መዝሙር 41:4 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 4 እኔም “ይሖዋ ሆይ፣ ሞገስ አሳየኝ።+ በአንተ ላይ ኃጢአት ሠርቻለሁና+ ፈውሰኝ”*+ አልኩ። መዝሙር 103:2, 3 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 2 ይሖዋን ላወድስ፤*ያደረጋቸውን ነገሮች ሁሉ ፈጽሞ አልርሳ።+ 3 እሱ በደልሽን ሁሉ ይቅር ይላል፤+ሕመምሽንም ሁሉ ይፈውሳል፤+