16 “ለመሆኑ አቢሜሌክን ንጉሥ ያደረጋችሁት+ በየዋህነትና በቅንነት ነው? ለየሩባአልና ለቤተሰቡ ጥሩነት አሳይታችኋል? የሚገባውን ውለታስ መልሳችሁለታል? 17 አባቴ ለእናንተ ሲል በተዋጋ ጊዜ+ እናንተን ከምድያማውያን እጅ ለመታደግ ሕይወቱን አደጋ ላይ ጥሏል።+ 18 እናንተ ግን ዛሬ በአባቴ ቤተሰብ ላይ ተነሳችሁ፤ 70 ልጆቹንም በአንድ ድንጋይ ላይ ገደላችኋቸው።+ ወንድማችሁ ስለሆነ ብቻ ከባሪያይቱ የወለደውን ልጁን አቢሜሌክን+ በሴኬም መሪዎች ላይ አነገሣችሁት።