ዘፀአት 20:4 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 4 “በላይ በሰማያት ወይም በታች በምድር አሊያም ከምድር በታች በውኃ ውስጥ ባለ በማንኛውም ነገር አምሳል የተቀረጸን ቅርጽ ወይም የተሠራን ምስል ለራስህ አታድርግ።+ ዘሌዋውያን 19:4 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 4 ከንቱ ወደሆኑ አማልክት ዞር አትበሉ፤+ ወይም ከቀለጠ ብረት ለራሳችሁ አማልክትን አትሥሩ።+ እኔ አምላካችሁ ይሖዋ ነኝ። የሐዋርያት ሥራ 17:29 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 29 “እንግዲህ እኛ የአምላክ ልጆች+ ከሆንን አምላክ በሰው ጥበብና ንድፍ ከወርቅ፣ ከብር ወይም ከድንጋይ የተቀረጸን ነገር ይመስላል ብለን ልናስብ አይገባም።+ 1 ቆሮንቶስ 8:4 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 4 ለጣዖቶች የቀረበ ምግብ መብላትን በተመለከተ፣ በዓለም ላይ ጣዖት ከንቱ እንደሆነና+ ከአንዱ በቀር አምላክ እንደሌለ እናውቃለን።+
4 “በላይ በሰማያት ወይም በታች በምድር አሊያም ከምድር በታች በውኃ ውስጥ ባለ በማንኛውም ነገር አምሳል የተቀረጸን ቅርጽ ወይም የተሠራን ምስል ለራስህ አታድርግ።+