መዝሙር
የዳዊት ማህሌት።
143 ይሖዋ ሆይ፣ ጸሎቴን ስማ፤+
እርዳታ ለማግኘት የማቀርበውን ልመና አዳምጥ።
እንደ ታማኝነትህና እንደ ጽድቅህ መጠን መልስልኝ።
2 ሕያው የሆነ ማንኛውም ሰው በፊትህ ጻድቅ ሊሆን ስለማይችል፣+
አገልጋይህን ለፍርድ አታቅርበው።
3 ጠላት ያሳድደኛልና፤*
ሕይወቴንም አድቆ ከአፈር ደባልቋታል።
ከረጅም ጊዜ በፊት እንደሞቱ ሰዎች በጨለማ ቦታ እንድኖር አድርጎኛል።
8 በአንተ ታምኛለሁና፣
በማለዳ ታማኝ ፍቅርህን ልስማ።
9 ይሖዋ ሆይ፣ ከጠላቶቼ ታደገኝ።
የአንተን ጥበቃ እሻለሁ።+
10 አንተ አምላኬ ስለሆንክ፣
ፈቃድህን እንድፈጽም አስተምረኝ።+
መንፈስህ ጥሩ ነው፤
በደልዳላ መሬት* ይምራኝ።
11 ይሖዋ ሆይ፣ ለስምህ ስትል በሕይወት አቆየኝ።