ዘፀአት 22:22, 23 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 22 “መበለቲቱን ወይም አባት የሌለውን* ልጅ አታጎሳቁሉ።+ 23 ብታጎሳቁለውና ወደ እኔ ቢጮኽ እኔ በእርግጥ ጩኸቱን እሰማለሁ፤+ ዘዳግም 24:14, 15 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 14 “ከወንድሞችህም ሆነ በምድርህ ይኸውም በከተሞችህ* ውስጥ ከሚኖሩ የባዕድ አገር ሰዎች መካከል የተቸገረውንና ድሃ የሆነውን ቅጥር ሠራተኛ አታታል።+ 15 ደሞዙን በዕለቱ ስጠው፤+ ችግረኛ በመሆኑና ሕይወቱ* የተመካው በደሞዙ ላይ ስለሆነ ፀሐይ ከመጥለቋ በፊት ስጠው። አለዚያ በአንተ የተነሳ ወደ ይሖዋ ይጮኻል፤ አንተም በኃጢአት ትጠየቃለህ።+ ምሳሌ 21:13 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 13 ችግረኛው የሚያሰማውን ጩኸት ላለመስማት ጆሮውን የሚደፍን ሁሉ፣እሱ ራሱ ይጮኻል፤ መልስም አያገኝም።+
14 “ከወንድሞችህም ሆነ በምድርህ ይኸውም በከተሞችህ* ውስጥ ከሚኖሩ የባዕድ አገር ሰዎች መካከል የተቸገረውንና ድሃ የሆነውን ቅጥር ሠራተኛ አታታል።+ 15 ደሞዙን በዕለቱ ስጠው፤+ ችግረኛ በመሆኑና ሕይወቱ* የተመካው በደሞዙ ላይ ስለሆነ ፀሐይ ከመጥለቋ በፊት ስጠው። አለዚያ በአንተ የተነሳ ወደ ይሖዋ ይጮኻል፤ አንተም በኃጢአት ትጠየቃለህ።+