ዘፀአት 1:5 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 5 ከያዕቆብ አብራክ የወጡት* በጠቅላላ 70* ነበሩ፤ ዮሴፍ ግን ቀድሞውኑም እዚያው ግብፅ ነበር።+ ዘዳግም 10:22 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 22 አባቶችህ ወደ ግብፅ ሲወርዱ 70* ነበሩ፤+ አሁን ግን አምላክህ ይሖዋ በሰማያት ላይ እንዳሉ ከዋክብት ቁጥርህን አብዝቶታል።+ የሐዋርያት ሥራ 7:14 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 14 ስለዚህ ዮሴፍ መልእክት ልኮ አባቱን ያዕቆብንና ዘመዶቹን ሁሉ ከዚያ አገር አስጠራ፤+ እነሱም በአጠቃላይ 75 ሰዎች* ነበሩ።+