ዘሌዋውያን 19:2 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 2 “ለመላው የእስራኤል ማኅበረሰብ እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ‘እኔ አምላካችሁ ይሖዋ ቅዱስ ስለሆንኩ እናንተም ቅዱስ ልትሆኑ ይገባል።+ መዝሙር 99:5 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 5 ይሖዋ አምላካችንን ከፍ ከፍ አድርጉት፤+ በእግሩ ማሳረፊያ ፊት ስገዱ፤*+እሱ ቅዱስ ነው።+ ኢሳይያስ 6:3 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 3 አንዳቸውም ሌላውን እንዲህ ይሉ ነበር፦ “የሠራዊት ጌታ ይሖዋ ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ ቅዱስ ነው።+ መላዋ ምድር በክብሩ ተሞልታለች።” 1 ጴጥሮስ 1:15 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 15 ከዚህ ይልቅ የጠራችሁ ቅዱስ አምላክ፣ ቅዱስ እንደሆነ ሁሉ እናንተም በምግባራችሁ ሁሉ ቅዱሳን ሁኑ፤+