2 ነገሥት 25:13 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 13 ከለዳውያኑም የይሖዋን ቤት የመዳብ ዓምዶች+ እንዲሁም በይሖዋ ቤት ውስጥ የነበሩትን የዕቃ ማጓጓዣ ጋሪዎችና+ የመዳብ ባሕር+ ሰባብረው መዳቡን ወደ ባቢሎን አጋዙ።+ 2 ነገሥት 25:17 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 17 የእያንዳንዱ ዓምድ ቁመት 18 ክንድ* ነበር፤+ በዓምዱ አናት ላይ ያለው ጌጥ ከመዳብ የተሠራ ሲሆን የጌጡ ርዝማኔ ሦስት ክንድ ነበር፤ በጌጡ ዙሪያ ያሉት ሮማኖችና መረቡ በሙሉ ከመዳብ የተሠሩ ነበሩ።+ ሁለተኛው ዓምድና መረቡም ከዚህ ጋር ተመሳሳይ ነበር። 2 ዜና መዋዕል 3:15 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 15 ከቤቱ ፊት ለፊትም 35 ክንድ ርዝመት ያላቸው ሁለት ዓምዶችን+ ሠራ፤ በእያንዳንዱ ዓምድ ላይ ያለው የዓምድ ራስ አምስት ክንድ ነበር።+ ኤርምያስ 52:21 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 21 ዓምዶቹ እያንዳንዳቸው 18 ክንድ* ቁመት ነበራቸው፤ የዙሪያቸው መጠን በመለኪያ ገመድ 12 ክንድ፣+ ውፍረታቸውም አራት ጣት* ሲሆን ውስጣቸው ክፍት ነበር።
13 ከለዳውያኑም የይሖዋን ቤት የመዳብ ዓምዶች+ እንዲሁም በይሖዋ ቤት ውስጥ የነበሩትን የዕቃ ማጓጓዣ ጋሪዎችና+ የመዳብ ባሕር+ ሰባብረው መዳቡን ወደ ባቢሎን አጋዙ።+
17 የእያንዳንዱ ዓምድ ቁመት 18 ክንድ* ነበር፤+ በዓምዱ አናት ላይ ያለው ጌጥ ከመዳብ የተሠራ ሲሆን የጌጡ ርዝማኔ ሦስት ክንድ ነበር፤ በጌጡ ዙሪያ ያሉት ሮማኖችና መረቡ በሙሉ ከመዳብ የተሠሩ ነበሩ።+ ሁለተኛው ዓምድና መረቡም ከዚህ ጋር ተመሳሳይ ነበር።