መዝሙር
ስለ ሰለሞን የተዘመረ መዝሙር።
72 አምላክ ሆይ፣ ፍርዶችህን ለንጉሡ ስጥ፤
ጽድቅህንም ለንጉሡ ልጅ አጎናጽፍ።+
2 ስለ ሕዝብህ በጽድቅ ይሟገት፤
ለተቸገሩ አገልጋዮችህም ፍትሕ ያስፍን።+
3 ተራሮች ለሕዝቡ ሰላም ያምጡ፤
ኮረብቶችም ጽድቅን ያስገኙ።
6 እሱ በታጨደ ሣር ላይ እንደሚዘንብ ዝናብ፣
ምድርንም እንደሚያጠጣ ካፊያ ይወርዳል።+
9 በበረሃ የሚኖሩ ሰዎች በፊቱ ይሰግዳሉ፤
ጠላቶቹም አፈር ይልሳሉ።+
10 የተርሴስና የደሴቶች ነገሥታት፣ ግብር ያመጣሉ።+
የሳባና የሴባ ነገሥታት፣ ስጦታ ይሰጣሉ።+
11 ነገሥታትም ሁሉ በፊቱ ይሰግዳሉ፤
ብሔራትም ሁሉ ያገለግሉታል።
12 እርዳታ ለማግኘት የሚጮኸውን ድሃ፣
እንዲሁም ችግረኛውንና ረዳት የሌለውን ሁሉ ይታደጋልና።
13 ለችግረኛውና ለድሃው ያዝናል፤
የድሆችንም ሕይወት* ያድናል።
14 ከጭቆናና ከግፍ ይታደጋቸዋል፤*
ደማቸውም በዓይኖቹ ፊት ክቡር ነው።
15 ረጅም ዘመን ይኑር፤ የሳባም ወርቅ ይሰጠው።+
ስለ እሱም ሁልጊዜ ጸሎት ይቅረብ፤
ቀኑንም ሙሉ ይባረክ።
16 በምድር ላይ እህል ይትረፈረፋል፤+
በተራሮችም አናት ላይ በብዛት ይኖራል።
17 ስሙ ለዘላለም ጸንቶ ይኑር፤+
ፀሐይም እስካለች ድረስ ስሙ ይግነን።
ሰዎች በእሱ አማካኝነት ለራሳቸው በረከት ያግኙ፤+
ብሔራት ሁሉ ደስተኛ ብለው ይጥሩት።
አሜን፣ አሜን።
20 የእሴይ ልጅ+ የዳዊት ጸሎቶች እዚህ ላይ አበቁ።