9 ይሖዋ እንዲረዳቸው ወደ እሱ በጮኹም ጊዜ+ ይሖዋ እስራኤላውያንን እንዲያድናቸው የካሌብ ታናሽ ወንድም የሆነውን የቀናዝን ልጅ ኦትኒኤልን+ አዳኝ አድርጎ አስነሳው።+ 10 የይሖዋም መንፈስ በእሱ ላይ ወረደ፤+ እሱም የእስራኤል መስፍን ሆነ። ለጦርነት በወጣም ጊዜ ይሖዋ የሜሶጶጣሚያውን ንጉሥ ኩሻንሪሻታይምን በእጁ አሳልፎ ሰጠው፤ እሱም በኩሻንሪሻታይም ላይ በረታበት። 11 ከዚያ በኋላ ምድሪቱ ለ40 ዓመት አረፈች። ከዚያም የቀናዝ ልጅ ኦትኒኤል ሞተ።