የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ዘፀአት 23:33
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 33 በእኔ ላይ ኃጢአት እንድትሠራ እንዳያደርጉህ በምድርህ ላይ መኖር የለባቸውም። አማልክታቸውን ብታገለግል ወጥመድ ይሆንብሃል።”+

  • ዘኁልቁ 33:55
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 55 “‘የምድሪቱን ነዋሪዎች ከፊታችሁ ሳታባርሩ እዚያው ከተዋችኋቸው+ ግን ዓይናችሁ ውስጥ እንደገባ ጉድፍ እንዲሁም ጎናችሁ ላይ እንደተሰካ እሾህ ይሆኑባችኋል፤ ደግሞም በምትኖሩበት ምድር ያንገላቷችኋል።+

  • ዘዳግም 20:16, 17
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 16 አምላክህ ይሖዋ ርስት አድርጎ በሚሰጥህ እነዚህ ሕዝቦች በሚኖሩባቸው ከተሞች ውስጥ ግን እስትንፋስ ያለውን ማንኛውንም ነገር በሕይወት አታስቀር።+ 17 ከዚህ ይልቅ አምላክህ ይሖዋ ባዘዘህ መሠረት ሂታውያንን፣ አሞራውያንን፣ ከነአናውያንን፣ ፈሪዛውያንን፣ ሂዋውያንንና ኢያቡሳውያንን ሙሉ በሙሉ አጥፋ፤+

  • ኢያሱ 23:12, 13
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 12 “ይሁንና ወደ ኋላ ዞር ብትሉና ከእነዚህ ብሔራት መካከል ተርፈው ከእናንተ ጋር ከቀሩት+ ሰዎች ጋር የጠበቀ ግንኙነት ብትመሠርቱ፣ በጋብቻ ብትዛመዱ+ እንዲሁም እናንተ ከእነሱ ጋር ብትወዳጁ፣ እነሱም ከእናንተ ጋር ወዳጅነት ቢመሠርቱ 13 አምላካችሁ ይሖዋ ከዚህ በኋላ ለእናንተ ሲል እነዚህን ብሔራት እንደማያባርራቸው* በእርግጥ እወቁ።+ እነሱም አምላካችሁ ይሖዋ ከሰጣችሁ ከዚህች መልካም ምድር ላይ እስክትጠፉ ድረስ ወጥመድ፣ አሽክላ፣ ለጀርባችሁ ጅራፍ እንዲሁም በዓይናችሁ ውስጥ እንዳለ እሾህ ይሆኑባችኋል።+

  • መሳፍንት 1:28
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 28 እስራኤላውያንም እያየሉ በሄዱ ጊዜ ከነአናውያንን የግዳጅ ሥራ እንዲሠሩ አስገደዷቸው+ እንጂ ሙሉ በሙሉ አላባረሯቸውም።+

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ