አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ ዘፀአት የመጽሐፉ ይዘት ዘፀአት የመጽሐፉ ይዘት 1 እስራኤላውያን በግብፅ እየበዙ ሄዱ (1-7) ፈርዖን እስራኤላውያንን ጨቆናቸው (8-14) ፈሪሃ አምላክ ያላቸው አዋላጆች ወንዶቹን ልጆች ሳይገድሏቸው ቀሩ (15-22) 2 ሙሴ ተወለደ (1-4) የፈርዖን ሴት ልጅ ሙሴን አሳደገችው (5-10) ሙሴ ወደ ምድያም ሸሸ፤ ሲፓራን አገባ (11-22) አምላክ የእስራኤላውያንን ጩኸት ሰማ (23-25) 3 ሙሴና የሚነደው ቁጥቋጦ (1-12) ይሖዋ የስሙን ትርጉም ገለጠ (13-15) ይሖዋ ለሙሴ የሰጠው ትእዛዝ (16-22) 4 ሙሴ ሦስት ተአምራት እንዲፈጽም ተነገረው (1-9) ሙሴ ብቁ እንዳልሆነ ተሰማው (10-17) ሙሴ ወደ ግብፅ ተመለሰ (18-26) ሙሴ በድጋሚ ከአሮን ጋር ተገናኘ (27-31) 5 ሙሴና አሮን ፈርዖን ፊት ቀረቡ (1-5) እስራኤላውያን የሚደርስባቸው ጭቆና እየባሰ ሄደ (6-18) እስራኤላውያን ሙሴንና አሮንን አማረሩ (19-23) 6 ነፃ እንደሚወጡ ዳግመኛ ተስፋ ተሰጣቸው (1-13) ይሖዋ ስሙን ሙሉ በሙሉ አልገለጠላቸውም ነበር (2, 3) የሙሴና የአሮን የዘር ሐረግ (14-27) ሙሴ በድጋሚ ፈርዖን ፊት ቀረበ (28-30) 7 ይሖዋ ሙሴን አበረታታው (1-7) የአሮን በትር ትልቅ እባብ ሆነ (8-13) የመጀመሪያው መቅሰፍት፦ ውኃው ወደ ደም ተለወጠ (14-25) 8 ሁለተኛው መቅሰፍት፦ እንቁራሪቶች (1-15) ሦስተኛው መቅሰፍት፦ ትንኝ (16-19) አራተኛው መቅሰፍት፦ ተናካሽ ዝንብ (20-32) መቅሰፍቱ ጎሸንን አልነካም (22, 23) 9 አምስተኛው መቅሰፍት፦ ከብቶቻቸው ሞቱ (1-7) ስድስተኛው መቅሰፍት፦ በሰዎችና በእንስሳት ላይ እባጭ ወጣ (8-12) ሰባተኛው መቅሰፍት፦ የበረዶ ውርጅብኝ (13-35) ፈርዖን የአምላክን ኃይል ያያል (16) የይሖዋ ስም ይታወጃል (16) 10 ስምንተኛው መቅሰፍት፦ አንበጦች (1-20) ዘጠነኛው መቅሰፍት፦ ድቅድቅ ጨለማ (21-29) 11 አሥረኛው መቅሰፍት እንደሚመጣ ተነገረ (1-10) እስራኤላውያን ከግብፃውያን ላይ ስጦታ እንዲጠይቁ ተነገራቸው (2) 12 የፋሲካ በዓል ተቋቋመ (1-28) ደሙን በበሩ መቃንና ጉበን ላይ እንዲረጩ ተነገራቸው (7) አሥረኛው መቅሰፍት፦ በኩር የሆኑት ተገደሉ (29-32) እስራኤላውያን ከግብፅ ወጡ (33-42) አራት መቶ ሠላሳው ዓመት ተፈጸመ (40, 41) ስለ ፋሲካ በዓል አከባበር የተሰጠ መመሪያ (43-51) 13 በኩር የሆነ ወንድ ሁሉ የይሖዋ ነው (1, 2) እርሾ ያልገባበት ቂጣ በዓል (3-10) በኩር የሆነ ወንድ ሁሉ ለአምላክ የተሰጠ ነው (11-16) እስራኤላውያን ወደ ቀይ ባሕር እንዲያመሩ ታዘዙ (17-20) የደመናና የእሳት ዓምድ (21, 22) 14 እስራኤላውያን ቀይ ባሕር ደረሱ (1-4) ፈርዖን እስራኤላውያንን አሳደዳቸው (5-14) እስራኤላውያን ቀይ ባሕርን ተሻገሩ (15-25) ግብፃውያን ባሕሩ ውስጥ ሰመጡ (26-28) እስራኤላውያን በይሖዋ አመኑ (29-31) 15 የሙሴና የእስራኤላውያን የድል መዝሙር (1-19) ሚርያም ከወንዶቹ ጋር እየተቀባበለች ዘመረች (20, 21) መራራው ውኃ ጣፋጭ ሆነ (22-27) 16 ሕዝቡ በምግብ የተነሳ አጉረመረመ (1-3) ይሖዋ ማጉረምረማቸውን ሰማ (4-12) ድርጭትና መና ተሰጣቸው (13-21) በሰንበት ቀን መና አልነበረም (22-30) መና ለመታሰቢያነት ተቀመጠ (31-36) 17 በኮሬብ ውኃ ባለማግኘታቸው አማረሩ (1-4) ከዓለት ውኃ ፈለቀ (5-7) ከአማሌቃውያን ጋር ተዋግተው አሸነፉ (8-16) 18 ዮቶርና ሲፓራ ወደ ሙሴ መጡ (1-12) ሙሴ ፈራጆችን እንዲሾም ዮቶር መከረው (13-27) 19 ሙሴ ወደ ሲና ተራራ ወጣ (1-25) እስራኤላውያን የካህናት መንግሥት ይሆናሉ (5, 6) ሕዝቡ አምላክ ፊት ለመቅረብ ተቀደሰ (14, 15) 20 አሥሩ ትእዛዛት (1-17) እስራኤላውያን በተራራው ላይ ባዩት ትዕይንት የተነሳ ፈሩ (18-21) አምልኮን በተመለከተ የተሰጠ መመሪያ (22-26) 21 ለእስራኤላውያን የተሰጡ ድንጋጌዎች (1-36) ከዕብራውያን ባሮች ጋር በተያያዘ (2-11) በባልንጀራ ላይ ከሚወሰድ የኃይል እርምጃ ጋር በተያያዘ (12-27) ከእንስሳት ጋር በተያያዘ (28-36) 22 ለእስራኤላውያን የተሰጡ ድንጋጌዎች (1-31) ከስርቆት ጋር በተያያዘ (1-4) በእህል ላይ ከሚደርስ ጉዳት ጋር በተያያዘ (5, 6) ካሳ ከመክፈልና ከንብረት ባለቤትነት ጋር በተያያዘ (7-15) ያልታጨችን ድንግል አባብሎ የፆታ ግንኙነት ከመፈጸም ጋር በተያያዘ (16, 17) ከአምልኮና ከማኅበራዊ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ (18-31) 23 ለእስራኤላውያን የተሰጡ ድንጋጌዎች (1-19) ከሐቀኝነትና ፍትሐዊ ከመሆን ጋር በተያያዘ (1-9) ከሰንበትና ከበዓላት ጋር በተያያዘ (10-19) እስራኤላውያንን የሚመራቸው መልአክ (20-26) ምድሩን መውረስና ወሰን መከለል (27-33) 24 ሕዝቡ ቃል ኪዳኑን ለማክበር ተስማማ (1-11) ሙሴ በሲና ተራራ ላይ (12-18) 25 ለማደሪያ ድንኳኑ የሚሰጥ መዋጮ (1-9) ታቦቱ (10-22) ጠረጴዛው (23-30) መቅረዙ (31-40) 26 የማደሪያ ድንኳኑ (1-37) የድንኳኑ ጨርቆች (1-14) አራት ማዕዘን ቋሚዎችና መሰኪያዎቻቸው (15-30) መጋረጃውና መከለያው (31-37) 27 የሚቃጠል መባ የሚቀርብበት መሠዊያ (1-8) የማደሪያ ድንኳኑ ግቢ (9-19) ለመብራት የሚሆን ዘይት (20, 21) 28 የካህናቱ አልባሳት (1-5) ኤፉዱ (6-14) የደረት ኪሱ (15-30) ኡሪሙና ቱሚሙ (30) እጅጌ የሌለው ቀሚስ (31-35) ጥምጥሙና በጥምጥሙ ላይ የሚደረገው ጠፍጣፋ ወርቅ (36-39) ሌሎች የካህናት አልባሳት (40-43) 29 የካህናቱ ሹመት (1-37) በየቀኑ የሚቀርብ መባ (38-46) 30 የዕጣን መሠዊያ (1-10) የሕዝብ ቆጠራና ለማስተሰረያ የሚሆን ገንዘብ (11-16) ለመታጠቢያ የሚያገለግለው የመዳብ ገንዳ (17-21) በብልሃት የተቀመመ የቅብዓት ዘይት (22-33) የቅዱሱ ዕጣን አቀማመም (34-38) 31 በአምላክ መንፈስ የተሞሉ የእጅ ጥበብ ባለሙያዎች (1-11) በአምላክና በእስራኤላውያን መካከል ምልክት የሆነው ሰንበት (12-17) ሁለቱ የድንጋይ ጽላቶች (18) 32 ለአምልኮ የተሠራው የወርቅ ጥጃ (1-35) ሙሴ ለየት ያለ መዝሙር ሰማ (17, 18) ሙሴ ሕጉ የተጻፈባቸውን ጽላቶች ሰባበራቸው (19) ሌዋውያን በታማኝነት ከይሖዋ ጎን ቆሙ (26-29) 33 አምላክ ሕዝቡን ገሠጸ (1-6) የመገናኛ ድንኳኑ ከሰፈሩ ውጭ ተተከለ (7-11) ሙሴ የይሖዋን ክብር ለማየት ጠየቀ (12-23) 34 አዲስ የድንጋይ ጽላቶች ተዘጋጁ (1-4) ሙሴ የይሖዋን ክብር አየ (5-9) ቃል ኪዳኑ የያዘው ዝርዝር ሐሳብ በድጋሚ ተነገረ (10-28) የሙሴ ፊት አንጸባረቀ (29-35) 35 ሰንበትን አስመልክቶ የተሰጠ መመሪያ (1-3) ለማደሪያ ድንኳኑ የሚሰጥ መዋጮ (4-29) ባስልኤልና ኤልያብ በመንፈስ ተሞሉ (30-35) 36 ከሚያስፈልገው በላይ ተዋጣ (1-7) የማደሪያ ድንኳኑ አሠራር (8-38) 37 የታቦቱ አሠራር (1-9) ጠረጴዛው (10-16) መቅረዙ (17-24) የዕጣን መሠዊያው (25-29) 38 የሚቃጠል መባ መሠዊያው (1-7) የመዳብ ገንዳው (8) የማደሪያ ድንኳኑ ግቢ (9-20) የማደሪያ ድንኳኑ ዕቃዎች ተቆጥረው ተመዘገቡ (21-31) 39 የካህናቱ አልባሳት አሠራር (1) ኤፉዱ (2-7) የደረት ኪሱ (8-21) እጅጌ የሌለው ቀሚስ (22-26) ሌሎቹ የካህናት አልባሳት (27-29) ጥምጥሙ ላይ የሚደረገው ጠፍጣፋ ወርቅ (30, 31) ሙሴ የማደሪያ ድንኳኑ በትክክል መሠራቱን ተመለከተ (32-43) 40 የማደሪያ ድንኳኑ ተተከለ (1-33) የይሖዋ ክብር የማደሪያ ድንኳኑን ሞላው (34-38)