የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ዘኁልቁ 9:14
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 14 “‘በመካከላችሁ የሚኖር የባዕድ አገር ሰው ካለ እሱም ለይሖዋ የፋሲካን መሥዋዕት ማዘጋጀት አለበት።+ ይህን በፋሲካው ደንብና በወጣለት ሥርዓት መሠረት ማድረግ አለበት።+ ለሁላችሁም ማለትም ለባዕድ አገሩም ሰው ሆነ ለአገሬው ተወላጅ አንድ ዓይነት ደንብ ይኑር።’”+

  • ሩት 1:16
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 16 ሩት ግን እንዲህ አለቻት፦ “ከአንቺ እንድለይና ትቼሽ እንድመለስ አትማጸኚኝ፤ እኔ እንደሆነ ወደምትሄጂበት እሄዳለሁ፤ በምታድሪበት አድራለሁ። ሕዝብሽ ሕዝቤ፣ አምላክሽም አምላኬ ይሆናል።+

  • 2 ነገሥት 5:15
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 15 ከዚያ በኋላ አጃቢዎቹን አስከትሎ ወደ እውነተኛው አምላክ ሰው ተመለሰ፤+ በፊቱም ቆሞ “በእስራኤል እንጂ በምድር ላይ በሌላ በየትኛውም ቦታ አምላክ እንደሌለ አሁን አውቄአለሁ።+ እባክህ ከአገልጋይህ ስጦታ* ተቀበል” አለው።

  • 2 ዜና መዋዕል 6:32, 33
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 32 “በተጨማሪም ከሕዝብህ ከእስራኤል ወገን ያልሆነ የባዕድ አገር ሰው ከታላቁ ስምህ፣* ከኃያሉ እጅህና ከተዘረጋው ክንድህ የተነሳ ከሩቅ አገር ቢመጣ፣+ ወደዚህም ቤት መጥቶ ቢጸልይ፣+ 33 ከመኖሪያ ቦታህ ከሰማያት ሆነህ ስማ፤ የምድር ሕዝቦች ሁሉ እንደ ሕዝብህ እንደ እስራኤል ስምህን እንዲያውቁና+ እንዲፈሩህ እንዲሁም ስምህ እኔ በሠራሁት በዚህ ቤት እንደሚጠራ እንዲያውቁ ያ የባዕድ አገር ሰው የጠየቀህን ሁሉ ፈጽምለት።

  • ኢሳይያስ 56:6, 7
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    •  6 እሱን ለማገልገል፣ የይሖዋን ስም ለመውደድና

      የእሱ አገልጋዮች ለመሆን

      ከይሖዋ ጋር የሚቆራኙትን የባዕድ አገር ሰዎች፣+

      ሰንበትን የሚጠብቁትንና የማያረክሱትን፣

      ቃል ኪዳኔንም አጥብቀው የሚይዙትን ሁሉ፣

       7 ቅዱስ ወደሆነው ተራራዬ አመጣቸዋለሁ፤+

      በጸሎት ቤቴም ውስጥ እጅግ እንዲደሰቱ አደርጋቸዋለሁ።

      የሚያቀርቧቸውም ሙሉ በሙሉ የሚቃጠሉ መባዎችና መሥዋዕቶች በመሠዊያዬ ላይ ተቀባይነት ያገኛሉ።

      ቤቴም ለሕዝቦች ሁሉ የጸሎት ቤት ተብሎ ይጠራልና።”+

  • የሐዋርያት ሥራ 8:27
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 27 እሱም ተነስቶ ሄደ፤ የኢትዮጵያ ንግሥት የህንደኬ* ባለሥልጣንና የገንዘቧ ሁሉ ኃላፊ የሆነ አንድ ኢትዮጵያዊ ጃንደረባም* አገኘ። ይህ ሰው ለአምልኮ ወደ ኢየሩሳሌም ሄዶ ነበር፤+

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ