ዘሌዋውያን 19:9 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 9 “‘የምድራችሁን አዝመራ በምትሰበስቡበት ጊዜ በእርሻችሁ ዳር ዳር ያለውን ሙልጭ አድርጋችሁ አትጨዱት፤ የእርሻችሁን ቃርሚያም አትልቀሙ።+ ዘዳግም 24:19 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 19 “በማሳህ ላይ ያለውን እህል በምታጭድበት ጊዜ በማሳው ላይ ነዶ ብትረሳ ያን ለመውሰድ አትመለስ። አምላክህ ይሖዋ የእጅህን ሥራ ሁሉ እንዲባርክልህ+ ለባዕድ አገሩ ሰው፣ አባት ለሌለው ልጅና ለመበለቲቱ እንዲሆን እዚያው ተወው።+ ሩት 2:2, 3 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 2 ሞዓባዊቷም ሩት ናኦሚን “እባክሽ ወደ እርሻ ቦታዎቹ ልሂድና ሞገስ የሚያሳየኝ ሰው ካገኘሁ እህል ልቃርም”+ አለቻት። ናኦሚም “ልጄ ሆይ፣ ሂጂ” አለቻት። 3 ሩትም ሄደች፤ በማሳውም ውስጥ ከአጫጆቹ ኋላ እየተከተለች መቃረም ጀመረች። እንደ አጋጣሚ ሆኖ የገባችው የኤሊሜሌክ ቤተሰብ+ ወደሆነው ወደ ቦዔዝ+ እርሻ ነበር።
19 “በማሳህ ላይ ያለውን እህል በምታጭድበት ጊዜ በማሳው ላይ ነዶ ብትረሳ ያን ለመውሰድ አትመለስ። አምላክህ ይሖዋ የእጅህን ሥራ ሁሉ እንዲባርክልህ+ ለባዕድ አገሩ ሰው፣ አባት ለሌለው ልጅና ለመበለቲቱ እንዲሆን እዚያው ተወው።+
2 ሞዓባዊቷም ሩት ናኦሚን “እባክሽ ወደ እርሻ ቦታዎቹ ልሂድና ሞገስ የሚያሳየኝ ሰው ካገኘሁ እህል ልቃርም”+ አለቻት። ናኦሚም “ልጄ ሆይ፣ ሂጂ” አለቻት። 3 ሩትም ሄደች፤ በማሳውም ውስጥ ከአጫጆቹ ኋላ እየተከተለች መቃረም ጀመረች። እንደ አጋጣሚ ሆኖ የገባችው የኤሊሜሌክ ቤተሰብ+ ወደሆነው ወደ ቦዔዝ+ እርሻ ነበር።