ዘፀአት 20:12 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 12 “አምላክህ ይሖዋ በሚሰጥህ ምድር ላይ ዕድሜህ እንዲረዝም+ አባትህንና እናትህን አክብር።+ ዘዳግም 27:16 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 16 “‘አባቱን ወይም እናቱን የሚንቅ የተረገመ ይሁን።’+ (ሕዝቡም ሁሉ ‘አሜን!’ ይላል።) ምሳሌ 1:8 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 8 ልጄ ሆይ፣ የአባትህን ተግሣጽ አዳምጥ፤+የእናትህንም መመሪያ* አትተው።+ ኤፌሶን 6:1 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 6 ልጆች ሆይ፣ ከጌታ ፈቃድ ጋር በሚስማማ መንገድ ለወላጆቻችሁ ታዘዙ፤+ ይህ የጽድቅ ተግባር ነውና።