ዘፍጥረት 9:4 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 4 ብቻ ሕይወቱ* ማለትም ደሙ+ በውስጡ ያለበትን ሥጋ አትብሉ።+ ዘሌዋውያን 3:17 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 17 “‘ስብም ሆነ ደም+ ፈጽሞ አትብሉ። ይህም በምትኖሩበት ስፍራ ሁሉ ለእናንተም ሆነ ለትውልዶቻችሁ ዘላቂ ደንብ ነው።’” ዘሌዋውያን 17:10 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 10 “‘ከእስራኤል ቤት የሆነ ማንኛውም ሰው ወይም በመካከላችሁ የሚኖር የትኛውም የባዕድ አገር ሰው ምንም ዓይነት ደም ቢበላ፣+ ደም በሚበላው ሰው* ላይ በእርግጥ ፊቴን አጠቁርበታለሁ፤ ከሕዝቡም መካከል ለይቼ አጠፋዋለሁ። ዘዳግም 12:16 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 16 ደሙን ግን እንዳትበሉ፤+ ከዚህ ይልቅ እንደ ውኃ መሬት ላይ አፍሱት።+ 1 ሳሙኤል 14:33 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 33 በመሆኑም ሳኦል “ይኸው ሕዝቡ ሥጋውን ከነደሙ በመብላት+ በይሖዋ ላይ ኃጢአት እየሠራ ነው” ተብሎ ተነገረው። እሱም በዚህ ጊዜ “እምነት እንደሌላችሁ የሚያሳይ ድርጊት ፈጽማችኋል። በሉ አሁኑኑ አንድ ትልቅ ድንጋይ አንከባላችሁ አምጡልኝ” አለ። የሐዋርያት ሥራ 15:20 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 20 ከዚህ ይልቅ በጣዖት+ ከረከሱ ነገሮች፣ ከፆታ ብልግና፣*+ ታንቆ ከሞተ* እንስሳ ሥጋ እንዲሁም ከደም እንዲርቁ+ እንጻፍላቸው። የሐዋርያት ሥራ 15:29 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 29 ለጣዖት ከተሠዉ ነገሮች፣+ ከደም፣+ ታንቆ ከሞተ እንስሳ* ሥጋና+ ከፆታ ብልግና* ራቁ።+ ከእነዚህ ነገሮች ሙሉ በሙሉ ከራቃችሁ መልካም ይሆንላችኋል። ጤና ይስጣችሁ!”*
10 “‘ከእስራኤል ቤት የሆነ ማንኛውም ሰው ወይም በመካከላችሁ የሚኖር የትኛውም የባዕድ አገር ሰው ምንም ዓይነት ደም ቢበላ፣+ ደም በሚበላው ሰው* ላይ በእርግጥ ፊቴን አጠቁርበታለሁ፤ ከሕዝቡም መካከል ለይቼ አጠፋዋለሁ።
33 በመሆኑም ሳኦል “ይኸው ሕዝቡ ሥጋውን ከነደሙ በመብላት+ በይሖዋ ላይ ኃጢአት እየሠራ ነው” ተብሎ ተነገረው። እሱም በዚህ ጊዜ “እምነት እንደሌላችሁ የሚያሳይ ድርጊት ፈጽማችኋል። በሉ አሁኑኑ አንድ ትልቅ ድንጋይ አንከባላችሁ አምጡልኝ” አለ።
29 ለጣዖት ከተሠዉ ነገሮች፣+ ከደም፣+ ታንቆ ከሞተ እንስሳ* ሥጋና+ ከፆታ ብልግና* ራቁ።+ ከእነዚህ ነገሮች ሙሉ በሙሉ ከራቃችሁ መልካም ይሆንላችኋል። ጤና ይስጣችሁ!”*