ዘፍጥረት 12:2 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 2 አንተን ታላቅ ብሔር አደርግሃለሁ፤ እንዲሁም እባርክሃለሁ፤ ስምህንም ታላቅ አደርገዋለሁ፤ አንተም በረከት ትሆናለህ።+ ዘፍጥረት 15:1 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 15 ከዚህ በኋላ የይሖዋ ቃል በራእይ ወደ አብራም መጥቶ “አብራም አትፍራ።+ እኔ ጋሻ እሆንሃለሁ።+ የምታገኘውም ሽልማት እጅግ ታላቅ ይሆናል”+ አለው። ዘፍጥረት 15:5 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 5 ወደ ውጭም ካወጣው በኋላ “እባክህ ቀና ብለህ ወደ ሰማይ ተመልከት፤ እስቲ መቁጠር ከቻልክ ከዋክብቱን ቁጠራቸው” አለው። ከዚያም “የአንተም ዘር እንዲሁ ይሆናል”+ አለው። ዘፀአት 1:7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 እስራኤላውያንም* ተዋለዱ፤ በጣም ብዙ ሆኑ፤ ቁጥራቸውም በከፍተኛ ፍጥነት እየጨመረና ኃያል እየሆኑ ሄዱ፤ ከዚህም የተነሳ ምድሪቱን ሞሏት።+ ዕብራውያን 11:12 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 12 ከዚህም የተነሳ እንደሞተ ያህል ከሚቆጠረው+ ከአንድ ሰው እንደ ሰማይ ከዋክብት የበዙና በባሕር ዳር እንዳለ አሸዋ የማይቆጠሩ ልጆች ተወለዱ።+
5 ወደ ውጭም ካወጣው በኋላ “እባክህ ቀና ብለህ ወደ ሰማይ ተመልከት፤ እስቲ መቁጠር ከቻልክ ከዋክብቱን ቁጠራቸው” አለው። ከዚያም “የአንተም ዘር እንዲሁ ይሆናል”+ አለው።