ዘሌዋውያን 14:2-4 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 2 “የሥጋ ደዌ ያለበት አንድ ሰው መንጻቱን ለማረጋገጥ ካህኑ ፊት እንዲቀርብ+ በሚደረግበት ዕለት የሚኖረው ሕግ ይህ ነው። 3 ካህኑ ከሰፈሩ ውጭ ወጥቶ ሰውየውን ይመረምረዋል። የሥጋ ደዌ ይዞት የነበረው ሰው ከሥጋ ደዌው ከዳነ 4 ካህኑ ሰውየው ራሱን ለማንጻት በሕይወት ያሉ ሁለት ንጹሕ ወፎችን፣ የአርዘ ሊባኖስ እንጨት፣ ደማቅ ቀይ ማግና ሂሶጵ እንዲያመጣ ያዘዋል።+ ዘዳግም 24:8 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 8 “የሥጋ ደዌ* ቢከሰት ሌዋውያን ካህናት የሚሰጧችሁን መመሪያዎች ሁሉ በጥንቃቄ ተከተሉ።+ እኔ የሰጠኋቸውንም ትእዛዝ በጥንቃቄ ፈጽሙ። ማቴዎስ 8:3, 4 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 3 ኢየሱስም እጁን ዘርግቶ ዳሰሰውና “እፈልጋለሁ! ንጻ” አለው።+ ወዲያውኑ ከሥጋ ደዌው ነጻ።+ 4 ከዚያም ኢየሱስ “ለማንም እንዳትናገር ተጠንቀቅ፤+ ነገር ግን ሄደህ ራስህን ለካህን አሳይ፤+ ሙሴ ያዘዘውንም መባ አቅርብ።+ ካህናቱም ማስረጃውን ይመለከታሉ” አለው። ሉቃስ 5:13, 14 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 13 ኢየሱስም እጁን ዘርግቶ ዳሰሰውና “እፈልጋለሁ! ንጻ” አለው። ወዲያውኑ የሥጋ ደዌው ለቀቀው።+ 14 ከዚያም ኢየሱስ ሰውየውን ለማንም እንዳይናገር አዘዘው፤ “ነገር ግን ሄደህ ራስህን ለካህን አሳይ፤ ሙሴ ባዘዘው መሠረት+ ስለ መንጻትህ መባ አቅርብ፤ ካህናቱም ማስረጃውን ይመለከታሉ” አለው።+
2 “የሥጋ ደዌ ያለበት አንድ ሰው መንጻቱን ለማረጋገጥ ካህኑ ፊት እንዲቀርብ+ በሚደረግበት ዕለት የሚኖረው ሕግ ይህ ነው። 3 ካህኑ ከሰፈሩ ውጭ ወጥቶ ሰውየውን ይመረምረዋል። የሥጋ ደዌ ይዞት የነበረው ሰው ከሥጋ ደዌው ከዳነ 4 ካህኑ ሰውየው ራሱን ለማንጻት በሕይወት ያሉ ሁለት ንጹሕ ወፎችን፣ የአርዘ ሊባኖስ እንጨት፣ ደማቅ ቀይ ማግና ሂሶጵ እንዲያመጣ ያዘዋል።+
3 ኢየሱስም እጁን ዘርግቶ ዳሰሰውና “እፈልጋለሁ! ንጻ” አለው።+ ወዲያውኑ ከሥጋ ደዌው ነጻ።+ 4 ከዚያም ኢየሱስ “ለማንም እንዳትናገር ተጠንቀቅ፤+ ነገር ግን ሄደህ ራስህን ለካህን አሳይ፤+ ሙሴ ያዘዘውንም መባ አቅርብ።+ ካህናቱም ማስረጃውን ይመለከታሉ” አለው።
13 ኢየሱስም እጁን ዘርግቶ ዳሰሰውና “እፈልጋለሁ! ንጻ” አለው። ወዲያውኑ የሥጋ ደዌው ለቀቀው።+ 14 ከዚያም ኢየሱስ ሰውየውን ለማንም እንዳይናገር አዘዘው፤ “ነገር ግን ሄደህ ራስህን ለካህን አሳይ፤ ሙሴ ባዘዘው መሠረት+ ስለ መንጻትህ መባ አቅርብ፤ ካህናቱም ማስረጃውን ይመለከታሉ” አለው።+