የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • 1 ዜና መዋዕል 23
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

1 ዜና መዋዕል የመጽሐፉ ይዘት

      • ዳዊት ሌዋውያኑን አደራጀ (1-32)

        • አሮንና ወንዶች ልጆቹ ተለዩ (13)

1 ዜና መዋዕል 23:1

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ባረጀና ዕድሜ በጠገበ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 1:33, 39፤ 1ዜና 28:5

1 ዜና መዋዕል 23:2

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 29:8, 9
  • +ዘኁ 3:6

1 ዜና መዋዕል 23:3

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘኁ 4:2, 3

1 ዜና መዋዕል 23:4

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 16:18፤ 1ዜና 26:29፤ 2ዜና 19:8

1 ዜና መዋዕል 23:5

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ዜና 26:12
  • +1ዜና 6:31, 32

1 ዜና መዋዕል 23:6

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ደለደላቸው።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 6:16
  • +2ዜና 8:14፤ 31:2

1 ዜና መዋዕል 23:8

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ዜና 26:21, 22

1 ዜና መዋዕል 23:10

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    በ1ዜና 23:11 ላይ ዚዛህ ተብሎም ተጠርቷል።

1 ዜና መዋዕል 23:12

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 6:21
  • +ዘፀ 6:18

1 ዜና መዋዕል 23:13

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 4:14
  • +ዘፀ 6:20, 26
  • +ዘሌ 9:22፤ ዘኁ 6:23-27፤ ዘዳ 21:5
  • +ዘፀ 28:1

1 ዜና መዋዕል 23:15

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 2:21, 22
  • +ዘፀ 18:3, 4

1 ዜና መዋዕል 23:16

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    በ1ዜና 24:20 ላይ ሹባኤል ተብሎም ተጠርቷል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ዜና 26:24

1 ዜና መዋዕል 23:17

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ወንዶች ልጆች።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ዜና 26:25

1 ዜና መዋዕል 23:18

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘኁ 3:27
  • +1ዜና 24:20, 22

1 ዜና መዋዕል 23:19

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ዜና 24:20, 23

1 ዜና መዋዕል 23:20

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 6:22

1 ዜና መዋዕል 23:21

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 6:19

1 ዜና መዋዕል 23:22

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ወንድሞቻቸው።”

1 ዜና መዋዕል 23:25

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ሳሙ 7:1
  • +1ነገ 8:12, 13፤ መዝ 135:21

1 ዜና መዋዕል 23:26

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘኁ 4:15

1 ዜና መዋዕል 23:28

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 6:36
  • +ዘኁ 3:9

1 ዜና መዋዕል 23:29

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ገጸ ኅብስቱን ያመለክታል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 24:5, 6፤ 1ዜና 9:32
  • +ዘፀ 29:1, 2፤ ዘሌ 2:4
  • +ዘሌ 7:12

1 ዜና መዋዕል 23:30

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 29:39
  • +1ዜና 16:4, 37

1 ዜና መዋዕል 23:31

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 20:10
  • +ዘኁ 10:10፤ መዝ 81:3
  • +ዘዳ 16:16

ተዛማጅ ሐሳብ

1 ዜና 23:11ነገ 1:33, 39፤ 1ዜና 28:5
1 ዜና 23:2ዘፀ 29:8, 9
1 ዜና 23:2ዘኁ 3:6
1 ዜና 23:3ዘኁ 4:2, 3
1 ዜና 23:4ዘዳ 16:18፤ 1ዜና 26:29፤ 2ዜና 19:8
1 ዜና 23:51ዜና 26:12
1 ዜና 23:51ዜና 6:31, 32
1 ዜና 23:6ዘፀ 6:16
1 ዜና 23:62ዜና 8:14፤ 31:2
1 ዜና 23:81ዜና 26:21, 22
1 ዜና 23:12ዘፀ 6:21
1 ዜና 23:12ዘፀ 6:18
1 ዜና 23:13ዘፀ 4:14
1 ዜና 23:13ዘፀ 6:20, 26
1 ዜና 23:13ዘሌ 9:22፤ ዘኁ 6:23-27፤ ዘዳ 21:5
1 ዜና 23:13ዘፀ 28:1
1 ዜና 23:15ዘፀ 2:21, 22
1 ዜና 23:15ዘፀ 18:3, 4
1 ዜና 23:161ዜና 26:24
1 ዜና 23:171ዜና 26:25
1 ዜና 23:18ዘኁ 3:27
1 ዜና 23:181ዜና 24:20, 22
1 ዜና 23:191ዜና 24:20, 23
1 ዜና 23:20ዘፀ 6:22
1 ዜና 23:21ዘፀ 6:19
1 ዜና 23:252ሳሙ 7:1
1 ዜና 23:251ነገ 8:12, 13፤ መዝ 135:21
1 ዜና 23:26ዘኁ 4:15
1 ዜና 23:281ነገ 6:36
1 ዜና 23:28ዘኁ 3:9
1 ዜና 23:29ዘሌ 24:5, 6፤ 1ዜና 9:32
1 ዜና 23:29ዘፀ 29:1, 2፤ ዘሌ 2:4
1 ዜና 23:29ዘሌ 7:12
1 ዜና 23:30ዘፀ 29:39
1 ዜና 23:301ዜና 16:4, 37
1 ዜና 23:31ዘፀ 20:10
1 ዜና 23:31ዘኁ 10:10፤ መዝ 81:3
1 ዜና 23:31ዘዳ 16:16
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
  • 23
  • 24
  • 25
  • 26
  • 27
  • 28
  • 29
  • 30
  • 31
  • 32
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
1 ዜና መዋዕል 23:1-32

አንደኛ ዜና መዋዕል

23 ዳዊት በሸመገለና የሕይወቱ ፍጻሜ በተቃረበ* ጊዜ ልጁን ሰለሞንን በእስራኤል ላይ አነገሠው።+ 2 ከዚያም የእስራኤልን መኳንንት፣ ካህናቱንና+ ሌዋውያኑን+ ሁሉ ሰበሰበ። 3 ዕድሜያቸው 30 እና ከዚያ በላይ የሆኑ ሌዋውያን ተቆጠሩ፤+ እያንዳንዱ ወንድ በነፍስ ወከፍ ሲቆጠር 38,000 ነበር። 4 ከእነዚህም መካከል 24,000ዎቹ የይሖዋን ቤት ሥራ በበላይነት ይቆጣጠሩ ነበር፤ በተጨማሪም 6,000 አለቆችና ዳኞች ነበሩ፤+ 5 ደግሞም 4,000 በር ጠባቂዎች+ እንዲሁም ዳዊት “ውዳሴ ለማቅረብ የሠራኋቸው ናቸው” ባላቸው መሣሪያዎች ለይሖዋ ውዳሴ+ የሚያቀርቡ 4,000 ሰዎች ነበሩ።

6 ከዚያም ዳዊት በሌዊ ልጆች በጌድሶን፣ በቀአት እና በሜራሪ+ ምድብ አደራጃቸው።*+ 7 ከጌድሶናውያን ወገን ላዳን እና ሺምአይ ነበሩ። 8 የላዳን ወንዶች ልጆች መሪው የሂኤል፣ ዜታም እና ኢዩኤል+ ሲሆኑ በአጠቃላይ ሦስት ነበሩ። 9 የሺምአይ ወንዶች ልጆች ሸሎሞት፣ ሃዚኤል እና ካራን ሲሆኑ በአጠቃላይ ሦስት ነበሩ። እነዚህ የላዳን ወገን የየአባቶቻቸው ቤቶች መሪዎች ነበሩ። 10 የሺምአይ ወንዶች ልጆች ያሃት፣ ዚና፣* የኡሽ እና በሪአ ነበሩ። እነዚህ አራቱ የሺምአይ ወንዶች ልጆች ነበሩ። 11 መሪው ያሃት ነበር፤ ሁለተኛው ደግሞ ዚዛህ ነበር። የኡሽ እና በሪአ ግን ብዙ ወንዶች ልጆች ስላልነበሯቸው በአንድ የሥራ መደብ እንደ አንድ የአባቶች ቤት ሆነው ተቆጠሩ።

12 የቀአት ወንዶች ልጆች አምራም፣ ይጽሃር፣+ ኬብሮን እና ዑዚኤል+ ሲሆኑ በአጠቃላይ አራት ነበሩ። 13 የአምራም ወንዶች ልጆች አሮን+ እና ሙሴ+ ነበሩ። ሆኖም አሮንና ወንዶች ልጆቹ ቅድስተ ቅዱሳኑን እንዲቀድሱ፣ በይሖዋ ፊት መሥዋዕት እንዲያቀርቡ፣ እሱን እንዲያገለግሉና ምንጊዜም በስሙ እንዲባርኩ+ በቋሚነት ተለይተው ነበር።+ 14 የእውነተኛው አምላክ ሰው የሙሴ ወንዶች ልጆች የሌዋውያን ነገድ ክፍል ሆነው ተቆጠሩ። 15 የሙሴ ወንዶች ልጆች ጌርሳም+ እና ኤሊዔዘር+ ነበሩ። 16 ከጌርሳም ወንዶች ልጆች መካከል መሪው ሸቡኤል*+ ነበር። 17 ከኤሊዔዘር ዘሮች* መካከል መሪው ረሃቢያህ+ ነበር፤ ኤሊዔዘር ሌሎች ወንዶች ልጆች አልነበሩትም፤ ይሁንና የረሃብያህ ወንዶች ልጆች እጅግ ብዙ ነበሩ። 18 ከይጽሃር+ ወንዶች ልጆች መካከል መሪው ሸሎሚት+ ነበር። 19 የኬብሮን ወንዶች ልጆች መሪ የሆነው የሪያ፣ ሁለተኛው አማርያህ፣ ሦስተኛው ያሃዚኤል እና አራተኛው የቃምአም+ ነበሩ። 20 የዑዚኤል ወንዶች ልጆች+ መሪ የሆነው ሚክያስ እና ሁለተኛው ይሽሺያህ ነበሩ።

21 የሜራሪ ወንዶች ልጆች ማህሊ እና ሙሺ ነበሩ።+ የማህሊ ወንዶች ልጆች አልዓዛር እና ቂስ ነበሩ። 22 ሆኖም አልዓዛር ሴቶች ልጆች ብቻ እንጂ ወንዶች ልጆች ሳይወልድ ሞተ። በመሆኑም ዘመዶቻቸው* የቂስ ልጆች አገቧቸው። 23 የሙሺ ወንዶች ልጆች ማህሊ፣ ኤዴር እና የሬሞት ሲሆኑ በአጠቃላይ ሦስት ነበሩ።

24 በአባቶቻቸው ቤት ይኸውም በአባቶቻቸው ቤት መሪዎች ተቆጥረውና በስም ተዘርዝረው የተመዘገቡት በይሖዋ ቤት ያለውን አገልግሎት ያከናውኑ የነበሩ 20 ዓመትና ከዚያ በላይ የሆናቸው የሌዊ ወንዶች ልጆች እነዚህ ናቸው። 25 ዳዊት እንዲህ ብሎ ነበርና፦ “የእስራኤል አምላክ ይሖዋ ለሕዝቡ እረፍት ሰጥቷል፤+ እሱም በኢየሩሳሌም ለዘላለም ይኖራል።+ 26 ሌዋውያኑም የማደሪያ ድንኳኑን ወይም በውስጡ ያሉትን ለአምልኮ የሚያገለግሉ ዕቃዎች ሁሉ መሸከም አያስፈልጋቸውም።”+ 27 ዳዊት በሰጠው የመጨረሻ መመሪያ መሠረት ከሌዊ ልጆች መካከል የተቆጠሩት 20 ዓመትና ከዚያ በላይ የሆናቸው ሰዎች እነዚህ ነበሩ። 28 የሌዋውያኑ ተግባር በይሖዋ ቤት አገልግሎት የሚከናወነውን ሥራ ይኸውም ቅጥር ግቢዎቹንና+ የመመገቢያ ክፍሎቹን፣ ቅዱስ የሆነውን ነገር ሁሉ የማንጻቱን ሥራና በእውነተኛው አምላክ ቤት የሚከናወኑትን አስፈላጊ ሥራዎች ሁሉ ኃላፊነት ወስደው በመሥራት የአሮንን ልጆች+ መርዳት ነበር። 29 ደግሞም የሚነባበረውን ዳቦ፣*+ ለእህል መባ የሚያገለግለውን የላመ ዱቄት፣ እርሾ ያልገባበትን ስስ ቂጣ፣+ በምጣድ የሚጋገረውን ቂጣና በዘይት የሚለወሰውን ሊጥ+ በማዘጋጀት እንዲሁም ከሁሉም ዓይነት መለኪያዎችና መስፈሪያዎች ጋር የተያያዙ ሥራዎችን በማከናወን ያግዟቸው ነበር። 30 ለይሖዋ ምስጋናና ውዳሴ ለማቅረብ ጠዋት ጠዋትም+ ሆነ ማታ ማታ+ ይቆሙ ነበር። 31 ሕጉ በሚያዘው ቁጥር መሠረት ዘወትር በይሖዋ ፊት በየሰንበቱ፣+ በየወር መባቻውና+ በበዓላት ወቅት+ ለይሖዋ የሚቃጠል መሥዋዕት በቀረበ ጊዜ ሁሉ ያግዟቸው ነበር። 32 በተጨማሪም በይሖዋ ቤት ለሚከናወነው አገልግሎት ከመገናኛ ድንኳኑ፣ ከቅዱሱ ስፍራና ወንድሞቻቸው ከሆኑት የአሮን ወንዶች ልጆች ጋር በተያያዘ ያሉባቸውን ኃላፊነቶች ይወጡ ነበር።

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ