ኢሳይያስ
5 እስቲ ለወዳጄ መዝሙር ልዘምር።
መዝሙሩ ስለ ወዳጄና ስለ ወይን እርሻው+ የሚገልጽ ነው።
ወዳጄ ለም በሆነ ኮረብታ ላይ የወይን እርሻ ነበረው።
2 እሱም መሬቱን ቆፈረ፤ ድንጋዮቹንም አስወገደ።
ከዚያም ‘ወይኑ ጥሩ ፍሬ ያፈራል’ ብሎ ይጠብቅ ጀመር፤
ይሁንና መጥፎ ፍሬ ብቻ አፈራ።+
3 “እናንተ የኢየሩሳሌም ነዋሪዎችና የይሁዳ ሰዎች ሆይ፣
በእኔና በወይን እርሻዬ መካከል እስቲ ፍረዱ።+
4 ለወይን እርሻዬ ከዚህ በላይ ላደርግለት የሚገባ
ምን ነገር አለ?+
‘ጥሩ ወይን ያፈራል’ ብዬ ስጠብቅ
መጥፎ ወይን ብቻ ያፈራው ለምንድን ነው?
5 እንግዲህ በወይን እርሻዬ ላይ
ምን እንደማደርግ ልንገራችሁ፦
በዙሪያው ያለውን የቁጥቋጦ አጥር እነቅላለሁ፤
ለእሳትም ይማገዳል።+
የድንጋይ ቅጥሩን አፈርሳለሁ፤
በእግርም ይረጋገጣል።
6 ቦታውን ጠፍ መሬት አደርገዋለሁ፤+
የወይን ተክሉ አይገረዝም እንዲሁም አይኮተኮትም።
11 የሚያሰክር መጠጥ ለመጠጣት በማለዳ ለሚነሱ፣+
የወይን ጠጅ እስከሚያቃጥላቸው ድረስ እስከ ሌሊት ለሚያመሹ ወዮላቸው!
12 በግብዣቸው ላይ በገና፣ ባለ አውታር መሣሪያ፣
አታሞና ዋሽንት እንዲሁም የወይን ጠጅ አለ፤
እነሱ ግን ይሖዋ ያከናወነውን ተግባር አያስቡም፤
የእጁንም ሥራ አይመለከቱም።
15 ሰውም አንገቱን ይደፋል፤
የሰው ልጅ ኀፍረት ይከናነባል፤
የትዕቢተኞችም ዓይን ይዋረዳል።
17 የበግ ጠቦቶችም በገዛ መሰማሪያቸው እንደተሰማሩ ሆነው ይግጣሉ፤
የባዕድ አገር ሰዎች፣ የሰቡ እንስሳት ይኖሩባቸው በነበሩ ወና የሆኑ ቦታዎች ይበላሉ።
18 በደላቸውን በአታላይ ገመድ የሚስቡ፣
ኃጢአታቸውንም በሠረገላ ገመድ የሚጎትቱ ወዮላቸው፤
19 “ሥራውን ያፋጥን፤
እናየውም ዘንድ ቶሎ ይምጣ።
21 በገዛ ዓይናቸው ጥበበኛ የሆኑና
በራሳቸው አመለካከት ልባም የሆኑ ወዮላቸው!+
22 የወይን ጠጅ በመጠጣት ረገድ ብርቱዎች የሆኑ፣
መጠጥ በመደባለቅም የተካኑ ወዮላቸው፤+
23 ጉቦ በመቀበል ክፉውን ከበደል ነፃ የሚያደርጉ፣+
ጻድቁንም ፍትሕ የሚነፍጉ ወዮላቸው!+
24 የእሳት ነበልባል ገለባን እንደሚበላ፣
የደረቀም ሣር በነበልባል በንኖ እንደሚጠፋ
የእነሱም ሥር ይበሰብሳል፤
አበባቸውም ልክ እንደ ዱቄት በየቦታው ይበናል፤
ምክንያቱም እነሱ የሠራዊት ጌታ የሆነውን የይሖዋን ሕግ* ለመቀበል አሻፈረን ብለዋል፣
የእስራኤል ቅዱስ የተናገረውንም ቃል ንቀዋል።+
25 የይሖዋ ቁጣ በሕዝቡ ላይ የነደደው በዚህ ምክንያት ነው፤
እሱም እጁን በእነሱ ላይ ይዘረጋል፤ ይመታቸዋልም።+
ተራሮችም ይናወጣሉ፤
አስከሬናቸውም በጎዳናዎች ላይ እንዳለ ቆሻሻ ይሆናል።+
ከዚህ ሁሉ የተነሳ ቁጣው አልተመለሰም፤
ይልቁንም እጁ ለመምታት ገና እንደተዘረጋ ነው።
27 ከእነሱ መካከል የደከመም ሆነ የሚደናቀፍ አንድም ሰው የለም።
የሚያንጎላጅም ሆነ የሚተኛ የለም።
በወገባቸውም ላይ ያለው ቀበቶ አልተፈታም፤
እንዲሁም የጫማቸው ማሠሪያ አልተበጠሰም።
28 ፍላጻዎቻቸው ሁሉ የሾሉ፣
ደጋኖቻቸውም በሙሉ የተወጠሩ* ናቸው።
29 ጩኸታቸው እንደ አንበሳ ነው፤
እንደ ደቦል አንበሳ ያገሳሉ።+
የጉርምርምታ ድምፅ እያሰሙ አድብተው ይይዛሉ፤
ከእጃቸውም የሚያስጥል ስለሌለ ተሸክመውት ይሄዳሉ።
30 በዚያም ቀን እንደ ባሕር ሞገድ
ያጉረመርሙበታል።+
ምድሪቷን ትኩር ብሎ የሚመለከት ማንኛውም ሰው የሚያስጨንቅ ጨለማ ያያል፤
ብርሃኑም እንኳ ከደመናው የተነሳ ጨልሟል።+