አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ ዕብራውያን የመጽሐፉ ይዘት ለዕብራውያን የተጻፈ ደብዳቤ የመጽሐፉ ይዘት 1 አምላክ በልጁ አማካኝነት ተናገረ (1-4) ልጁ ከመላእክት የላቀ ነው (5-14) 2 ‘ከወትሮው የበለጠ ትኩረት ስጡ’ (1-4) “ሁሉንም ነገር ከእግሩ በታች አስገዛህለት” (5-9) ኢየሱስና ወንድሞቹ (10-18) ‘ለመዳን የሚያበቃ ዋና ወኪል’ (10) መሐሪ የሆነ ሊቀ ካህናት (17) 3 ኢየሱስ ከሙሴ ይበልጣል (1-6) ‘ሁሉን ነገር የሠራው አምላክ ነው’ (4) ‘እምነት የለሽ ልብ በውስጣችሁ እንዳያቆጠቁጥ ተጠንቀቁ’ (7-19) “ዛሬ ድምፁን የምትሰሙ ከሆነ” (7, 15) 4 “ወደ እረፍቴ አይገቡም” (1-10) ወደ አምላክ እረፍት እንዲገቡ የተሰጠ ማበረታቻ (11-13) ‘የአምላክ ቃል ሕያው ነው’ (12) ኢየሱስ፣ ታላቅ ሊቀ ካህናት (14-16) 5 ኢየሱስ ከሰብዓዊ ሊቀ ካህናት ሁሉ የላቀ ነው (1-10) “ከመልከጼዴቅ ጋር በሚመሳሰል ሁኔታ” (6, 10) “ከደረሰበት መከራ መታዘዝን ተማረ” (8) “ዘላለማዊ መዳን እንዲያገኙ ምክንያት ሆነላቸው” (9) ‘ወተት የሚጋት ሁሉ ሕፃን ነው’ (11-14) 6 “ወደ ጉልምስና ለመድረስ እንጣጣር” (1-3) ወደኋላ ያሉት የአምላክን ልጅ እንደገና ይቸነክሩታል (4-8) ተስፋችሁን አስተማማኝ አድርጉ (9-12) አስተማማኝና ጽኑ ተስፋ አለን (13-20) የአምላክ የተስፋ ቃልና መሐላ ፈጽሞ አይለወጥም (17, 18) 7 መልከጼዴቅ፣ ልዩ የሆነ ንጉሥና ካህን (1-10) የክርስቶስ ክህነት ያለው ብልጫ (11-28) ክርስቶስ ሙሉ በሙሉ ሊያድን ይችላል (25) 8 ለሰማያዊ ነገሮች ጥላ የሆነ ድንኳን (1-6) አሮጌውና አዲሱ ቃል ኪዳን ሲነጻጸሩ (7-13) 9 በምድራዊው መቅደስ ይቀርብ የነበረው ቅዱስ አገልግሎት (1-10) ክርስቶስ ደሙን ይዞ ወደ ሰማይ ገባ (11-28) “የአዲስ ቃል ኪዳን መካከለኛ” (15) 10 የእንስሳት መሥዋዕት ኃጢአትን ማስወገድ አይችልም (1-4) ሕጉ ጥላ ነው (1) ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የቀረበ የክርስቶስ መሥዋዕት (5-18) “ወደ ሕይወት የሚመራ አዲስ መንገድ” (19-25) “መሰብሰባችንን ቸል አንበል” (24, 25) ሆን ብሎ በኃጢአት ጎዳና ከመመላለስ መራቅ (26-31) የተስፋው ቃል ሲፈጸም ለማየት መጽናት (32-39) 11 የእምነት ፍቺ (1, 2) የእምነት ምሳሌዎች (3-40) ‘ያለ እምነት አምላክን ደስ ማሰኘት አይቻልም’ (6) 12 የእምነታችን ፍጹም አድራጊ የሆነው ኢየሱስ (1-3) “ታላቅ የምሥክሮች ደመና” (1) “ይሖዋ የሚሰጥህን ተግሣጽ አቅልለህ አትመልከት” (4-11) ‘እግራችሁ ቀና በሆነ መንገድ እንዲጓዝ አድርጉ’ (12-17) ወደ ሰማያዊቱ ኢየሩሳሌም ቀርባችኋል’ (18-29) 13 መደምደሚያ ላይ የቀረበ ማሳሰቢያና ሰላምታ (1-25) “እንግዳ መቀበልን አትርሱ” (2) ‘ጋብቻ በሁሉ ዘንድ ክቡር ይሁን’ (4) “አመራር ለሚሰጧችሁ ታዘዙ” (7, 17) የምስጋና መሥዋዕት አቅርቡ (15, 16)