የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • መኃልየ መኃልይ 5
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

መኃልየ መኃልይ የመጽሐፉ ይዘት

    • ሱላማዊቷ በኢየሩሳሌም (3:6–8:4)

መኃልየ መኃልይ 5:1

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መኃ 4:16
  • +መኃ 4:13, 14
  • +መኃ 4:11
  • +መኃ 1:2

መኃልየ መኃልይ 5:2

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መኃ 3:1
  • +ሉቃስ 2:8

መኃልየ መኃልይ 5:6

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ነፍሴ ሄደች።” “እሱ በተናገረ ጊዜ ነፍሴ ትታኝ ሄደች” ማለትም ሊሆን ይችላል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መኃ 3:1, 3

መኃልየ መኃልይ 5:7

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “መሸፈኛዬን።”

መኃልየ መኃልይ 5:11

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    “እንደ ቴምር ዘለላ” ማለትም ሊሆን ይችላል።

መኃልየ መኃልይ 5:12

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    “በምንጩ ዳርቻ” ማለትም ሊሆን ይችላል።

መኃልየ መኃልይ 5:13

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መኃ 6:2
  • +መኃ 1:13

መኃልየ መኃልይ 5:15

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 92:12

መኃልየ መኃልይ 5:16

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ላንቃው።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መኃ 2:3

ተዛማጅ ሐሳብ

መኃ. 5:1መኃ 4:16
መኃ. 5:1መኃ 4:13, 14
መኃ. 5:1መኃ 4:11
መኃ. 5:1መኃ 1:2
መኃ. 5:2መኃ 3:1
መኃ. 5:2ሉቃስ 2:8
መኃ. 5:6መኃ 3:1, 3
መኃ. 5:13መኃ 6:2
መኃ. 5:13መኃ 1:13
መኃ. 5:15መዝ 92:12
መኃ. 5:16መኃ 2:3
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
መኃልየ መኃልይ 5:1-16

መኃልየ መኃልይ

5 “እህቴ፣ ሙሽራዬ ሆይ፣

ወደ አትክልት ቦታዬ ገብቻለሁ።+

ከርቤዬንና ቅመሜን+ ወስጃለሁ።

የማር እንጀራዬንና ወለላውን በልቻለሁ፤

የወይን ጠጄንና ወተቴን ጠጥቻለሁ።”+

“ውድ ጓደኞቼ፣ ብሉ!

ጠጥታችሁም በፍቅር መግለጫዎች ስከሩ!”+

 2 “እኔ ተኝቻለሁ፤ ልቤ ግን ነቅቷል።+

ውዴ በሩን ሲያንኳኳ ይሰማኛል!

‘እህቴ ሆይ፣ የእኔ ፍቅር፣

እንከን የለሽ ርግቤ ሆይ፣ ክፈቺልኝ!

ራሴ በጤዛ፣

ፀጉሬም በሌሊቱ እርጥበት ርሷል።’+

 3 ልብሴን አውልቄአለሁ።

መልሼ መልበስ ሊኖርብኝ ነው?

እግሬን ታጥቤአለሁ።

እንደገና ላቆሽሸው ነው?

 4 ውዴ እጁን ከበሩ ቀዳዳ መለሰ፤

ለእሱ ያለኝ ስሜትም ተነሳሳ።

 5 እኔም ለውዴ በሩን ለመክፈት ተነሳሁ፤

የመዝጊያው እጀታ ላይ

እጆቼ ከርቤ፣

ጣቶቼም የከርቤ ፈሳሽ አንጠባጠቡ።

 6 ለውዴ በሩን ከፈትኩለት፤

ውዴ ግን በዚያ አልነበረም፤ ሄዶ ነበር።

በመሄዱም ተስፋ ቆረጥኩ።*

ፈለግኩት፤ ግን አላገኘሁትም።+

ጠራሁት፤ እሱ ግን አልመለሰልኝም።

 7 ከተማዋን እየተዘዋወሩ የሚጠብቁት ሰዎች አገኙኝ።

መቱኝ፤ አቆሰሉኝ።

የቅጥሩ ጠባቂዎች ነጠላዬን* ገፈፉኝ።

 8 የኢየሩሳሌም ሴቶች ልጆች ሆይ፣

ውዴን ካገኛችሁት በፍቅሩ ተይዤ መታመሜን

እንድትነግሩት አምላችኋለሁ።”

 9 “አንቺ ከሴቶች ሁሉ እጅግ የተዋብሽ ሆይ፣

ውድሽ ሌሎች ከሚያፈቅሯቸው ወንዶች ሁሉ እንዴት ቢበልጥ ነው?

እንዲህ ያለ መሐላ ያስገባሽን፣

ለመሆኑ ውድሽ ሌሎች ከሚያፈቅሯቸው ወንዶች ሁሉ እንዴት ቢበልጥ ነው?”

10 “ውዴ በጣም ቆንጆና ቀይ ነው፤

በአሥር ሺህ ሰዎች መካከል እንኳ ጎልቶ ይታያል።

11 ራሱ እንደ ወርቅ፣ አዎ እንደጠራ ወርቅ ነው።

ፀጉሩ እንደሚወዛወዝ የዘንባባ ዝንጣፊ* ነው፤

እንደ ቁራም ጥቁር ነው።

12 ዓይኖቹ በውኃ ጅረት አጠገብ እንዳሉ፣

ጢም ብሎ በሞላ ኩሬ ዳርቻ* ሆነው

በወተት እንደሚታጠቡ ርግቦች ናቸው።

13 ጉንጮቹ የቅመማ ቅመም መደብ፣+

ጥሩ መዓዛ ያላቸው ዕፀዋት ክምር ይመስላሉ።

ከንፈሮቹ ፈሳሽ ከርቤ የሚያንጠባጥቡ አበቦች ናቸው።+

14 የእጆቹ ጣቶች ወርቅ፣ የጣቶቹም ጫፎች ክርስቲሎቤ ናቸው።

ሆዱ በሰንፔር የተሸፈነ የተወለወለ የዝሆን ጥርስ ነው።

15 እግሮቹ ከምርጥ ወርቅ በተሠሩ መሰኪያዎች ላይ የቆሙ የእብነ በረድ ዓምዶች ናቸው።

መልኩ እንደ ሊባኖስ ያማረ ነው፤ እንደ አርዘ ሊባኖስም አቻ የለውም።+

16 አፉ* እጅግ ጣፋጭ ነው፤

ሁለመናውም ደስ ያሰኛል።+

የኢየሩሳሌም ሴቶች ልጆች ሆይ፣ ውዴ ይህ ነው፤ ፍቅሬ እንዲህ ያለ ነው።”

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ