የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ዘኁልቁ 20
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

ዘኁልቁ የመጽሐፉ ይዘት

      • ሚርያም በቃዴስ ሞታ ተቀበረች (1)

      • ሙሴ ከዓለቱ ውኃ አፈለቀ፤ እንዲሁም ኃጢአት ሠራ (2-13)

      • ኤዶማውያን፣ እስራኤላውያን ክልላቸውን አቋርጠው እንዳያልፉ ከለከሉ (14-21)

      • አሮን ሞተ (22-29)

ዘኁልቁ 20:1

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘኁ 13:26፤ 20:22፤ 33:36፤ ዘዳ 2:14
  • +ዘፀ 15:20፤ ዘኁ 26:59፤ ሚክ 6:4

ዘኁልቁ 20:2

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 17:1

ዘኁልቁ 20:3

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 17:2

ዘኁልቁ 20:4

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 14:11፤ 17:3፤ ዘኁ 16:13, 14፤ 21:5

ዘኁልቁ 20:5

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 8:14, 15
  • +ዘዳ 8:7, 8

ዘኁልቁ 20:6

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 16:10፤ ዘኁ 14:10

ዘኁልቁ 20:8

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 17:5, 6፤ መዝ 78:15፤ 105:41፤ 114:8፤ ኢሳ 48:21

ዘኁልቁ 20:9

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 7:12, 19፤ ዘኁ 17:10

ዘኁልቁ 20:10

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 106:32, 33

ዘኁልቁ 20:11

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ቆሮ 10:1, 4

ዘኁልቁ 20:12

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘኁ 27:12-14፤ ዘዳ 1:37፤ 3:26፤ 32:51, 52፤ 34:4፤ ኢያሱ 1:2

ዘኁልቁ 20:13

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    “ጠብ” የሚል ትርጉም አለው።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 106:32, 33

ዘኁልቁ 20:14

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መሳ 11:17
  • +ዘፍ 36:8፤ ዘዳ 2:4፤ 23:7

ዘኁልቁ 20:15

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ቀናት።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 46:6
  • +ዘፍ 15:13፤ ዘፀ 12:40
  • +ዘፀ 1:11, 14

ዘኁልቁ 20:16

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 2:23፤ 3:7
  • +ዘፀ 14:19፤ 23:20፤ 33:2

ዘኁልቁ 20:17

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘኁ 21:21, 22፤ ዘዳ 2:26, 27

ዘኁልቁ 20:19

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 2:5, 6
  • +ዘዳ 2:26, 28

ዘኁልቁ 20:20

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “እጅ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መሳ 11:17

ዘኁልቁ 20:21

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 2:8፤ መሳ 11:18

ዘኁልቁ 20:22

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘኁ 21:4፤ 33:37

ዘኁልቁ 20:24

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ይህ ሞትን የሚያመለክት ቅኔያዊ አነጋገር ነው።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘኁ 33:38፤ ዘዳ 32:50
  • +ዘኁ 20:12፤ ዘዳ 32:51, 52

ዘኁልቁ 20:26

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “በዚያ ይሰበሰባል፣ ይሞታልም።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 28:2፤ 29:29
  • +ዘፀ 6:23፤ ዘኁ 4:16

ዘኁልቁ 20:28

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘኁ 33:39፤ ዘዳ 10:6፤ 32:50

ዘኁልቁ 20:29

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 34:8

ተዛማጅ ሐሳብ

ዘኁ. 20:1ዘኁ 13:26፤ 20:22፤ 33:36፤ ዘዳ 2:14
ዘኁ. 20:1ዘፀ 15:20፤ ዘኁ 26:59፤ ሚክ 6:4
ዘኁ. 20:2ዘፀ 17:1
ዘኁ. 20:3ዘፀ 17:2
ዘኁ. 20:4ዘፀ 14:11፤ 17:3፤ ዘኁ 16:13, 14፤ 21:5
ዘኁ. 20:5ዘዳ 8:14, 15
ዘኁ. 20:5ዘዳ 8:7, 8
ዘኁ. 20:6ዘፀ 16:10፤ ዘኁ 14:10
ዘኁ. 20:8ዘፀ 17:5, 6፤ መዝ 78:15፤ 105:41፤ 114:8፤ ኢሳ 48:21
ዘኁ. 20:9ዘፀ 7:12, 19፤ ዘኁ 17:10
ዘኁ. 20:10መዝ 106:32, 33
ዘኁ. 20:111ቆሮ 10:1, 4
ዘኁ. 20:12ዘኁ 27:12-14፤ ዘዳ 1:37፤ 3:26፤ 32:51, 52፤ 34:4፤ ኢያሱ 1:2
ዘኁ. 20:13መዝ 106:32, 33
ዘኁ. 20:14መሳ 11:17
ዘኁ. 20:14ዘፍ 36:8፤ ዘዳ 2:4፤ 23:7
ዘኁ. 20:15ዘፍ 46:6
ዘኁ. 20:15ዘፍ 15:13፤ ዘፀ 12:40
ዘኁ. 20:15ዘፀ 1:11, 14
ዘኁ. 20:16ዘፀ 2:23፤ 3:7
ዘኁ. 20:16ዘፀ 14:19፤ 23:20፤ 33:2
ዘኁ. 20:17ዘኁ 21:21, 22፤ ዘዳ 2:26, 27
ዘኁ. 20:19ዘዳ 2:5, 6
ዘኁ. 20:19ዘዳ 2:26, 28
ዘኁ. 20:20መሳ 11:17
ዘኁ. 20:21ዘዳ 2:8፤ መሳ 11:18
ዘኁ. 20:22ዘኁ 21:4፤ 33:37
ዘኁ. 20:24ዘኁ 33:38፤ ዘዳ 32:50
ዘኁ. 20:24ዘኁ 20:12፤ ዘዳ 32:51, 52
ዘኁ. 20:26ዘፀ 28:2፤ 29:29
ዘኁ. 20:26ዘፀ 6:23፤ ዘኁ 4:16
ዘኁ. 20:28ዘኁ 33:39፤ ዘዳ 10:6፤ 32:50
ዘኁ. 20:29ዘዳ 34:8
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
  • 23
  • 24
  • 25
  • 26
  • 27
  • 28
  • 29
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
ዘኁልቁ 20:1-29

ዘኁልቁ

20 በመጀመሪያው ወር መላው የእስራኤል ማኅበረሰብ ወደ ጺን ምድረ በዳ መጣ፤ ሕዝቡም በቃዴስ+ ተቀመጠ። ሚርያም+ የሞተችውም ሆነ የተቀበረችው በዚያ ነበር።

2 በዚያ ለማኅበረሰቡ የሚሆን ውኃ አልነበረም፤+ ሕዝቡም ሙሴንና አሮንን በመቃወም በእነሱ ላይ ተሰበሰበ። 3 ሕዝቡም እንዲህ በማለት ከሙሴ ጋር ተጣላ፦+ “ምነው ወንድሞቻችን በይሖዋ ፊት በሞቱ ጊዜ እኛም ሞተን ባረፍነው ኖሮ! 4 እኛም ሆንን ከብቶቻችን እዚህ እንድናልቅ የይሖዋን ጉባኤ ወደዚህ ምድረ በዳ ያመጣችሁት ለምንድን ነው?+ 5 ከግብፅ አውጥታችሁ ወደዚህ መጥፎ ቦታ እየመራችሁ ያመጣችሁን ለምንድን ነው?+ ይህ ቦታ እህልም ሆነ በለስ፣ የወይን ፍሬም ሆነ ሮማን የሌለበት ነው፤ የሚጠጣ ውኃም የለም።”+ 6 ከዚያም ሙሴና አሮን ከጉባኤው ፊት ተነስተው ወደ መገናኛ ድንኳኑ መግቢያ በመሄድ በግንባራቸው መሬት ላይ ተደፉ፤ የይሖዋም ክብር ተገለጠላቸው።+

7 ከዚያም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ 8 “በትሩን ውሰድ፤ አንተና ወንድምህ አሮንም ማኅበረሰቡን ሰብስቡ፤ ዓለቱም ውኃውን እንዲሰጥ በእነሱ ፊት ተናገሩት፤ አንተም ከዓለቱ ውኃ ታፈልቅላቸዋለህ፤ ማኅበረሰቡም ሆነ ከብቶቻቸው እንዲጠጡም ትሰጣቸዋለህ።”+

9 ሙሴም ልክ እንደታዘዘው በትሩን ከይሖዋ ፊት ወሰደ።+ 10 ከዚያም ሙሴና አሮን ጉባኤውን በዓለቱ ፊት ሰበሰቡ፤ እሱም “እናንተ ዓመፀኞች ስሙ! ከዚህ ዓለት ለእናንተ ውኃ ማፍለቅ አለብን?” አላቸው።+ 11 ሙሴም ይህን ካለ በኋላ እጁን አንስቶ ዓለቱን ሁለት ጊዜ በበትሩ መታው፤ ውኃውም ይንዶለዶል ጀመር፤ ማኅበረሰቡና ከብቶቻቸውም ጠጡ።+

12 በኋላም ይሖዋ ሙሴንና አሮንን እንዲህ አላቸው፦ “በእስራኤል ሕዝብ ፊት በእኔ ስላልታመናችሁና እኔን ስላልቀደሳችሁ ይህን ጉባኤ እኔ ወደምሰጠው ምድር ይዛችሁ አትገቡም።”+ 13 ይሖዋ በመካከላቸው ይቀደስ ዘንድ እስራኤላውያን ከእሱ ጋር የተጣሉባቸው የመሪባ*+ ውኃዎች እነዚህ ናቸው።

14 ከዚያም ሙሴ ለኤዶም ንጉሥ እንዲህ ብለው እንዲነግሩት ከቃዴስ መልእክተኞችን ላከ፦+ “ወንድምህ እስራኤል+ እንዲህ ይላል፦ ‘መቼም የደረሰብንን መከራ ሁሉ በሚገባ ታውቃለህ። 15 አባቶቻችን ወደ ግብፅ ወርደው ነበር፤+ እኛም በግብፅ ለብዙ ዓመታት* ኖርን፤+ ግብፃውያኑም በእኛም ሆነ በአባቶቻችን ላይ በደል ይፈጽሙብን ነበር።+ 16 በመጨረሻም ወደ ይሖዋ ጮኽን፤+ እሱም ጩኸታችንን ሰምቶ መልአክ በመላክ+ ከግብፅ አወጣን፤ ይኸው አሁን ድንበርህ ላይ ባለችው በቃዴስ ከተማ እንገኛለን። 17 እናም አሁን እባክህ በምድርህ እንለፍ። በየትኛውም እርሻ ወይም በየትኛውም የወይን ቦታ አቋርጠን አንሄድም፤ ከየትኛውም ጉድጓድ ውኃ አንጠጣም። ክልልህን አቋርጠን እስክናልፍ ድረስ ወደ ቀኝም ሆነ ወደ ግራ ዞር ሳንል በንጉሡ መንገድ እንሄዳለን።’”+

18 ኤዶም ግን “ክልላችንን አቋርጠህ ማለፍ አትችልም። እንዲህ ካደረግክ ወጥቼ በሰይፍ እገጥምሃለሁ” አለው። 19 እስራኤላውያንም መልሰው እንዲህ አሉት፦ “አውራ ጎዳናውን ይዘን እናቀናለን፤ እኛም ሆን ከብቶቻችን ከውኃህ ከጠጣን ዋጋውን እንከፍልሃለን።+ በእግራችን አልፈን ከመሄድ በስተቀር ሌላ ምንም ነገር አንፈልግም።”+ 20 እሱ ግን አሁንም “በዚህ ማለፍ አትችልም”+ ሲል መልስ ሰጠ። ከዚያም ኤዶም ብዙ ሕዝብና ኃያል ሠራዊት* ይዞ ሊገጥመው ወጣ። 21 በዚህ መንገድ ኤዶም እስራኤል በክልሉ እንዳያልፍ ከለከለ፤ ስለዚህ እስራኤል ከእሱ ተመለሰ።+

22 የእስራኤል ሕዝብ ይኸውም መላው ማኅበረሰብ ከቃዴስ ተነስቶ ወደ ሆር ተራራ+ መጣ። 23 ከዚያም ይሖዋ በኤዶም ምድር ወሰን ላይ ባለው በሆር ተራራ ሙሴንና አሮንን እንዲህ አላቸው፦ 24 “አሮን ወደ ወገኖቹ ይሰበሰባል።*+ ሁለታችሁም ከመሪባ ውኃ ጋር በተያያዘ በሰጠሁት ትእዛዝ ላይ ስላመፃችሁ ለእስራኤላውያን ወደምሰጣት ምድር አይገባም።+ 25 አሮንንና ልጁን አልዓዛርን ይዘህ ወደ ሆር ተራራ ውጣ። 26 የአሮንን ልብስ አውልቀህ+ ልጁን አልዓዛርን+ አልብሰው፤ አሮንም በዚያ ይሞታል።”*

27 በመሆኑም ሙሴ ልክ ይሖዋ እንዳዘዘው አደረገ፤ እነሱም መላው ማኅበረሰብ እያየ ወደ ሆር ተራራ ወጡ። 28 ሙሴም የአሮንን ልብስ አውልቆ ልጁን አልዓዛርን አለበሰው። ከዚያም አሮን እዚያው ተራራው አናት ላይ ሞተ።+ ሙሴና አልዓዛርም ከተራራው ወረዱ። 29 መላው ማኅበረሰብም አሮን መሞቱን አየ፤ በዚህ ጊዜ የእስራኤል ቤት በሙሉ ለአሮን 30 ቀን አለቀሰለት።+

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ