-
1 ነገሥት 7:15-22አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
15 እሱም ሁለቱን ዓምዶች+ ከቀለጠ መዳብ ሠራ፤ እያንዳንዱም ዓምድ ቁመቱ 18 ክንድ ነበር፤ ሁለቱ ዓምዶች እያንዳንዳቸው በመለኪያ ገመድ ሲለኩ መጠነ ዙሪያቸው 12 ክንድ ነበር።+ 16 እንዲሁም በዓምዶቹ አናት ላይ የሚሆኑ ሁለት የዓምድ ራሶችን ከመዳብ ሠራ። የአንደኛው የዓምድ ራስ ቁመት አምስት ክንድ የሌላኛው የዓምድ ራስ ቁመትም አምስት ክንድ ነበር። 17 በእያንዳንዱ ዓምድ አናት ላይ ያለው የዓምድ ራስ በሰንሰለት ጉንጉን የተሠሩ መረቦች ነበሩት፤+ በአንደኛው የዓምድ ራስ ላይ ሰባት በሌላኛው የዓምድ ራስ ላይም ሰባት ነበሩ። 18 በዓምዶቹ አናት ላይ ያሉትን የዓምድ ራሶች ለማስጌጥ በአንደኛው መረብ ዙሪያ ሮማኖችን በሁለት ረድፍ ሠራ፤ በሁለቱም የዓምድ ራሶች ላይ እንዲሁ አደረገ። 19 በረንዳው አጠገብ በሚገኙት ዓምዶች አናት ላይ ያሉት የዓምድ ራሶች አራት ክንድ ቁመት ያለው የአበባ ቅርጽ ነበራቸው። 20 የዓምድ ራሶቹ በሁለቱ ዓምዶች ላይ፣ ልክ ከመረብ ሥራው ቀጥሎ ካለው ከሆዱ በላይ ነበሩ፤ በእያንዳንዱ የዓምድ ራስ ዙሪያ 200 ሮማኖች በረድፍ ተደርድረው ነበር።+
21 እሱም የቤተ መቅደሱን* በረንዳ ዓምዶች አቆመ።+ በስተ ቀኝ* ያለውን ዓምድ አቁሞ ያኪን* ብሎ ሰየመው፤ ከዚያም በስተ ግራ* ያለውን ዓምድ አቁሞ ቦዔዝ* ብሎ ሰየመው።+ 22 የዓምዶቹም አናቶች የአበባ ቅርጽ ነበራቸው። በዚህ መንገድ የዓምዶቹ ሥራ ተጠናቀቀ።
-
-
2 ዜና መዋዕል 4:11-13አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
11 በተጨማሪም ኪራም አመድ ማጠራቀሚያዎቹን፣ አካፋዎቹንና ጎድጓዳ ሳህኖቹን ሠራ።+
ኪራምም በእውነተኛው አምላክ ቤት ለንጉሥ ሰለሞን ያከናውን የነበረውን ሥራ ጨረሰ፤+ 12 ሁለቱን ዓምዶች፣+ በሁለቱ ዓምዶች አናት ላይ የነበሩትን የጎድጓዳ ሳህን ቅርጽ ያላቸው የዓምድ ራሶች፣ በዓምዶቹ አናት ላይ የነበሩትን የጎድጓዳ ሳህን ቅርጽ ያላቸውን ሁለቱን ክብ የዓምድ ራሶች የሚያስጌጡትን ሁለት መረቦች፣+ 13 ለሁለቱ መረቦች የተሠሩትን 400 ሮማኖች+ ማለትም በዓምዶቹ አናት ላይ የነበሩትን የጎድጓዳ ሳህን ቅርጽ ያላቸውን ሁለት የዓምድ ራሶች ለማስጌጥ የተሠሩትን በእያንዳንዱ መረብ ላይ በሁለት ረድፍ የተደረደሩትን ሮማኖች፣+
-