-
ዘፀአት 7:5አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
5 በግብፅ ላይ እጄን ስዘረጋና እስራኤላውያንን ከመካከላቸው ሳወጣ ግብፃውያን እኔ ይሖዋ መሆኔን በእርግጥ ያውቃሉ።”+
-
-
ዘፀአት 7:17አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
17 እንግዲህ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ በዚህ ታውቃለህ።+ ይኸው በበትሬ በአባይ ወንዝ ውስጥ ያለውን ውኃ እመታለሁ፤ ውኃውም ወደ ደም ይለወጣል።
-
-
ዘፀአት 8:9, 10አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
9 ከዚያም ሙሴ ፈርዖንን እንዲህ አለው፦ “እንቁራሪቶቹ ከአንተ፣ ከአገልጋዮችህ፣ ከሕዝብህና ከቤቶችህ ይወገዱ ዘንድ አምላክን እንድለምንልህ የምትፈልገው መቼ እንደሆነ የመወሰኑን ጉዳይ ለአንተ ትቼዋለሁ። እንቁራሪቶቹ በአባይ ወንዝ ውስጥ ብቻ ተወስነው ይቀራሉ።” 10 እሱም “ነገ ይሁን” አለው። በመሆኑም ሙሴ እንዲህ አለው፦ “እንደ አምላካችን እንደ ይሖዋ ያለ ማንም እንደሌለ+ እንድታውቅ ልክ እንዳልከው ይሆናል።
-
-
መዝሙር 24:1አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
24 ምድርና በውስጧ ያለው ነገር ሁሉ፣
ፍሬያማ የሆነችው ምድርና በእሷ ላይ የሚኖር ሁሉ የይሖዋ ነው።+
-