የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • መዝሙር 144
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

መዝሙር የመጽሐፉ ይዘት

      • ድል ለመቀዳጀት የቀረበ ጸሎት

        • “ሟች የሆነው የሰው ልጅ ምንድን ነው?” (3)

        • ‘ጠላቶች ይበተኑ’ (6)

        • የይሖዋ ሕዝብ ደስተኛ ነው (15)

መዝሙር 144:1

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ሳሙ 22:35፤ መዝ 18:2, 34
  • +ዘዳ 32:4

መዝሙር 144:2

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ሳሙ 22:2, 3
  • +መዝ 18:47

መዝሙር 144:3

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 8:4፤ ዕብ 2:6

መዝሙር 144:4

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 39:5
  • +1ዜና 29:15፤ ኢዮብ 14:1, 2

መዝሙር 144:5

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “አጥፈህ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 18:9
  • +ዘፀ 19:18

መዝሙር 144:6

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢዮብ 36:32
  • +2ሳሙ 22:15

መዝሙር 144:7

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “መዳፍ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ሳሙ 22:17, 18፤ መዝ 18:16, 17፤ 54:3

መዝሙር 144:8

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ቀኝ እጃቸውም የውሸት ቀኝ እጅ ናት።”

መዝሙር 144:9

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 33:3፤ 40:3፤ 96:1፤ ኢሳ 42:10፤ ራእይ 5:9፤ 14:3

መዝሙር 144:10

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “መዳን።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ሳሙ 5:19፤ መዝ 18:50
  • +1ሳሙ 17:45, 46፤ 2ሳሙ 21:15, 17

መዝሙር 144:15

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 33:12፤ 37:9, 37፤ 146:5

ተዛማጅ ሐሳብ

መዝ. 144:12ሳሙ 22:35፤ መዝ 18:2, 34
መዝ. 144:1ዘዳ 32:4
መዝ. 144:22ሳሙ 22:2, 3
መዝ. 144:2መዝ 18:47
መዝ. 144:3መዝ 8:4፤ ዕብ 2:6
መዝ. 144:4መዝ 39:5
መዝ. 144:41ዜና 29:15፤ ኢዮብ 14:1, 2
መዝ. 144:5መዝ 18:9
መዝ. 144:5ዘፀ 19:18
መዝ. 144:6ኢዮብ 36:32
መዝ. 144:62ሳሙ 22:15
መዝ. 144:72ሳሙ 22:17, 18፤ መዝ 18:16, 17፤ 54:3
መዝ. 144:9መዝ 33:3፤ 40:3፤ 96:1፤ ኢሳ 42:10፤ ራእይ 5:9፤ 14:3
መዝ. 144:102ሳሙ 5:19፤ መዝ 18:50
መዝ. 144:101ሳሙ 17:45, 46፤ 2ሳሙ 21:15, 17
መዝ. 144:15መዝ 33:12፤ 37:9, 37፤ 146:5
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
መዝሙር 144:1-15

መዝሙር

የዳዊት መዝሙር።

144 እጆቼን ለውጊያ፣

ጣቶቼንም ለጦርነት የሚያሠለጥነው፣+

ዓለቴ የሆነው ይሖዋ+ ይወደስ።

 2 እሱ ታማኝ ፍቅር የሚያሳየኝ አምላኬና ምሽጌ፣

አስተማማኝ መጠጊያዬና ታዳጊዬ፣

ጋሻዬና መጠለያዬ፣+

ሕዝቦችን ከበታቼ የሚያስገዛልኝ አምላኬ ነው።+

 3 ይሖዋ ሆይ፣ ታስተውለው ዘንድ ሰው ምንድን ነው?

ቦታ ትሰጠውስ ዘንድ ሟች የሆነው የሰው ልጅ ምንድን ነው?+

 4 ሰው እንደ እስትንፋስ ነው፤+

ዘመኑ እንደሚያልፍ ጥላ ነው።+

 5 ይሖዋ ሆይ፣ ሰማያትህን ወደ ታች ዝቅ አድርገህ* ውረድ፤+

ተራሮችን ዳስሰህ እንዲጨሱ አድርግ።+

 6 መብረቅ ልከህ ጠላትን በትን፤+

ፍላጻዎችህን ወርውረህ ግራ አጋባቸው።+

 7 እጆችህን ከላይ ዘርጋ፤

ከሚያጥለቀልቅ ውኃ ታደገኝ፤ ደግሞም አድነኝ፤

ከባዕድ አገር ሰዎች እጅ* አስጥለኝ፤+

 8 እነሱ በአፋቸው ውሸት ይናገራሉ፤

ደግሞም በውሸት ለመማል ቀኝ እጃቸውን ወደ ላይ ያነሳሉ።*

 9 አምላክ ሆይ፣ አዲስ መዝሙር እዘምርልሃለሁ።+

አሥር አውታር ባለው መሣሪያ የታጀበ የውዳሴ መዝሙር እዘምርልሃለሁ፤

10 እሱ ነገሥታትን ድል* ያጎናጽፋል፤+

አገልጋዩን ዳዊትን ከገዳይ ሰይፍ ይታደጋል።+

11 ከባዕድ አገር ሰዎች እጅ ታደገኝ፤ አድነኝም፤

እነሱ በአፋቸው ውሸት ይናገራሉ፤

ደግሞም በውሸት ለመማል ቀኝ እጃቸውን ወደ ላይ ያነሳሉ።

12 ያን ጊዜ ወንዶች ልጆቻችን በፍጥነት እንደሚያድጉ ችግኞች፣

ሴቶች ልጆቻችን ደግሞ ቤተ መንግሥት ለማስጌጥ እንደተቀረጹ የማዕዘን ዓምዶች ይሆናሉ።

13 ጎተራዎቻችን በልዩ ልዩ የእህል ዓይነቶች ጢም ብለው ይሞላሉ፤

በመስክ ያሉት መንጎቻችን ተራብተው ሺዎች ደግሞም አሥር ሺዎች ይሆናሉ።

14 የከበዱት ከብቶቻችን ጉዳት አይደርስባቸውም ወይም አይጨነግፉም፤

በአደባባዮቻችን ላይ የጭንቅ ዋይታ አይሰማም።

15 ይህ የሚሆንለት ሕዝብ ደስተኛ ነው!

አምላኩ ይሖዋ የሆነለት ሕዝብ ደስተኛ ነው!+

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ