አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ ዕንባቆም የመጽሐፉ ይዘት ዕንባቆም የመጽሐፉ ይዘት 1 ነቢዩ እርዳታ ለማግኘት ያሰማው ጩኸት (1-4) ‘ይሖዋ ሆይ፣ እስከ መቼ ነው?’ (2) ‘ጭቆናን ለምን ዝም ብለህ ታያለህ?’ (3) የአምላክን ፍርድ ለማስፈጸም መሣሪያ ሆነው ያገለገሉት ከለዳውያን (5-11) ነቢዩ ይሖዋን ተማጸነ (12-17) “አምላኬ ሆይ፣ አንተ አትሞትም” (12) ‘ክፉ የሆነውን ነገር እንዳታይ እጅግ ንጹሕ ነህ’ (13) 2 ‘የሚናገረውን ለማየት በንቃት እጠባበቃለሁ’ (1) ይሖዋ ለነቢዩ የሰጠው መልስ (2-20) ‘ራእዩን በተስፋ ጠብቅ!’ (3) ‘ጻድቅ በታማኝነቱ በሕይወት ይኖራል’ (4) ለከለዳውያን የተነገሩ አምስት ወዮታዎች (6-20) ምድር ይሖዋን በማወቅ ትሞላለች (14) 3 ነቢዩ ይሖዋ እርምጃ እንዲወስድ ጸለየ (1-19) አምላክ የቀባውን ሕዝብ ያድናል (13) መከራ ቢኖርም በይሖዋ መደሰት (17, 18)