የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • መኃልየ መኃልይ 4
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

መኃልየ መኃልይ የመጽሐፉ ይዘት

    • ሱላማዊቷ በኢየሩሳሌም (3:6–8:4)

መኃልየ መኃልይ 4:1

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘኁ 32:1፤ ዘዳ 3:12፤ መኃ 6:5-7

መኃልየ መኃልይ 4:3

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ሰሪሳራዎችሽ።” በዓይንና በጆሮ መካከል ያለውን የአካል ክፍል ያመለክታል።

መኃልየ መኃልይ 4:4

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መኃ 1:10
  • +2ሳሙ 8:7፤ 2ነገ 11:10
  • +ነህ 3:25፤ መኃ 7:4

መኃልየ መኃልይ 4:5

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መኃ 7:3

መኃልየ መኃልይ 4:6

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መክ 2:5

መኃልየ መኃልይ 4:7

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መኃ 4:1

መኃልየ መኃልይ 4:8

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 3:25
  • +ዘዳ 3:8, 9፤ መዝ 133:3

መኃልየ መኃልይ 4:9

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ምሳሌ 5:18, 19

መኃልየ መኃልይ 4:10

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መኃ 7:12
  • +አስ 2:12፤ መኃ 1:12
  • +መኃ 1:2, 4

መኃልየ መኃልይ 4:11

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ምሳሌ 16:24
  • +መኃ 5:1

መኃልየ መኃልይ 4:13

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    “ገላሽ” ማለትም ሊሆን ይችላል።

  • *

    ወይም “የአትክልት ስፍራ።”

መኃልየ መኃልይ 4:14

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    የአበባ ዓይነት ነው።

  • *

    በመጽሐፍ ቅዱስ ዘመን ሽቶ ለመሥራት የሚያገለግል ጥሩ መዓዛ ያለው ንጥረ ነገር የሚገኝበትን ዛፍ ያመለክታል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዮሐ 12:3
  • +ኢሳ 43:24
  • +ምሳሌ 7:17
  • +መዝ 45:8
  • +ዘፀ 30:23, 24, 34፤ ሕዝ 27:2, 22

መኃልየ መኃልይ 4:15

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 18:14

መኃልየ መኃልይ 4:16

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “በቀስታ ንፈስ።”

ተዛማጅ ሐሳብ

መኃ. 4:1ዘኁ 32:1፤ ዘዳ 3:12፤ መኃ 6:5-7
መኃ. 4:4መኃ 1:10
መኃ. 4:42ሳሙ 8:7፤ 2ነገ 11:10
መኃ. 4:4ነህ 3:25፤ መኃ 7:4
መኃ. 4:5መኃ 7:3
መኃ. 4:6መክ 2:5
መኃ. 4:7መኃ 4:1
መኃ. 4:8ዘዳ 3:25
መኃ. 4:8ዘዳ 3:8, 9፤ መዝ 133:3
መኃ. 4:9ምሳሌ 5:18, 19
መኃ. 4:10መኃ 7:12
መኃ. 4:10አስ 2:12፤ መኃ 1:12
መኃ. 4:10መኃ 1:2, 4
መኃ. 4:11ምሳሌ 16:24
መኃ. 4:11መኃ 5:1
መኃ. 4:14ዮሐ 12:3
መኃ. 4:14ኢሳ 43:24
መኃ. 4:14ምሳሌ 7:17
መኃ. 4:14መዝ 45:8
መኃ. 4:14ዘፀ 30:23, 24, 34፤ ሕዝ 27:2, 22
መኃ. 4:15ኤር 18:14
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
መኃልየ መኃልይ 4:1-16

መኃልየ መኃልይ

4 “ፍቅሬ ሆይ፣ እነሆ፣ አንቺ ውብ ነሽ።

እነሆ፣ አንቺ ውብ ነሽ።

ዓይኖችሽ በፊትሽ መሸፈኛ ውስጥ ሲታዩ እንደ ርግብ ዓይኖች ናቸው።

ፀጉርሽ ከጊልያድ+ ተራሮች

እየተግተለተለ እንደሚወርድ የፍየል መንጋ ነው።

 2 ጥርሶችሽ ገና ተሸልተውና

ታጥበው እንደወጡ፣

ሁሉም መንታ መንታ እንደወለዱ የበግ መንጋ ናቸው፤

ደግሞም ከመካከላቸው ግልገሉን ያጣ የለም።

 3 ከንፈሮችሽ እንደ ደማቅ ቀይ ፈትል ናቸው፤

ንግግርሽም አስደሳች ነው።

በመሸፈኛሽ ውስጥ ያሉት ጉንጮችሽ*

የተከፈለ ሮማን ይመስላሉ።

 4 አንገትሽ+ አንድ ሺህ ጋሻዎች፣

ይኸውም ኃያላን ሰዎች የሚይዟቸው ክብ ጋሻዎች+ ሁሉ የተንጠለጠሉበትንና

በንብርብር ድንጋዮች የተገነባውን

የዳዊት ማማ+ ይመስላል።

 5 ሁለቱ ጡቶችሽ

በአበቦች መካከል የተሰማሩ፣

መንታ የሆኑ ሁለት የሜዳ ፍየል ግልገሎችን ይመስላሉ።”+

 6 “የቀኑ ነፋስ መንፈስ ከመጀመሩና ጥላው ከመሸሹ በፊት

ወደ ከርቤው ተራራና

ወደ ነጭ ዕጣኑ ኮረብታ እሄዳለሁ።”+

 7 “ፍቅሬ ሆይ፣ ሁለንተናሽ ውብ ነው፤+

እንከንም የለብሽም።

 8 ሙሽራዬ ሆይ፣ ተያይዘን ከሊባኖስ እንሂድ፤

አዎ፣ ከሊባኖስ+ አብረን እንሂድ።

ከአማና አናት፣

ከሰኒር ጫፍ፣ ከሄርሞን+ አናት፣

ከአንበሳ ዋሻዎች፣ ከነብር ተራሮች ውረጂ።

 9 እህቴ፣ ሙሽራዬ ሆይ፣ ልቤን ማርከሽዋል፤+

በአንድ አፍታ እይታሽ፣

ከሐብልሽ ዶቃዎች በአንዱ ልቤን ማርከሽዋል።

10 እህቴ፣ ሙሽራዬ ሆይ፣ የፍቅር መግለጫዎችሽ እንዴት ደስ ያሰኛሉ!+

የፍቅር መግለጫሽ ከወይን ጠጅ፣

የሽቶሽም መዓዛ ከየትኛውም ዓይነት ቅመም+ እጅግ ይበልጣል!+

11 ሙሽራዬ ሆይ፣ ከንፈሮችሽ የማር እንጀራ ወለላ ያንጠባጥባሉ።+

ከምላስሽ ሥር ማርና ወተት ይፈልቃል፤+

የልብሶችሽም ጠረን እንደ ሊባኖስ መዓዛ ነው።

12 እህቴ፣ ሙሽራዬ፣ የተቆለፈ የአትክልት ቦታ፣

አዎ የተቆለፈ የአትክልት ቦታ፣ የታሸገም ምንጭ ናት።

13 ቡቃያሽ* ሮማንና ምርጥ ፍራፍሬዎች

ደግሞም የሂና እና የናርዶስ ተክሎች የበቀሉበት ገነት* ነው፤

14 በተጨማሪም ናርዶስ፣+ ሳፍሮን፣* ጠጅ ሣር፣+ ቀረፋ፣+

ነጭ ዕጣን የሚገኝባቸው የተለያዩ ዛፎች፣ ከርቤ፣ እሬትና*+

ሁሉም ዓይነት ምርጥ ሽቶዎች+ ያሉበት ገነት ነው።

15 አንቺ በአትክልት ቦታ ያለ ምንጭ፣ ንጹሕ ውኃ የሚገኝበት ጉድጓድና

ከሊባኖስ የሚፈስሱ ጅረቶች ነሽ።+

16 የሰሜን ነፋስ ሆይ፣ ንቃ፤

የደቡብ ነፋስ ሆይ፣ ና።

በአትክልት ቦታዬ ላይ ንፈስ።*

መዓዛውም አካባቢውን ያውደው።”

“ውዴ ወደ አትክልት ቦታው ይግባና

ምርጥ የሆኑትን ፍራፍሬዎች ይብላ።”

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ