-
ማርቆስ 6:17-20አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
17 ሄሮድስ የወንድሙ የፊልጶስ ሚስት በሆነችው በሄሮድያዳ ምክንያት ሰዎች ልኮ ዮሐንስን በማስያዝ በሰንሰለት አስሮ ወህኒ አስገብቶት ነበር፤ ይህም የሆነው ሄሮድስ እሷን አግብቶ ስለነበር ነው።+ 18 ዮሐንስ ሄሮድስን “የወንድምህን ሚስት እንድታገባ ሕግ አይፈቅድልህም” ይለው ነበር።+ 19 በመሆኑም ሄሮድያዳ በእሱ ላይ ቂም ይዛ ልትገድለው ትፈልግ ነበር፤ ሆኖም ይህን ማድረግ አልቻለችም። 20 ሄሮድስ፣ ዮሐንስ ጻድቅና ቅዱስ ሰው+ መሆኑን ስለሚያውቅ ይፈራውና ጉዳት እንዳያገኘው ይጠብቀው ነበር። ዮሐንስ የሚናገረውን ሲሰማ ምን እንደሚያደርገው ግራ ይገባው የነበረ ቢሆንም በደስታ ያዳምጠው ነበር።
-