የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ዘፍጥረት 13:14, 15
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 14 ሎጥ ከአብራም ከተለየ በኋላ ይሖዋ አብራምን እንዲህ አለው፦ “እባክህ ካለህበት ቦታ ሆነህ ዓይንህን አቅንተህ ወደ ሰሜን፣ ወደ ደቡብ፣ ወደ ምሥራቅና ወደ ምዕራብ ተመልከት፤ 15 ምክንያቱም የምታየውን ምድር ሁሉ ለአንተና ለዘርህ ለዘለቄታው ርስት አድርጌ እሰጣለሁ።+

  • ዘፍጥረት 26:3, 4
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 3 በዚህ ምድር እንደ ባዕድ አገር ሰው ሆነህ ተቀመጥ፤+ እኔም ከአንተ ጋር መሆኔን እቀጥላለሁ፤ እንዲሁም እባርክሃለሁ። ምክንያቱም ይህችን ምድር በሙሉ ለአንተና ለዘሮችህ እሰጣለሁ፤+ ደግሞም ለአባትህ ለአብርሃም እንዲህ ስል የማልሁለትን መሐላ እፈጽማለሁ፦+ 4 ‘ዘርህን በሰማያት ላይ እንዳሉ ከዋክብት አበዛዋለሁ፤+ ይህችንም ምድር በሙሉ ለዘርህ እሰጣለሁ፤+ የምድርም ብሔራት ሁሉ በዘርህ አማካኝነት ለራሳቸው በረከት ያገኛሉ።’+

  • ዘዳግም 34:4
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 4 ከዚያም ይሖዋ እንዲህ አለው፦ “ለአብርሃም፣ ለይስሐቅና ለያዕቆብ ‘ለዘርህ እሰጣታለሁ’+ በማለት የማልኩላቸው ምድር ይህች ናት። በዓይንህ እንድታያት አድርጌሃለሁ፤ ነገር ግን ወደዚያ አትሻገርም።”+

  • የሐዋርያት ሥራ 7:4, 5
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 4 እሱም ከከለዳውያን አገር ወጥቶ በካራን መኖር ጀመረ። አባቱ ከሞተ+ በኋላ ደግሞ አምላክ ከዚያ ተነስቶ አሁን እናንተ ወደምትኖሩበት ወደዚህ ምድር እንዲዛወር አደረገው።+ 5 ሆኖም በወቅቱ በዚህ ምድር ምንም ርስት፣ ሌላው ቀርቶ እግሩን ሊያሳርፍ የሚችልበት መሬት እንኳ አልሰጠውም፤ ይሁንና ገና ልጅ ሳይኖረው ለእሱም ሆነ ከእሱ በኋላ ለዘሮቹ ምድሪቱን ርስት አድርጎ እንደሚሰጣቸው ቃል ገባለት።+

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ