የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ዘዳግም 4:6
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 6 እነዚህንም በጥንቃቄ ጠብቋቸው፤+ ፈጽሟቸውም፤ እንዲህ ብታደርጉ ስለ እነዚህ ሥርዓቶች ሁሉ በሚሰሙ ሕዝቦች ፊት እንደ ጥበበኞችና+ እንደ አስተዋዮች+ ትቆጠራላችሁ፤ እነሱም ‘ይህ ታላቅ ብሔር በእርግጥም ጥበበኛና አስተዋይ ሕዝብ ነው’+ ይላሉ።

  • ኢያሱ 1:7, 8
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 7 “ብቻ አንተ ደፋርና ብርቱ ሁን፤ አገልጋዬ ሙሴ ያዘዘህን ሕግ በሙሉ በጥንቃቄ ፈጽም። በምትሄድበት በየትኛውም ቦታ ማንኛውንም ነገር በጥበብ ማከናወን እንድትችል+ ከዚህ ሕግ ወደ ቀኝም ሆነ ወደ ግራ ዞር አትበል።+ 8 ይህ የሕግ መጽሐፍ ከአፍህ አይለይ፤+ በውስጡ የተጻፈውንም በጥንቃቄ መፈጸም እንድትችል ቀንም ሆነ ሌሊት በለሆሳስ አንብበው፤*+ እንዲህ ካደረግክ መንገድህ ይቃናልሃል፤ እንዲሁም ማንኛውንም ነገር በጥበብ ማከናወን ትችላለህ።+

  • 1 ነገሥት 2:3
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 3 በሙሴ ሕግ ላይ በተጻፈው መሠረት በመንገዶቹ በመሄድ እንዲሁም ደንቦቹን፣ ትእዛዛቱን፣ ፍርዶቹንና ማሳሰቢያዎቹን በመጠበቅ ለአምላክህ ለይሖዋ ያለብህን ግዴታ ፈጽም፤+ ይህን ካደረግክ የምታከናውነው ሁሉ ይሳካልሃል፤ በምትሄድበትም ሁሉ ይቃናልሃል።

  • መዝሙር 119:100
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 100 መመሪያዎችህን ስለማከብር፣

      ከሽማግሌዎች ይበልጥ በማስተዋል እመላለሳለሁ።

  • 2 ጢሞቴዎስ 3:14, 15
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 14 አንተ ግን በተማርካቸውና አምነህ በተቀበልካቸው ነገሮች ጸንተህ ኑር፤+ ምክንያቱም እነዚህን ነገሮች እነማን እንዳስተማሩህ ታውቃለህ፤ 15 እንዲሁም በክርስቶስ ኢየሱስ በማመን ለመዳን የሚያበቃ ጥበብ እንድታገኝ የሚያስችሉህን ቅዱሳን መጻሕፍት+ ከጨቅላነትህ+ ጀምሮ አውቀሃል።+

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ