የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • መክብብ 12
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

መክብብ የመጽሐፉ ይዘት

      • እርጅና ሳይመጣ ፈጣሪን አስብ (1-8)

      • የሰብሳቢው የመደምደሚያ ቃላት (9-14)

        • “የጥበበኞች ቃላት እንደ በሬ መውጊያ ናቸው” (11)

        • “እውነተኛውን አምላክ ፍራ” (13)

መክብብ 12:1

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “የመከራ ቀናት።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 90:10
  • +መዝ 71:17፤ 148:7, 12፤ ሉቃስ 2:48, 49፤ 2ጢሞ 3:15

መክብብ 12:2

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    “ደመናት ዶፍ ይዘው” ማለትም ሊሆን ይችላል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ሳሙ 4:15

መክብብ 12:3

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ዘበኞች።”

  • *

    ወይም “ይብረከረካሉ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 48:10

መክብብ 12:4

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ሳሙ 19:34, 35

መክብብ 12:5

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    እዚህ ላይ የተሠራበት ቃል የምግብን ፍላጎት ለመቀስቀስ የሚያገለግልን ከእንጆሪ ጋር የሚመሳሰል ተክል ያመለክታል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ምሳሌ 16:31
  • +ኢዮብ 30:23፤ መክ 9:10
  • +ዘፍ 50:7, 10

መክብብ 12:6

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “መዘውር።”

መክብብ 12:7

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “የሕይወት ኃይልም።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 3:19፤ መዝ 146:4
  • +ዘፍ 2:7፤ ኢዮብ 27:3፤ 34:14, 15፤ መዝ 104:29፤ ኢሳ 42:5

መክብብ 12:8

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ዋጋ ቢስ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 8:1
  • +መክ 1:2, 14

መክብብ 12:9

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “በሥርዓት ማዘጋጀት።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 10:1, 3, 6, 8
  • +1ነገ 4:29, 32፤ ምሳሌ 1:1

መክብብ 12:10

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ምሳሌ 16:24፤ 25:11

መክብብ 12:11

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሥራ 2:37፤ ዕብ 4:12

መክብብ 12:12

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መክ 1:18

መክብብ 12:13

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢዮብ 28:28፤ መዝ 111:10፤ ምሳሌ 1:7
  • +1ዮሐ 5:3
  • +ዘዳ 6:1, 2፤ 10:12

መክብብ 12:14

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 62:12፤ መክ 11:9፤ ማቴ 12:36, 37፤ ሥራ 17:31፤ 2ቆሮ 5:10፤ 1ጢሞ 5:24

ተዛማጅ ሐሳብ

መክ. 12:1መዝ 90:10
መክ. 12:1መዝ 71:17፤ 148:7, 12፤ ሉቃስ 2:48, 49፤ 2ጢሞ 3:15
መክ. 12:21ሳሙ 4:15
መክ. 12:3ዘፍ 48:10
መክ. 12:42ሳሙ 19:34, 35
መክ. 12:5ምሳሌ 16:31
መክ. 12:5ኢዮብ 30:23፤ መክ 9:10
መክ. 12:5ዘፍ 50:7, 10
መክ. 12:7ዘፍ 3:19፤ መዝ 146:4
መክ. 12:7ዘፍ 2:7፤ ኢዮብ 27:3፤ 34:14, 15፤ መዝ 104:29፤ ኢሳ 42:5
መክ. 12:81ነገ 8:1
መክ. 12:8መክ 1:2, 14
መክ. 12:91ነገ 10:1, 3, 6, 8
መክ. 12:91ነገ 4:29, 32፤ ምሳሌ 1:1
መክ. 12:10ምሳሌ 16:24፤ 25:11
መክ. 12:11ሥራ 2:37፤ ዕብ 4:12
መክ. 12:12መክ 1:18
መክ. 12:13ኢዮብ 28:28፤ መዝ 111:10፤ ምሳሌ 1:7
መክ. 12:131ዮሐ 5:3
መክ. 12:13ዘዳ 6:1, 2፤ 10:12
መክ. 12:14መዝ 62:12፤ መክ 11:9፤ ማቴ 12:36, 37፤ ሥራ 17:31፤ 2ቆሮ 5:10፤ 1ጢሞ 5:24
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
መክብብ 12:1-14

መክብብ

12 እንግዲያው አስጨናቂ የሆኑት ዘመናት*+ ከመምጣታቸው እንዲሁም “ደስ አያሰኙኝም” የምትላቸው ዓመታት ከመድረሳቸው በፊት በወጣትነትህ ጊዜ ታላቁን ፈጣሪህን አስብ፤+ 2 ፀሐይ፣ ብርሃን፣ ጨረቃና ከዋክብት ከመጨለማቸው በፊት+ እንዲሁም ዶፍ ከጣለ በኋላ ደመናት ተመልሰው* ከመምጣታቸው በፊት ፈጣሪህን አስብ፤ 3 በዚያን ጊዜ ቤት ጠባቂዎች* ይንቀጠቀጣሉ፤* ጠንካራ የነበሩ ሰዎች ይጎብጣሉ፤ የሚፈጩ ሴቶች ጥቂት በመሆናቸው ሥራቸውን ያቆማሉ፤ በመስኮት የሚያዩ ወይዛዝርትም ይጨልምባቸዋል፤+ 4 ወደ መንገድ የሚያወጡ በሮች ይዘጋሉ፤ የወፍጮ ድምፅ ይቀንሳል፤ ሰውም የወፍ ድምፅ ይቀሰቅሰዋል፤ ሴቶች ልጆችም ሁሉ ዝግ ባለ ድምፅ ይዘምራሉ።+ 5 በተጨማሪም ሰው ከፍታ ያስፈራዋል፤ በመንገድ ሲሄድም ይሸበራል። የአልሞንድ ዛፍ ያብባል፤+ ፌንጣም እየተጎተተ ይሄዳል፤ የምግብ ፍላጎት* ይጠፋል፤ ምክንያቱም ሰው ለረጅም ጊዜ ወደሚኖርበት ቤት ይሄዳል፤+ አልቃሾችም በጎዳና ይዞራሉ፤+ 6 የብር ገመድ ሳይበጠስ፣ የወርቅ ሳህን ሳይሰበር፣ እንስራ በምንጭ አጠገብ ሳይከሰከስ፣ ከጉድጓድ ውኃ ለማውጣት የሚያገለግለው መንኮራኩር* ሳይሰበር ፈጣሪህን አስብ። 7 አፈር ቀድሞ ወደነበረበት መሬት ይመለሳል፤+ መንፈስም* ወደ ሰጪው፣ ወደ እውነተኛው አምላክ ይመለሳል።+

8 ሰብሳቢው+ “የከንቱ ከንቱ* ነው! ሁሉም ነገር ከንቱ ነው!” ይላል።+

9 ሰብሳቢው ጥበበኛ ከመሆኑም በተጨማሪ ለሕዝቡ የሚያውቀውን ነገር ሁልጊዜ ያስተምር ነበር፤+ ብዙ ምሳሌዎችንም ማጠናቀር* ይችል ዘንድ አሰላሰለ እንዲሁም ሰፊ ምርምር አደረገ።+ 10 ሰብሳቢው ደስ የሚያሰኙ ቃላትን+ ለማግኘትና የእውነትን ቃል በትክክል ለመመዝገብ ጥረት አደረገ።

11 የጥበበኞች ቃላት እንደ በሬ መውጊያ ናቸው፤+ የሰበሰቧቸው አባባሎችም በሚገባ እንደተቸነከሩ ምስማሮች ናቸው፤ እነዚህ ቃላት ከአንድ እረኛ የተሰጡ ናቸው። 12 ልጄ ሆይ፣ ከዚህም ሌላ ይህን ማስጠንቀቂያ ልብ በል፦ ብዙ መጻሕፍት መጻፍ ማብቂያ የለውም፤ በእነሱ ዙሪያ ምርምር ማብዛትም ሰውነትን ያደክማል።+

13 ሁሉ ነገር ከተሰማ በኋላ መደምደሚያው ይህ ነው፦ እውነተኛውን አምላክ ፍራ፤+ ትእዛዛቱንም ጠብቅ፤+ ይህ የሰው አጠቃላይ ግዴታ ነውና።+ 14 እውነተኛው አምላክ እያንዳንዱን የተሰወረ ነገር ጨምሮ ማንኛውንም ሥራ፣ ጥሩም ይሁን መጥፎ ወደ ፍርድ ያመጣዋልና።+

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ