የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • መዝሙር 35
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

መዝሙር የመጽሐፉ ይዘት

      • ዳዊት፣ አምላክ ከጠላት እጅ እንዲታደገው ያቀረበው ጸሎት

        • ጠላቶች ይባረራሉ (5)

        • በብዙ ሕዝብ መካከል አምላክን ማወደስ (18)

        • ያለ ምክንያት ጠሉኝ (19)

መዝሙር 35:1

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ሳሙ 24:15
  • +መዝ 3:7

መዝሙር 35:2

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    አብዛኛውን ጊዜ ቀስተኞች የሚይዙት ትንሽ ጋሻ።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 15:3
  • +ኢሳ 42:13

መዝሙር 35:3

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “በሁለቱም በኩል ስለት ያለው መጥረቢያ፤ የውጊያ መጥረቢያ።”

  • *

    ወይም “ነፍሴንም ‘የማድንሽ እኔ ነኝ’ በላት።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ሳሙ 23:26
  • +ኢሳ 12:2

መዝሙር 35:4

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ነፍሴን።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 17:18

መዝሙር 35:5

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 14:19, 20፤ ኢሳ 37:36

መዝሙር 35:7

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ለነፍሴ ጉድጓድ ቆፍረውላታል።”

መዝሙር 35:8

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 57:6፤ 141:10

መዝሙር 35:9

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ነፍሴ ግን በይሖዋ ሐሴት ታደርጋለች።”

መዝሙር 35:10

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 18:17፤ 40:17፤ ምሳሌ 22:22, 23

መዝሙር 35:11

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 27:12፤ ማቴ 26:59

መዝሙር 35:12

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ነፍሴን ሐዘን ላይ ጣሏት።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ሳሙ 19:4, 5፤ 20:33፤ ኤር 18:20

መዝሙር 35:13

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ነፍሴን።”

  • *

    ወይም “ወደ ጉያዬ በተመለሰ ጊዜ።”

መዝሙር 35:16

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    “ፈሪሃ አምላክ የሌላቸው ሰዎች ለምግብ ብለው ያፌዛሉ” ማለትም ሊሆን ይችላል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 37:12

መዝሙር 35:17

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ነፍሴን ታደግ።”

  • *

    ቃል በቃል “አንድ ያለችኝን።” ነፍሱን ወይም ሕይወቱን ያመለክታል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዕን 1:13
  • +መዝ 142:6
  • +መዝ 22:20፤ 57:4

መዝሙር 35:18

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 22:22

መዝሙር 35:19

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 69:4፤ ዮሐ 15:24, 25
  • +ምሳሌ 6:12, 13

መዝሙር 35:20

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 31:13፤ ኤር 11:19፤ ማቴ 26:4

መዝሙር 35:22

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 28:1
  • +መዝ 10:1፤ 71:12

መዝሙር 35:24

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 26:1፤ 96:13

መዝሙር 35:25

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “እሰይ! ነፍሳችን ደስ አላት።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 41:1, 2

መዝሙር 35:27

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 84:11፤ 149:4

መዝሙር 35:28

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ምላሴ በጽድቅህ ላይ ያሰላስላል።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 51:14
  • +መዝ 71:24

ተዛማጅ ሐሳብ

መዝ. 35:11ሳሙ 24:15
መዝ. 35:1መዝ 3:7
መዝ. 35:2ዘፀ 15:3
መዝ. 35:2ኢሳ 42:13
መዝ. 35:31ሳሙ 23:26
መዝ. 35:3ኢሳ 12:2
መዝ. 35:4ኤር 17:18
መዝ. 35:5ዘፀ 14:19, 20፤ ኢሳ 37:36
መዝ. 35:8መዝ 57:6፤ 141:10
መዝ. 35:10መዝ 18:17፤ 40:17፤ ምሳሌ 22:22, 23
መዝ. 35:11መዝ 27:12፤ ማቴ 26:59
መዝ. 35:121ሳሙ 19:4, 5፤ 20:33፤ ኤር 18:20
መዝ. 35:16መዝ 37:12
መዝ. 35:17ዕን 1:13
መዝ. 35:17መዝ 142:6
መዝ. 35:17መዝ 22:20፤ 57:4
መዝ. 35:18መዝ 22:22
መዝ. 35:19መዝ 69:4፤ ዮሐ 15:24, 25
መዝ. 35:19ምሳሌ 6:12, 13
መዝ. 35:20መዝ 31:13፤ ኤር 11:19፤ ማቴ 26:4
መዝ. 35:22መዝ 28:1
መዝ. 35:22መዝ 10:1፤ 71:12
መዝ. 35:24መዝ 26:1፤ 96:13
መዝ. 35:25መዝ 41:1, 2
መዝ. 35:27መዝ 84:11፤ 149:4
መዝ. 35:28መዝ 51:14
መዝ. 35:28መዝ 71:24
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
  • 23
  • 24
  • 25
  • 26
  • 27
  • 28
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
መዝሙር 35:1-28

መዝሙር

የዳዊት መዝሙር።

35 ይሖዋ ሆይ፣ ባላጋራዎቼን በመቃወም ተሟገትልኝ፤+

የሚዋጉኝን ተዋጋቸው።+

 2 ትንሹንና* ትልቁን ጋሻህን ያዝ፤+

ለእኔ ለመከላከልም ተነስ።+

 3 በሚያሳድዱኝ ላይ ጦርና መጥረቢያ* አንሳ።+

“የማድንህ እኔ ነኝ” በለኝ።*+

 4 ሕይወቴን* የሚሹ ይፈሩ፤ ይዋረዱም።+

እኔን ለማጥፋት የሚያሴሩ ተዋርደው ያፈግፍጉ።

 5 በነፋስ ፊት እንዳለ ገለባ ይሁኑ፤

የይሖዋ መልአክም ያባርራቸው።+

 6 የይሖዋ መልአክ ሲያሳድዳቸው

መንገዳቸው በጨለማ የተዋጠና የሚያዳልጥ ይሁን።

 7 ያላንዳች ምክንያት እኔን ለማጥመድ በስውር መረብ ዘርግተዋልና፤

ያላንዳች ምክንያት ጉድጓድ ቆፍረውልኛል።*

 8 ሳያስቡት ጥፋት ይምጣባቸው፤

በስውር ያስቀመጡት መረብም እነሱኑ ይያዛቸው፤

እዚያም ውስጥ ወድቀው ይጥፉ።+

 9 እኔ ግን በይሖዋ ሐሴት አደርጋለሁ፤*

በማዳን ሥራውም እጅግ ደስ ይለኛል።

10 አጥንቶቼ ሁሉ እንዲህ ይላሉ፦

“ይሖዋ ሆይ፣ እንደ አንተ ያለ ማን ነው?

ምስኪኑን ብርቱ ከሆኑት፣

ምስኪኑንና ድሃውን ከሚዘርፏቸው ሰዎች ትታደጋለህ።”+

11 ክፉ ምሥክሮች ቀረቡ፤+

ምንም ስለማላውቀው ነገር ጠየቁኝ።

12 ለመልካም ነገር ክፉ መለሱልኝ፤+

ደግሞም ሐዘን ላይ ጣሉኝ።*

13 እኔ ግን እነሱ በታመሙ ጊዜ ማቅ ለበስኩ፤

ራሴን* በጾም አጎሳቆልኩ፤

ጸሎቴም መልስ ሳያገኝ በተመለሰ ጊዜ፣*

14 ለጓደኛዬ ወይም ለወንድሜ እንደማደርገው እየተንቆራጠጥኩ አለቀስኩ፤

እናቱ ሞታበት እንደሚያለቅስ ሰው አንገቴን በሐዘን ደፋሁ።

15 እኔ ስደናቀፍ ግን እነሱ ደስ ብሏቸው ተሰበሰቡ፤

አድብተው እኔን ለመምታት ተሰበሰቡ፤

ዘነጣጠሉኝ፤ በነገር መጎንተላቸውንም አልተዉም።

16 ፈሪሃ አምላክ የሌላቸው ሰዎች በንቀት ያፌዙብኛል፤*

በእኔ ላይ ጥርሳቸውን ያፋጫሉ።+

17 ይሖዋ ሆይ፣ ዝም ብለህ የምታየው እስከ መቼ ነው?+

ከሚሰነዝሩብኝ ጥቃት ታደገኝ፤*+

ውድ ሕይወቴን* ከደቦል አንበሶች አድናት።+

18 ያን ጊዜ በታላቅ ጉባኤ መካከል አመሰግንሃለሁ፤+

በብዙ ሕዝብ መካከል አወድስሃለሁ።

19 ያላንዳች ምክንያት ጠላቶቼ የሆኑ እኔን አይተው እንዲፈነድቁ፣

ያለምክንያት የሚጠሉኝ+ በተንኮል እንዲጠቃቀሱብኝ አትፍቀድ።+

20 የሰላም ቃል ከአፋቸው አይወጣምና፤

ከዚህ ይልቅ በምድሪቱ በሰላም በሚኖሩት ላይ ተንኮል ይሸርባሉ።+

21 እኔን ለመወንጀል አፋቸውን ይከፍታሉ፤

“እሰይ! እሰይ! ዓይናችን ይህን አየ” ይላሉ።

22 ይሖዋ ሆይ፣ ይህን ተመልክተሃል። ዝም አትበል።+

ይሖዋ ሆይ፣ ከእኔ አትራቅ።+

23 ለእኔ ጥብቅና ለመቆም ንቃ፤ ተነሳም፤

ይሖዋ አምላኬ ሆይ፣ ተሟገትልኝ።

24 ይሖዋ አምላኬ ሆይ፣ እንደ ጽድቅህ ፍረድልኝ፤+

በእኔ እንዲፈነድቁ አትፍቀድ።

25 በልባቸው “እሰይ! የተመኘነውን አገኘን”* አይበሉ።

ደግሞም “ዋጥነው” አይበሉ።+

26 እኔ ላይ በደረሰው ጉዳት የሚፈነድቁ ሁሉ

ይፈሩ፣ ይዋረዱም።

በእኔ ላይ ራሳቸውን ከፍ ከፍ የሚያደርጉ ኀፍረትና ውርደት ይከናነቡ።

27 በእኔ ጽድቅ የሚደሰቱ ግን እልል ይበሉ፤

ሁልጊዜም እንዲህ ይበሉ፦

“በአገልጋዩ ሰላም የሚደሰተው ይሖዋ ከፍ ከፍ ይበል።”+

28 በዚህ ጊዜ ምላሴ ስለ ጽድቅህ ይናገራል፤*+

ቀኑን ሙሉም ያወድስሃል።+

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ