ዘዳግም 24:8 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 8 “የሥጋ ደዌ* ቢከሰት ሌዋውያን ካህናት የሚሰጧችሁን መመሪያዎች ሁሉ በጥንቃቄ ተከተሉ።+ እኔ የሰጠኋቸውንም ትእዛዝ በጥንቃቄ ፈጽሙ። ሕዝቅኤል 44:23 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 23 “‘ቅዱስ በሆነና ተራ በሆነ ነገር መካከል ያለውን ልዩነት ለሕዝቤ ያስተምሩ፤ ንጹሕ ባልሆነውና ንጹሕ በሆነው ነገር መካከል ያለውንም ልዩነት ያሳውቋቸው።+ ሚልክያስ 2:7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 ካህኑ ምንጊዜም በከንፈሮቹ ላይ እውቀት ሊኖረው ይገባል፤ ሰዎችም ሕጉን* ከአፉ ሊሹ ይገባል፤+ ምክንያቱም እሱ የሠራዊት ጌታ የይሖዋ መልእክተኛ ነው። ሉቃስ 17:14 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 14 እሱም ባያቸው ጊዜ “ሄዳችሁ ራሳችሁን ለካህናት አሳዩ” አላቸው።+ ከዚያም እየሄዱ ሳሉ ነጹ።+