የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ዘካርያስ 14
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

ዘካርያስ የመጽሐፉ ይዘት

      • እውነተኛው አምልኮ የሚቀዳጀው የተሟላ ድል (1-21)

        • የደብረ ዘይት ተራራ ለሁለት ይከፈላል (4)

        • “ይሖዋ አንድ፣ ስሙም አንድ ይሆናል” (9)

        • አምላክ ኢየሩሳሌምን የሚቃወሙትን ይቀስፋል (12-15)

        • የዳስ በዓል (16-19)

        • ድስቶች በሙሉ ለይሖዋ የተቀደሱ ይሆናሉ (20, 21)

ዘካርያስ 14:1

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    በዘካ 14:2 ላይ የተገለጸችውን ከተማ ያመለክታል።

ዘካርያስ 14:3

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 15:3፤ 2ዜና 20:15፤ ሕዝ 38:23፤ ኢዩ 3:2, 14፤ ራእይ 16:14

ዘካርያስ 14:4

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ከፀሐይ መውጫ።”

  • *

    ቃል በቃል “ባሕሩ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሉቃስ 19:29፤ ሥራ 1:12

ዘካርያስ 14:5

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +አሞጽ 1:1
  • +ዘዳ 33:2፤ ኢዩ 3:11፤ ይሁዳ 14

ዘካርያስ 14:6

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “መንቀሳቀስ ያቅታቸዋል።” በቅዝቃዜ የደረቁ ያህል ይሆናሉ።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 13:9, 10፤ አሞጽ 5:18

ዘካርያስ 14:7

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢዩ 2:31፤ 1ተሰ 5:2፤ 2ጴጥ 3:10

ዘካርያስ 14:8

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ሙት ባሕርን ያመለክታል።

  • *

    ሜድትራንያንን ያመለክታል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ራእይ 21:6፤ 22:17
  • +ኤር 17:13፤ ሕዝ 47:1፤ ኢዩ 3:18፤ ራእይ 22:1
  • +ዘዳ 3:17
  • +ኢያሱ 1:4

ዘካርያስ 14:9

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 97:1፤ ራእይ 19:6
  • +ዘዳ 6:4
  • +ኢሳ 42:8፤ 44:6

ዘካርያስ 14:10

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “የጭማቂ ማጠራቀሚያዎች።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 15:22
  • +1ዜና 4:24, 32
  • +ዘዳ 1:7
  • +ኤር 30:18
  • +ኤር 37:13
  • +ነህ 3:1፤ ኤር 31:38

ዘካርያስ 14:11

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 60:18፤ ኤር 31:40
  • +ኤር 23:6፤ 33:16

ዘካርያስ 14:12

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 19:34, 35፤ ኢዩ 3:2

ዘካርያስ 14:13

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “አንዱም በሌላው ላይ ጥቃት ይሰነዝራል።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መሳ 7:22፤ ሕዝ 38:21

ዘካርያስ 14:14

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 14:13፤ 20:25፤ ዘካ 2:8, 9

ዘካርያስ 14:16

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ይሖዋን ለማምለክና።”

  • *

    ወይም “የጊዜያዊ መጠለያ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 86:9
  • +ዘሌ 23:34፤ ነህ 8:14, 15
  • +ኢሳ 66:23

ዘካርያስ 14:17

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 60:12

ዘካርያስ 14:20

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 28:36፤ 39:30
  • +1ሳሙ 2:13, 14
  • +ዘፀ 25:29፤ ዘኁ 4:7

ዘካርያስ 14:21

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    “ነጋዴ” ማለትም ሊሆን ይችላል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሕዝ 44:9

ተዛማጅ ሐሳብ

ዘካ. 14:3ዘፀ 15:3፤ 2ዜና 20:15፤ ሕዝ 38:23፤ ኢዩ 3:2, 14፤ ራእይ 16:14
ዘካ. 14:4ሉቃስ 19:29፤ ሥራ 1:12
ዘካ. 14:5አሞጽ 1:1
ዘካ. 14:5ዘዳ 33:2፤ ኢዩ 3:11፤ ይሁዳ 14
ዘካ. 14:6ኢሳ 13:9, 10፤ አሞጽ 5:18
ዘካ. 14:7ኢዩ 2:31፤ 1ተሰ 5:2፤ 2ጴጥ 3:10
ዘካ. 14:8ራእይ 21:6፤ 22:17
ዘካ. 14:8ኤር 17:13፤ ሕዝ 47:1፤ ኢዩ 3:18፤ ራእይ 22:1
ዘካ. 14:8ዘዳ 3:17
ዘካ. 14:8ኢያሱ 1:4
ዘካ. 14:9መዝ 97:1፤ ራእይ 19:6
ዘካ. 14:9ዘዳ 6:4
ዘካ. 14:9ኢሳ 42:8፤ 44:6
ዘካ. 14:101ነገ 15:22
ዘካ. 14:101ዜና 4:24, 32
ዘካ. 14:10ዘዳ 1:7
ዘካ. 14:10ኤር 30:18
ዘካ. 14:10ኤር 37:13
ዘካ. 14:10ነህ 3:1፤ ኤር 31:38
ዘካ. 14:11ኢሳ 60:18፤ ኤር 31:40
ዘካ. 14:11ኤር 23:6፤ 33:16
ዘካ. 14:122ነገ 19:34, 35፤ ኢዩ 3:2
ዘካ. 14:13መሳ 7:22፤ ሕዝ 38:21
ዘካ. 14:142ዜና 14:13፤ 20:25፤ ዘካ 2:8, 9
ዘካ. 14:16መዝ 86:9
ዘካ. 14:16ዘሌ 23:34፤ ነህ 8:14, 15
ዘካ. 14:16ኢሳ 66:23
ዘካ. 14:17ኢሳ 60:12
ዘካ. 14:20ዘፀ 28:36፤ 39:30
ዘካ. 14:201ሳሙ 2:13, 14
ዘካ. 14:20ዘፀ 25:29፤ ዘኁ 4:7
ዘካ. 14:21ሕዝ 44:9
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
ዘካርያስ 14:1-21

ዘካርያስ

14 “እነሆ፣ የይሖዋ ቀን ይመጣል፤ በዚያን ጊዜ ከአንቺ* የተማረከው በመካከልሽ ይከፋፈላል። 2 ኢየሩሳሌምን እንዲወጉ ብሔራትን ሁሉ እሰበስባለሁ፤ ከተማዋም ትያዛለች፤ ቤቶቹ ይዘረፋሉ፤ ሴቶቹም ይደፈራሉ። የከተማዋም እኩሌታ ለግዞት ይዳረጋል፤ ከሕዝቡ መካከል የሚቀሩት ሰዎች ግን ከከተማዋ አይወገዱም።

3 “ይሖዋ ይወጣል፤ በጦርነት ቀን እንደሚዋጋው እነዚያን ብሔራት ይዋጋል።+ 4 በዚያ ቀን እግሮቹ በስተ ምሥራቅ በኢየሩሳሌም ትይዩ በሚገኘው በደብረ ዘይት ተራራ+ ላይ ይቆማሉ፤ የደብረ ዘይት ተራራም ከምሥራቅ* አንስቶ እስከ ምዕራብ* ድረስ ለሁለት ይከፈላል፤ እጅግ ትልቅ ሸለቆም ይፈጠራል፤ የተራራው አንዱ ግማሽ ወደ ሰሜን፣ ሌላው ግማሽ ደግሞ ወደ ደቡብ ፈቀቅ ይላል። 5 እናንተ በተራሮቼ መካከል ወዳለው ሸለቆ ትሸሻላችሁ፤ በተራሮቹ መካከል ያለው ሸለቆ እስከ አዜል ድረስ ይደርሳልና። በይሁዳ ንጉሥ በዖዝያ ዘመን ከተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ የተነሳ+ ሸሽታችሁ እንደነበረ ሁሉ አሁንም ትሸሻላችሁ። አምላኬ ይሖዋም ይመጣል፤ ቅዱሳኑም ሁሉ ከእሱ ጋር ይሆናሉ።+

6 “በዚያ ቀን ደማቅ ብርሃን አይኖርም፤+ ነገሮች ሁሉ ባሉበት ይረጋሉ።* 7 ያም ቀን የይሖዋ ቀን ተብሎ የሚታወቅ ልዩ ቀን ይሆናል።+ ቀንም ሆነ ሌሊት አይሆንም፤ በመሸም ጊዜ ብርሃን ይኖራል። 8 በዚያ ቀን ከኢየሩሳሌም ሕያው ውኃዎች+ ይወጣሉ፤+ ግማሾቹ በስተ ምሥራቅ ወዳለው ባሕር፣*+ ግማሾቹ ደግሞ በስተ ምዕራብ ወዳለው ባሕር* ይፈስሳሉ።+ ይህም በበጋና በክረምት ይሆናል። 9 ይሖዋም በመላው ምድር ላይ ይነግሣል።+ በዚያ ቀን ይሖዋ አንድ፣+ ስሙም አንድ ይሆናል።+

10 “ከጌባ+ አንስቶ ከኢየሩሳሌም በስተ ደቡብ እስካለችው እስከ ሪሞን+ ድረስ መላው ምድር እንደ አረባ+ ይሆናል፤ ኢየሩሳሌም በቀድሞ ስፍራዋ ላይ ትነሳለች፤ የሰዎችም መኖሪያ ትሆናለች፤+ ደግሞም ከቢንያም በር+ አንስቶ እስከ መጀመሪያው በርና እስከ ማዕዘን በር ድረስ ያለው ስፍራ ሁሉ እንዲሁም ከሃናንኤል ማማ+ አንስቶ እስከ ንጉሡ የወይን መጭመቂያዎች* ድረስ ያለው ስፍራ ሁሉ ሰው ይኖርበታል። 11 በከተማዋም ውስጥ ሰዎች ይኖራሉ፤ ከእንግዲህም ጥፋት እንዲደርስባት አትረገምም፤+ ደግሞም ኢየሩሳሌም ሰዎች ያለስጋት የሚኖሩባት ቦታ ትሆናለች።+

12 “ይሖዋ ኢየሩሳሌምን የሚወጉ ሕዝቦችን ሁሉ የሚቀስፍበት መቅሰፍት ይህ ነው፦+ በእግራቸው ቆመው እያለ ሥጋቸው ይበሰብሳል፤ ዓይኖቻቸውም በጉድጓዶቻቸው ውስጥ ይበሰብሳሉ፤ ምላሳቸውም በአፋቸው ውስጥ ይበሰብሳል።

13 “በዚያ ቀን ከይሖዋ ዘንድ የመጣ ሽብር በመካከላቸው ይሰራጫል፤ እያንዳንዱም ሰው የባልንጀራውን እጅ ይይዛል፤ እጁንም በባልንጀራው እጅ ላይ ያነሳል።*+ 14 ይሁዳም ራሱ በኢየሩሳሌም በሚደረገው ውጊያ ይካፈላል፤ በዙሪያዋም ያሉ ብሔራት ሁሉ ሀብት ይኸውም ወርቅ፣ ብርና ልብስ በብዛት ይሰበሰባል።+

15 “በየሰፈሩ ባሉት ፈረሶች፣ በቅሎዎች፣ ግመሎች፣ አህዮችና መንጎች ሁሉ ላይ ተመሳሳይ መቅሰፍት ይወርዳል።

16 “በኢየሩሳሌም ላይ ከተነሱት ብሔራት ሁሉ የሚተርፉት ሰዎች በሙሉ ለንጉሡ ለሠራዊት ጌታ ለይሖዋ ለመስገድና*+ የዳስ* በዓልን ለማክበር+ በየዓመቱ ይወጣሉ።+ 17 ይሁንና ከምድር ብሔራት መካከል ለንጉሡ ለሠራዊት ጌታ ለይሖዋ ለመስገድ ወደ ኢየሩሳሌም የማይወጡ ቢኖሩ ዝናብ አይዘንብላቸውም።+ 18 የግብፅ ሰዎች ባይወጡና ወደ ከተማዋ ባይገቡ ዝናብ አይዘንብላቸውም። እንዲያውም ይሖዋ የዳስ በዓልን ለማክበር ባልመጡት ብሔራት ላይ በሚያመጣቸው መቅሰፍቶች ይቀሰፋሉ። 19 ግብፅ ለፈጸመችው ኃጢአትና የዳስ በዓልን ለማክበር ያልወጡት ብሔራት ሁሉ ለሠሩት ኃጢአት ይህ ቅጣት ይደርስባቸዋል።

20 “በዚያ ቀን በፈረሶቹ ቃጭል ላይ ‘ቅድስና የይሖዋ ነው!’ ተብሎ ይጻፋል።+ በይሖዋ ቤት ያሉት ድስቶች+ በመሠዊያው ፊት እንዳሉት ሳህኖች+ ይሆናሉ። 21 በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ያሉ ድስቶች በሙሉ ቅዱስና ለሠራዊት ጌታ ለይሖዋ የተወሰኑ ይሆናሉ፤ መሥዋዕት የሚያቀርቡትም ሁሉ ገብተው የተወሰኑትን ድስቶች ለመቀቀያ ይጠቀሙባቸዋል። በዚያ ቀን በሠራዊት ጌታ በይሖዋ ቤት ዳግመኛ ከነአናዊ* አይገኝም።”+

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ