መዝሙር
ዳዊት በአቢሜሌክ* ፊት አእምሮውን የሳተ መስሎ በመቅረቡ+ አባሮ ባስወጣው ጊዜ የዘመረው መዝሙር።
א [አሌፍ]
34 ይሖዋን ሁልጊዜ አወድሰዋለሁ፤
ውዳሴው ምንጊዜም ከአፌ አይለይም።
ב [ቤት]
ג [ጊሜል]
3 ይሖዋን ከእኔ ጋር አወድሱት፤+
በኅብረት ስሙን ከፍ ከፍ እናድርግ።
ד [ዳሌት]
4 ይሖዋን ጠየቅኩት፤ እሱም መለሰልኝ።+
ከምፈራው ነገር ሁሉ ታደገኝ።+
ה [ሄ]
5 እሱን ተስፋ ያደረጉ በደስታ ፈኩ፤
ፊታቸው ፈጽሞ ለኀፍረት አይዳረግም።
ז [ዛየን]
6 ይህ ችግረኛ ተጣራ፤ ይሖዋም ሰማው።
ከጭንቀቱ ሁሉ ገላገለው።+
ח [ኼት]
ט [ቴት]
8 ይሖዋ ጥሩ መሆኑን ቅመሱ፤ እዩም፤+
እሱን መጠጊያ የሚያደርግ ሰው ደስተኛ ነው።
י [ዮድ]
9 ቅዱሳን አገልጋዮቹ ሁሉ፣ ይሖዋን ፍሩ፤
እሱን የሚፈሩ የሚያጡት ነገር የለምና።+
כ [ካፍ]
10 ብርቱ ደቦል አንበሶች እንኳ የሚበሉት አጥተው ይራባሉ፤
ይሖዋን የሚሹ ግን መልካም ነገር አይጎድልባቸውም።+
ל [ላሜድ]
11 ልጆቼ ሆይ፣ ኑ፣ አዳምጡኝ፤
ይሖዋን መፍራት አስተምራችኋለሁ።+
מ [ሜም]
12 ከእናንተ መካከል በሕይወት የሚደሰት፣
ብዙ መልካም ዘመን ማየት የሚወድስ ማን ነው?+
נ [ኑን]
ס [ሳሜኽ]
ע [አይን]
פ [ፔ]
16 ሆኖም የክፉዎችን መታሰቢያ ሁሉ ከምድር ለማጥፋት፣
የይሖዋ ፊት በእነሱ ላይ ነው።+
צ [ጻዴ]
ק [ኮፍ]
ר [ረሽ]
ש [ሺን]
20 አጥንቶቹን ሁሉ ይጠብቃል፤
አንዳቸውም ቢሆኑ አልተሰበሩም።+
ת [ታው]
21 ክፉ ሰው በአደጋ ይሞታል፤
ጻድቁን የሚጠሉ ሰዎችም ይፈረድባቸዋል።