳ 18:29
2 ዜና 30:52ዜና 35:18
2 ዜና 30:62ነገ 15:29፤ 1ዜና 5:26፤ 2ዜና 28:20, 21
2 ዜና 30:72ዜና 29:8, 9
2 ዜና 30:8ዘፀ 32:9
2 ዜና 30:82ዜና 29:10
2 ዜና 30:8ዘዳ 12:5, 6፤ መዝ 132:13
2 ዜና 30:91ነገ 8:49, 50
2 ዜና 30:9ዘዳ 30:1-3
2 ዜና 30:9ዘፀ 34:6፤ መዝ 86:5፤ ሚክ 7:18
2 ዜና 30:92ዜና 15:2፤ ኢሳ 55:7፤ ያዕ 4:8
2 ዜና 30:102ዜና 30:1
2 ዜና 30:102ዜና 36:15, 16
2 ዜና 30:112ዜና 11:14, 16
2 ዜና 30:13ዘኁ 9:10, 11
2 ዜና 30:13ዘሌ 23:6
2 ዜና 30:142ነገ 18:22፤ 2ዜና 28:24
2 ዜና 30:16ዘሌ 1:5
2 ዜና 30:172ዜና 29:34
2 ዜና 30:182ዜና 30:1
2 ዜና 30:18መዝ 86:5
2 ዜና 30:19ዘኁ 9:6, 10
2 ዜና 30:192ዜና 19:2, 3፤ ዕዝራ 7:10
2 ዜና 30:21ዘሌ 23:6
2 ዜና 30:21ዘዳ 12:5, 7፤ ነህ 8:10
2 ዜና 30:212ዜና 29:25
2 ዜና 30:22ዘሌ 3:1
2 ዜና 30:22ዘሌ 23:6
2 ዜና 30:231ነገ 8:65
2 ዜና 30:242ዜና 35:7, 8
2 ዜና 30:242ዜና 29:34
2 ዜና 30:252ዜና 30:11, 18
2 ዜና 30:25ዘፀ 12:49
2 ዜና 30:261ነገ 8:65, 66
2 ዜና 30:27ዘኁ 6:23-26፤ ዘዳ 10:8
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
  • 23
  • 24
  • 25
  • 26
  • 27
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
2 ዜና መዋዕል 30:1-27

ሁለተኛ ዜና መዋዕል

30 ሕዝቅያስ ለእስራኤል አምላክ ለይሖዋ ፋሲካን*+ ለማክበር በኢየሩሳሌም ወደሚገኘው ወደ ይሖዋ ቤት እንዲመጡ ለእስራኤልና ለይሁዳ ሁሉ መልእክት ላከ፤+ ለኤፍሬምና ለምናሴም እንኳ ሳይቀር ደብዳቤ ጻፈ።+ 2 ይሁን እንጂ ንጉሡና መኳንንቱ እንዲሁም በኢየሩሳሌም ያለው መላው ጉባኤ ፋሲካን በሁለተኛው ወር ለማክበር ወሰኑ፤+ 3 በቂ ካህናት ራሳቸውን ስላልቀደሱና+ ሕዝቡ ገና በኢየሩሳሌም ስላልተሰበሰበ ፋሲካውን በመደበኛው ጊዜ ማክበር አልቻሉም ነበር።+ 4 ይህ ዝግጅት በንጉሡና በመላው ጉባኤ ፊት ተቀባይነት አገኘ። 5 ስለዚህ ሕዝቡ ወደ ኢየሩሳሌም መጥቶ ለእስራኤል አምላክ ለይሖዋ ፋሲካን እንዲያከብር በመላው እስራኤል፣ ከቤርሳቤህ አንስቶ እስከ ዳን+ ድረስ አዋጅ እንዲነገር ወሰኑ፤ በተጻፈው መሠረት በዓሉን በጋራ አክብረው አያውቁም ነበር።+

6 ከዚያም መልእክተኞቹ* የንጉሡንና የመኳንንቱን ደብዳቤዎች ይዘው ወደ እስራኤልና ወደ ይሁዳ ሁሉ ሄዱ፤ ንጉሡም እንዲህ የሚል ትእዛዝ አስተላልፎ ነበር፦ “የእስራኤል ሕዝብ ሆይ፣ የአብርሃም፣ የይስሐቅና የእስራኤል አምላክ ወደሆነው ወደ ይሖዋ ተመለሱ፤ እሱም ከአሦር ነገሥታት እጅ ወዳመለጡት ቀሪዎች ይመለሳል።+ 7 አሁን እንደምታዩት፣ መቀጣጫ እስኪያደርጋቸው ድረስ በአባቶቻቸው አምላክ በይሖዋ ላይ ታማኝነት የጎደለው ድርጊት እንደፈጸሙት እንደ አባቶቻችሁና እንደ ወንድሞቻችሁ አትሁኑ።+ 8 አሁንም እንደ አባቶቻችሁ አንገታችሁን አታደንድኑ።+ የሚነድ ቁጣው ከእናንተ እንዲመለስ ለይሖዋ ተገዙ፤+ ለዘላለም ወደቀደሰው መቅደሱ ኑ፤+ አምላካችሁን ይሖዋን አገልግሉ። 9 ወደ ይሖዋ ስትመለሱ ወንድሞቻችሁና ልጆቻችሁ በማረኳቸው ዘንድ ምሕረት ያገኛሉ፤+ ወደዚህች ምድር እንዲመለሱም ይለቋቸዋል፤+ አምላካችሁ ይሖዋ ሩኅሩኅና* መሐሪ ነውና፤+ ወደ እሱም ከተመለሳችሁ ፊቱን አያዞርባችሁም።”+

10 ስለዚህ መልእክተኞቹ* ከከተማ ወደ ከተማ እየተዘዋወሩ የኤፍሬምንና የምናሴን+ እንዲሁም የዛብሎንን አገር ሁሉ አዳረሱ፤ ሕዝቡ ግን ያፌዝባቸውና ይሳለቅባቸው ነበር።+ 11 ይሁን እንጂ ከአሴር፣ ከምናሴና ከዛብሎን ምድር የተወሰኑ ሰዎች ራሳቸውን ዝቅ አድርገው ወደ ኢየሩሳሌም መጡ።+ 12 በተጨማሪም የእውነተኛው አምላክ እጅ ከይሁዳ ሰዎች ጋር ስለነበር ንጉሡና መኳንንቱ በይሖዋ ቃል መሠረት ያስተላለፉትን ትእዛዝ እንዲፈጽሙ አንድ ልብ ሰጣቸው።

13 በሁለተኛው ወር+ የቂጣን በዓል+ ለማክበር እጅግ ብዙ ሕዝብ በኢየሩሳሌም ተሰበሰበ፤ ጉባኤው እጅግ ታላቅ ነበር። 14 እነሱም ተነስተው በኢየሩሳሌም የነበሩትን መሠዊያዎችና የዕጣን መሠዊያዎች ከነቃቀሉ+ በኋላ በቄድሮን ሸለቆ ውስጥ ጣሏቸው። 15 ከዚያም በሁለተኛው ወር በ14ኛው ቀን የፋሲካን መሥዋዕት አረዱ። ካህናቱና ሌዋውያኑ አፍረው ስለነበር ራሳቸውን ቀደሱ፤ ወደ ይሖዋም ቤት የሚቃጠል መባ አመጡ። 16 በእውነተኛው አምላክ ሰው በሙሴ ሕግ መሠረት የተሰጣቸውን መመሪያ ተከትለው መደበኛ ቦታቸውን ያዙ፤ ከዚያም ካህናቱ ከሌዋውያኑ እጅ የተቀበሉትን ደም ረጩ።+ 17 በጉባኤው መካከል ራሳቸውን ያልቀደሱ ብዙ ሰዎች ስለነበሩ ሌዋውያኑ ያልነጹትን ሰዎች+ ለይሖዋ ለመቀደስ የፋሲካን መሥዋዕት የማረድ ኃላፊነት ተጥሎባቸው ነበር። 18 እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሕዝብ በተለይም ከኤፍሬም፣ ከምናሴ፣+ ከይሳኮርና ከዛብሎን የመጡ ሰዎች ራሳቸውን ያላነጹ ቢሆንም የተጻፈውን መመሪያ ተላልፈው ፋሲካውን በሉ። ይሁንና ሕዝቅያስ እንዲህ ሲል ጸለየላቸው፦ “ጥሩ የሆነው+ ይሖዋ ይቅር ይበል፤ 19 የቅድስናውን መሥፈርት አሟልተው ራሳቸውን ባያነጹም+ እንኳ እውነተኛ አምላክ የሆነውን የአባቶቻቸውን አምላክ ይሖዋን ለመፈለግ ልባቸውን ያዘጋጁትን+ ሁሉ ይቅር ይበላቸው።” 20 ይሖዋም ሕዝቅያስን ሰምቶ ሕዝቡን ይቅር አለ።*

21 በመሆኑም በኢየሩሳሌም የተገኙት እስራኤላውያን የቂጣን በዓል+ ለሰባት ቀናት በታላቅ ደስታ አከበሩ፤+ ሌዋውያኑና ካህናቱም ከፍ ባለ ድምፅ ለይሖዋ የሙዚቃ መሣሪያዎቻቸውን በመጫወት በየዕለቱ ይሖዋን ያወድሱ ነበር።+ 22 በተጨማሪም ሕዝቅያስ ይሖዋን በማስተዋል ያገለግሉ የነበሩትን ሌዋውያን ሁሉ በማነጋገር አበረታታቸው።* እነሱም የኅብረት መሥዋዕቶች+ በማቅረብና ለአባቶቻቸው አምላክ ለይሖዋ ምስጋና በማቅረብ በዓሉ ተጀምሮ እስኪያበቃ ድረስ ለሰባት ቀናት በሉ።+

23 ከዚያም መላው ጉባኤ ለተጨማሪ ሰባት ቀናት በዓሉን ለማክበር ወሰነ፤ በመሆኑም እንደገና ለሰባት ቀናት በዓሉን በታላቅ ደስታ አከበሩ።+ 24 የይሁዳ ንጉሥ ሕዝቅያስም 1,000 በሬዎችና 7,000 በጎች ለጉባኤው ሰጥቶ ነበር፤ መኳንንቱ ደግሞ 1,000 በሬዎችና 10,000 በጎች ለጉባኤው አበረከቱ፤+ እጅግ ብዙ ካህናትም ራሳቸውን ቀደሱ።+ 25 መላው የይሁዳ ጉባኤ፣ ካህናቱ፣ ሌዋውያኑ፣ ከእስራኤል የመጣው መላው ጉባኤ+ እንዲሁም ከእስራኤል ምድር የመጡትና በይሁዳ የሚኖሩት የባዕድ አገር ሰዎች+ እጅግ ተደሰቱ። 26 ከእስራኤል ንጉሥ ከዳዊት ልጅ ከሰለሞን ዘመን አንስቶ በኢየሩሳሌም እንዲህ ያለ ነገር ሆኖ ስለማያውቅ በኢየሩሳሌም ታላቅ ደስታ ሆነ።+ 27 በመጨረሻም ሌዋውያኑ ካህናት ተነስተው ሕዝቡን ባረኩ፤+ አምላክም ድምፃቸውን ሰማ፤ ጸሎታቸውም ወደ ቅዱሱ መኖሪያው ወደ ሰማያት ደረሰ።

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ