የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • 2 ዜና መዋዕል 31
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

2 ዜና መዋዕል የመጽሐፉ ይዘት

      • ሕዝቅያስ የሐሰት አምልኮን አስወገደ (1)

      • ካህናቱና ሌዋውያኑ ተገቢውን ድጋፍ እንዲያገኙ ተደረገ (2-21)

2 ዜና መዋዕል 31:1

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    የቃላት መፍቻውን ተመልከት።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 30:1, 18
  • +ዘፀ 23:24
  • +ዘዳ 7:5፤ 2ነገ 18:1, 4፤ 2ዜና 14:2, 3፤ 34:1, 3
  • +ዘዳ 12:2
  • +2ዜና 23:16, 17

2 ዜና መዋዕል 31:2

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “የሰፈሮቹ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ዜና 24:1
  • +1ዜና 23:6
  • +2ዜና 8:14
  • +1ዜና 23:13, 27-30

2 ዜና መዋዕል 31:3

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 29:39
  • +ዘኁ 28:9
  • +ዘኁ 10:10
  • +ዘዳ 16:16
  • +2ዜና 30:24

2 ዜና መዋዕል 31:4

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ሙሉ በሙሉ ለይሖዋ ሕግ ማደር።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘኁ 18:21፤ ነህ 10:38, 39

2 ዜና መዋዕል 31:5

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘኁ 18:12
  • +ዘፀ 22:29፤ 23:19፤ ነህ 10:37
  • +ምሳሌ 3:9

2 ዜና መዋዕል 31:6

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 27:30፤ ዘዳ 14:28

2 ዜና መዋዕል 31:7

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 23:16
  • +ዘሌ 23:24

2 ዜና መዋዕል 31:10

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘኁ 18:8
  • +ሚል 3:10

2 ዜና መዋዕል 31:11

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “መመገቢያ ክፍሎች።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ነህ 10:38, 39፤ 12:44

2 ዜና መዋዕል 31:12

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “አሥራቱንና።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 27:30፤ ዘዳ 14:28

2 ዜና መዋዕል 31:14

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ዜና 26:17, 19
  • +ዘዳ 12:5, 6፤ 16:10
  • +ዘኁ 18:8
  • +ዘሌ 2:10፤ 7:1

2 ዜና መዋዕል 31:15

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ዜና 24:1
  • +ኢያሱ 21:19

2 ዜና መዋዕል 31:17

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘኁ 4:2, 3፤ 8:24፤ 1ዜና 23:24
  • +1ዜና 24:4
  • +1ዜና 23:6

2 ዜና መዋዕል 31:19

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 25:33, 34፤ ዘኁ 35:2፤ ኢያሱ 21:13

2 ዜና መዋዕል 31:21

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 29:35

ተዛማጅ ሐሳብ

2 ዜና 31:12ዜና 30:1, 18
2 ዜና 31:1ዘፀ 23:24
2 ዜና 31:1ዘዳ 7:5፤ 2ነገ 18:1, 4፤ 2ዜና 14:2, 3፤ 34:1, 3
2 ዜና 31:1ዘዳ 12:2
2 ዜና 31:12ዜና 23:16, 17
2 ዜና 31:21ዜና 24:1
2 ዜና 31:21ዜና 23:6
2 ዜና 31:22ዜና 8:14
2 ዜና 31:21ዜና 23:13, 27-30
2 ዜና 31:3ዘፀ 29:39
2 ዜና 31:3ዘኁ 28:9
2 ዜና 31:3ዘኁ 10:10
2 ዜና 31:3ዘዳ 16:16
2 ዜና 31:32ዜና 30:24
2 ዜና 31:4ዘኁ 18:21፤ ነህ 10:38, 39
2 ዜና 31:5ዘኁ 18:12
2 ዜና 31:5ዘፀ 22:29፤ 23:19፤ ነህ 10:37
2 ዜና 31:5ምሳሌ 3:9
2 ዜና 31:6ዘሌ 27:30፤ ዘዳ 14:28
2 ዜና 31:7ዘሌ 23:16
2 ዜና 31:7ዘሌ 23:24
2 ዜና 31:10ዘኁ 18:8
2 ዜና 31:10ሚል 3:10
2 ዜና 31:11ነህ 10:38, 39፤ 12:44
2 ዜና 31:12ዘሌ 27:30፤ ዘዳ 14:28
2 ዜና 31:141ዜና 26:17, 19
2 ዜና 31:14ዘዳ 12:5, 6፤ 16:10
2 ዜና 31:14ዘኁ 18:8
2 ዜና 31:14ዘሌ 2:10፤ 7:1
2 ዜና 31:151ዜና 24:1
2 ዜና 31:15ኢያሱ 21:19
2 ዜና 31:17ዘኁ 4:2, 3፤ 8:24፤ 1ዜና 23:24
2 ዜና 31:171ዜና 24:4
2 ዜና 31:171ዜና 23:6
2 ዜና 31:19ዘሌ 25:33, 34፤ ዘኁ 35:2፤ ኢያሱ 21:13
2 ዜና 31:212ዜና 29:35
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
2 ዜና መዋዕል 31:1-21

ሁለተኛ ዜና መዋዕል

31 ከዚህ በኋላ በዚያ የተገኙት እስራኤላውያን በሙሉ ወደ ይሁዳ ከተሞች ወጥተው በመላው ይሁዳና ቢንያም እንዲሁም በኤፍሬምና በምናሴ+ የነበሩትን የማምለኪያ ዓምዶች+ ሰባበሩ፤ የማምለኪያ ግንዶቹን*+ ቆረጡ፤ ከፍ ያሉትንም የማምለኪያ ቦታዎችና+ መሠዊያዎቹን+ አፈራረሱ፤ ምንም ያስቀሩት ነገር አልነበረም፤ ከዚህ በኋላ እስራኤላውያን በሙሉ ወደየከተሞቻቸው፣ እያንዳንዳቸውም ወደየርስታቸው ተመለሱ።

2 ከዚያም ሕዝቅያስ ካህናቱን በየምድባቸው፣+ ሌዋውያኑንም በየምድባቸው+ ሾማቸው፤ እያንዳንዱን ካህንና ሌዋዊ በተሰጠው ሥራ መሠረት ደለደለ።+ እነሱም የሚቃጠለውን መባና የኅብረት መሥዋዕቶቹን ያቀርባሉ፣ ያገለግላሉ እንዲሁም በይሖዋ ቤተ መቅደስ ዙሪያ ባሉት የግቢዎቹ* በሮች ለእሱ ምስጋናና ውዳሴ ያቀርባሉ።+ 3 በይሖዋ ሕግ ላይ በተጻፈው መሠረት ጠዋትና ማታ የሚቀርበውን መባ+ እንዲሁም በየሰንበቱ፣+ በየወር መባቻውና+ በበዓላት ወቅት+ የሚቀርቡትን የሚቃጠሉ መባዎች ጨምሮ ለሚቃጠሉት መባዎች+ እንዲውል ከንጉሡ ንብረት ላይ የተወሰነ ድርሻ ይሰጥ ነበር።

4 በተጨማሪም ሕዝቅያስ የይሖዋን ሕግ በጥብቅ መከተል* እንዲችሉ በኢየሩሳሌም የሚኖረው ሕዝብ ለካህናቱና ለሌዋውያኑ ተገቢውን ድርሻ እንዲሰጥ አዘዘ።+ 5 ትእዛዙ እንደወጣ እስራኤላውያን የእህሉን፣ የአዲሱን የወይን ጠጅ፣ የዘይቱን፣+ የማሩንና የእርሻውን ፍሬ+ ሁሉ በኩራት በብዛት ሰጡ፤ ከእያንዳንዱም ነገር ላይ አንድ አሥረኛውን አትረፍርፈው አመጡ።+ 6 በይሁዳ ከተሞች ይኖሩ የነበሩት የእስራኤልና የይሁዳ ሕዝብም ከከብቶቻቸውና ከበጎቻቸው አንድ አሥረኛውን እንዲሁም ለአምላካቸው ለይሖዋ ከተለዩት ቅዱስ የሆኑ ነገሮች ላይ አንድ አሥረኛውን አመጡ።+ ያመጡትንም ብዙ ቦታ ላይ ቆለሉት። 7 በሦስተኛው ወር+ ያመጡትን መዋጮ መከመር የጀመሩ ሲሆን በሰባተኛው ወር+ አጠናቀቁ። 8 ሕዝቅያስና መኳንንቱ መጥተው ክምሩን ባዩ ጊዜ ይሖዋን አወደሱ፤ ሕዝቡን እስራኤልንም ባረኩ።

9 ሕዝቅያስ ካህናቱንና ሌዋውያኑን ስለ ክምሩ ሲጠይቃቸው 10 ከሳዶቅ ቤት የሆነው የካህናት አለቃው አዛርያስ እንዲህ አለው፦ “መዋጮውን ወደ ይሖዋ ቤት ማምጣት+ ከጀመሩበት ጊዜ አንስቶ ሕዝቡ እስኪጠግብ ድረስ ሲበላ ቆይቷል፤ ገና ያልተነካ ብዙ ነገር አለ፤ ይሖዋ ሕዝቡን ስለባረከ ይህን ያህል ብዛት ያለው ነገር ሊተርፍ ችሏል።”+

11 በዚህ ጊዜ ሕዝቅያስ በይሖዋ ቤት ማከማቻ ክፍሎች*+ እንዲያዘጋጁ አዘዘ፤ እነሱም አዘጋጁ። 12 ከዚያም መዋጮውን፣ አንድ አሥረኛውንና*+ ቅዱስ የሆኑትን ነገሮች በታማኝነት ማምጣታቸውን ቀጠሉ፤ ሌዋዊው ኮናንያ የእነዚህ ሁሉ ነገሮች ተቆጣጣሪ ሆኖ ተሹሞ የነበረ ሲሆን ወንድሙ ሺምአይ ደግሞ የእሱ ምክትል ነበር። 13 የሂኤል፣ አዛዝያ፣ ናሃት፣ አሳሄል፣ የሪሞት፣ ዮዛባድ፣ ኤሊዔል፣ ይስማክያ፣ ማሃት እና በናያህ በንጉሥ ሕዝቅያስ ትእዛዝ ኮናንያን እና ወንድሙን ሺምአይን የሚረዱ ሹሞች ነበሩ፤ አዛርያስም የእውነተኛው አምላክ ቤት ተቆጣጣሪ ነበር። 14 የምሥራቁ በር ጠባቂ የሆነው ሌዋዊው+ የይምናህ ልጅ ቆረ ለእውነተኛው አምላክ በበጎ ፈቃድ የሚቀርቡትን መባዎች+ ይቆጣጠር ነበር፤ ደግሞም ለይሖዋ የተሰጠውን መዋጮና+ እጅግ ቅዱስ የሆኑትን ነገሮች+ ያከፋፍል ነበር። 15 በእሱም አመራር ሥር ኤደን፣ ሚንያሚን፣ የሹዋ፣ ሸማያህ፣ አማርያህ እና ሸካንያህ የነበሩ ሲሆን በየምድቦቹ ውስጥ ላሉት ወንድሞቻቸው፣+ ለትልቁም ሆነ ለትንሹ ድርሻቸውን እኩል ለማከፋፈል በካህናቱ ከተሞች+ ታማኝነት በሚጠይቅ ቦታ ላይ ተሹመው ነበር። 16 ይህም ስማቸው በትውልድ ሐረግ መዝገቡ ላይ ለሰፈሩት ሦስት ዓመትና ከዚያ በላይ ለሆናቸው ወንዶች የሚከፋፈለውን ሳይጨምር ነው፤ እነሱም በይሖዋ ቤት ለማገልገል በየዕለቱ ይመጡና እንደየምድባቸው ያሉባቸውን ኃላፊነቶች ይፈጽሙ ነበር።

17 ካህናቱ፣ 20 ዓመትና ከዚያ በላይ+ እንደሆናቸው ሌዋውያን ሁሉ በትውልድ ሐረግ መዝገቡ ላይ የሰፈሩት በየአባቶቻቸው ቤት+ እንደየምድብ ሥራቸው ነበር።+ 18 የትውልድ ሐረግ መዝገቡ ልጆቻቸውን፣ ሚስቶቻቸውን፣ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን በሙሉ፣ መላውን የሌዋውያን ማኅበረሰብ ይጨምራል፤ እነሱ በተሾሙበት ታማኝነት የሚጠይቅ ቦታ የተነሳ ቅዱስ ለሆነው ነገር ራሳቸውን ቀድሰዋል፤ 19 በተጨማሪም መዝገቡ ላይ በከተሞቻቸው ዙሪያ ባሉ የግጦሽ መሬቶች ላይ የሚኖሩት የአሮን ዘሮች የሆኑት ካህናትም ይገኛሉ።+ በሁሉም ከተሞች ውስጥ በካህናት ቤተሰብ ውስጥ ላሉት ወንዶች ሁሉና በሌዋውያን የትውልድ ሐረግ መዝገብ ላይ ለተጻፉት በሙሉ እንዲያከፋፍሉ በስም ተጠቅሰው ኃላፊነት የተሰጣቸው ወንዶች ነበሩ።

20 ሕዝቅያስ በመላው ይሁዳ ይህን አደረገ፤ በአምላኩ በይሖዋም ፊት ጥሩና ትክክል የሆነውን አደረገ፤ ለእሱም ታማኝ ነበር። 21 ከእውነተኛው አምላክ ቤት+ አገልግሎት ጋርም ሆነ ከሕጉና ከትእዛዙ ጋር በተያያዘ አምላኩን ይፈልግ ዘንድ የጀመረውን ሥራ ሁሉ፣ በሙሉ ልቡ አከናወነ፤ ደግሞም ተሳካለት።

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ