መዝሙር 91:11 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 11 በመንገድህ ሁሉ እንዲጠብቁህ+መላእክቱን ስለ አንተ ያዛልና።+ መዝሙር 97:10 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 10 እናንተ ይሖዋን የምትወዱ፣ ክፉ የሆነውን ነገር ጥሉ።+ እሱ የታማኝ አገልጋዮቹን ሕይወት* ይጠብቃል፤+ከክፉዎች እጅ* ይታደጋቸዋል።+ መዝሙር 121:3 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 3 እሱ እግርህ እንዲንሸራተት* ፈጽሞ አይፈቅድም።+ ጠባቂህ በጭራሽ አያንቀላፋም።