መዝሙር
ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ። የዳዊት ማህሌት።
41 ለተቸገረ ሰው የሚያስብ ደስተኛ ነው፤+
በመከራ ቀን ይሖዋ ይታደገዋል።
2 ይሖዋ ይጠብቀዋል፤ በሕይወትም ያኖረዋል።
3 ታሞ በአልጋ ላይ ተኝቶ ሳለ ይሖዋ ይደግፈዋል፤+
በታመመበት ወቅት መኝታውን ሙሉ በሙሉ ትቀይርለታለህ።
4 እኔም “ይሖዋ ሆይ፣ ሞገስ አሳየኝ።+
በአንተ ላይ ኃጢአት ሠርቻለሁና+ ፈውሰኝ”*+ አልኩ።
5 ጠላቶቼ ግን “የሚሞተውና ስሙ ከናካቴው የሚረሳው መቼ ነው?” እያሉ
ስለ እኔ ክፉ ወሬ ያወራሉ።
6 ከእነሱ አንዱ እኔን ለማየት ቢመጣ ልቡ ውሸት ይናገራል።
እኔን የሚጎዳ ወሬ ይቃርማል፤
ከዚያም ወደ ውጭ ወጥቶ በየቦታው ያወራዋል።
7 የሚጠሉኝ ሁሉ እርስ በርስ ይንሾካሾካሉ፤
በእኔ ላይ ክፉ ነገር ይሸርባሉ፤
8 “ክፉ ነገር ደርሶበታል፤
ከእንግዲህ ከወደቀበት አይነሳም” ይላሉ።+
10 ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ግን ብድራታቸውን እከፍል ዘንድ
ሞገስ አሳየኝ፤ ደግሞም አንሳኝ።
11 ጠላቴ በእኔ ላይ በድል አድራጊነት እልል ሳይል ሲቀር፣
አንተ በእኔ ደስ እንደተሰኘህ በዚህ አውቃለሁ።+
13 የእስራኤል አምላክ ይሖዋ
ከዘላለም እስከ ዘላለም ይወደስ።+
አሜን፣ አሜን።