የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ዘኁልቁ 11:16, 17
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 16 ይሖዋም መልሶ ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ከእስራኤል ሽማግሌዎች መካከል የሕዝቡ ሽማግሌዎችና አለቆች+ የመሆን ብቃት አላቸው የምትላቸውን 70 ሰዎች ሰብስብልኝ፤ እነሱንም ወደ መገናኛ ድንኳኑ ውሰዳቸውና በዚያ ከአንተ ጋር ይቁሙ። 17 እኔም ወርጄ+ በዚያ ከአንተ ጋር እነጋገራለሁ፤+ በአንተ ላይ ካለው መንፈስ+ ወስጄ በእነሱ ላይ አደርጋለሁ፤ እነሱም የሕዝቡን ሸክም ብቻህን እንዳትሸከም ይረዱሃል።+

  • መሳፍንት 6:34
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 34 የይሖዋም መንፈስ በጌድዮን ላይ ወረደ፤* + እሱም ቀንደ መለከት ነፋ፤+ አቢዔዜራውያንም+ እሱን በመደገፍ ተከትለውት ወጡ።

  • መሳፍንት 11:29
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 29 የይሖዋ መንፈስ በዮፍታሔ ላይ ወረደ፤+ እሱም በጊልያድ ወደምትገኘው ወደ ምጽጳ+ ለመሄድ ጊልያድንና ምናሴን አቋርጦ አለፈ፤ በጊልያድ ከምትገኘው ምጽጳም ተነስቶ ወደ አሞናውያን ሄደ።

  • መሳፍንት 14:5, 6
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 5 ስለዚህ ሳምሶን ከአባቱና ከእናቱ ጋር ወደ ቲምና ወረደ። በቲምና ወዳለው የወይን እርሻ ሲደርስም አንድ ደቦል አንበሳ እያገሳ መጣበት። 6 ከዚያም የይሖዋ መንፈስ ኃይል ሰጠው፤+ አንድ ሰው በባዶ እጁ የፍየልን ጠቦት ለሁለት እንደሚገነጥል እሱም አንበሳውን ለሁለት ገነጠለው። ሆኖም ያደረገውን ነገር ለአባቱም ሆነ ለእናቱ አልነገራቸውም።

  • መሳፍንት 15:14
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 14 እሱም ሊሃይ ሲደርስ ፍልስጤማውያኑ እሱን በማግኘታቸው በድል አድራጊነት ጮኹ። በዚህ ጊዜ የይሖዋ መንፈስ ኃይል ሰጠው፤+ እጆቹ የታሰሩባቸውም ገመዶች እሳት እንደበላው የበፍታ ክር ሆኑ፤ ማሰሪያዎቹም ከእጆቹ ላይ ቀልጠው ወደቁ።+

  • 1 ሳሙኤል 11:6
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 6 ሳኦልም ይህን ሲሰማ የአምላክ መንፈስ ኃይል ሰጠው፤+ ቁጣውም ነደደ።

  • 1 ሳሙኤል 16:13
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 13 ስለዚህ ሳሙኤል የዘይቱን ቀንድ+ ወስዶ በወንድሞቹ ፊት ቀባው። ከዚያም ቀን አንስቶ የይሖዋ መንፈስ ለዳዊት ኃይል ሰጠው።+ በኋላም ሳሙኤል ተነስቶ ወደ ራማ+ ሄደ።

  • 2 ዜና መዋዕል 15:1
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 15 የአምላክ መንፈስ በኦዴድ ልጅ በአዛርያስ ላይ ወረደ።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ