የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • መኃልየ መኃልይ 8
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

መኃልየ መኃልይ የመጽሐፉ ይዘት

    • ሱላማዊቷ በኢየሩሳሌም (3:6–8:4)

    • ሱላማዊቷ ተመለሰች፤ ታማኝነቷን አስመሠከረች (8:5-14)

        • የልጃገረዷ ወንድሞች (5ለ)

          • ‘ውዷን ደገፍ ብላ የምትመጣው ይህች ማን ናት?’

        • ልጃገረዷ (5ለ-7)

          • “ፍቅር እንደ ሞት የበረታ ነው” (6)

        • የልጃገረዷ ወንድሞች (8, 9)

          • “እሷ ቅጥር ብትሆን . . . በር ብትሆን ግን . . .” (9)

        • ልጃገረዷ (10-12)

          • “እኔ ቅጥር ነኝ” (10)

        • እረኛው (13)

          • ‘ድምፅሽን ልስማው’

        • ልጃገረዷ (14)

          • ‘እንደ ሜዳ ፍየል ፍጠን’

መኃልየ መኃልይ 8:1

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መኃ 1:2

መኃልየ መኃልይ 8:2

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መኃ 3:4

መኃልየ መኃልይ 8:3

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መኃ 2:6

መኃልየ መኃልይ 8:4

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መኃ 2:7፤ 3:5

መኃልየ መኃልይ 8:6

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ሙሉ በሙሉ ያደሩ መሆንም።”

  • *

    ወይም “ሲኦል።” የሰው ልጆችን ሁሉ መቃብር ያመለክታል። የቃላት መፍቻውን ተመልከት።

  • *

    “ያህ” የይሖዋ ስም አጭር መጠሪያ ነው።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዮሐ 15:13፤ ኤፌ 5:25፤ ራእይ 12:11
  • +ዘዳ 4:24፤ 1ዮሐ 4:8

መኃልየ መኃልይ 8:7

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    “ይንቁታል” ማለትም ሊሆን ይችላል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ቆሮ 13:8, 13
  • +ሮም 8:38, 39

መኃልየ መኃልይ 8:8

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መኃ 1:6

መኃልየ መኃልይ 8:11

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መክ 2:4

መኃልየ መኃልይ 8:12

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “አንድ ሺው።”

መኃልየ መኃልይ 8:13

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    “ጓደኞችሽ” ማለትም ሊሆን ይችላል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መኃ 1:6፤ 6:11
  • +መኃ 2:14

መኃልየ መኃልይ 8:14

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መኃ 2:9, 17

ተዛማጅ ሐሳብ

መኃ. 8:1መኃ 1:2
መኃ. 8:2መኃ 3:4
መኃ. 8:3መኃ 2:6
መኃ. 8:4መኃ 2:7፤ 3:5
መኃ. 8:6ዮሐ 15:13፤ ኤፌ 5:25፤ ራእይ 12:11
መኃ. 8:6ዘዳ 4:24፤ 1ዮሐ 4:8
መኃ. 8:71ቆሮ 13:8, 13
መኃ. 8:7ሮም 8:38, 39
መኃ. 8:8መኃ 1:6
መኃ. 8:11መክ 2:4
መኃ. 8:13መኃ 1:6፤ 6:11
መኃ. 8:13መኃ 2:14
መኃ. 8:14መኃ 2:9, 17
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
መኃልየ መኃልይ 8:1-14

መኃልየ መኃልይ

8 “ምነው አንተ፣ የእናቴን ጡት እንደጠባ፣

እንደ ወንድሜ በሆንክ!

እንዲህ ቢሆን ኖሮ ውጭ ሳገኝህ በሳምኩህ ነበር፤+

ማንም ባልናቀኝ ነበር።

 2 እኔም ወዳስተማረችኝ

ወደ እናቴ ቤት በወሰድኩህና

ወደዚያ ባስገባሁህ ነበር።+

ትጠጣው ዘንድ ቅመም የተጨመረበት ወይን ጠጅና

የሮማን ጭማቂ በሰጠሁህ ነበር።

 3 ግራ እጁን በተንተራስኩ፣

ቀኝ እጁም ባቀፈኝ ነበር።+

 4 የኢየሩሳሌም ሴቶች ልጆች ሆይ፣

በራሱ እስኪነሳሳ ድረስ ፍቅርን በውስጤ እንዳትቀሰቅሱ ወይም እንዳታነሳሱ አምላችኋለሁ።”+

 5 “ውዷን ደገፍ ብላ

ከምድረ በዳ የምትመጣው ይህች ማን ናት?”

“ከፖም ዛፍ ሥር ቀሰቀስኩህ።

በዚያ እናትህ አንተን ለመውለድ አማጠች።

በዚያም ወላጅ እናትህ ምጥ ይዟት ነበር።

 6 እንደ ማኅተም በልብህ፣

እንደ ማኅተም በክንድህ አስቀምጠኝ፤

ፍቅር እንደ ሞት የበረታ ነውና፤+

ታማኝነትም* እንደ መቃብር* ጽኑ ነው፤

የፍቅር ወላፈን የእሳት ወላፈን ነው፤ የያህም* ነበልባል ነው።+

 7 ጎርፍ ፍቅርን ሊያጠፋው አይችልም፤+

ወንዞችም ጠራርገው ሊወስዱት አይችሉም።+

አንድ ሰው ለፍቅር ሲል የቤቱን ሀብት ሁሉ ለመስጠት ቢያቀርብ

ሰዎች በጣም ይንቁበታል።”*

 8 “ገና ጡት ያላወጣች

ትንሽ እህት አለችን።+

እሷን በሚጠይቁን ቀን

ለእህታችን ምን ብናደርግ ይሻላል?”

 9 “እሷ ቅጥር ብትሆን

በላይዋ ላይ የብር ጉልላት እንሠራለን፤

በር ብትሆን ግን

ከአርዘ ሊባኖስ በተሠራ ሳንቃ እናሽጋታለን።”

10 “እኔ ቅጥር ነኝ፤

ጡቶቼም እንደ ማማ ናቸው።

በእሱም ፊት

ሰላም እንዳገኘች ሴት ሆንኩ።

11 ሰለሞን በበዓልሃሞን የወይን እርሻ ነበረው።+

እሱም የወይን እርሻውን ለጠባቂዎች በአደራ ሰጠ።

እያንዳንዳቸውም ለሚያገኙት ፍሬ አንድ ሺህ የብር ሰቅል ያመጡ ነበር።

12 የራሴ የሆነ የወይን እርሻ አለኝ።

ሰለሞን ሆይ፣ አንድ ሺው የብር ሰቅል* የአንተ ነው፤

ሁለት መቶው ደግሞ ፍሬውን ለሚጠብቁት ነው።”

13 “አንቺ በአትክልት ቦታዎቹ የምትኖሪ ሆይ፣+

ጓደኞቼ* ድምፅሽን ያዳምጣሉ።

እስቲ እኔም ልስማው።”+

14 “ውዴ ሆይ፣ ቶሎ ና፤

እንደ ሜዳ ፍየል

ወይም የቅመም ተክሎች በሚበቅሉባቸው ተራሮች ላይ እንዳለ

የአጋዘን ግልገል ፍጠን።”+

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ