41 “በተጨማሪም ከሕዝብህ ከእስራኤል ወገን ያልሆነ የባዕድ አገር ሰው በስምህ የተነሳ ከሩቅ አገር ቢመጣ፣+ 42 (መቼም ስለ ታላቁ ስምህ፣+ ስለ ኃያሉ እጅህና ስለተዘረጋው ክንድህ መስማታቸው አይቀርም) ወደዚህም ቤት መጥቶ ቢጸልይ 43 ከመኖሪያ ቦታህ ከሰማያት+ ሆነህ ስማ፤ የምድር ሕዝቦች ሁሉ እንደ ሕዝብህ እንደ እስራኤል ስምህን እንዲያውቁና እንዲፈሩህ+ እንዲሁም ስምህ እኔ በሠራሁት በዚህ ቤት እንደሚጠራ እንዲያውቁ ያ የባዕድ አገር ሰው የጠየቀህን ሁሉ ፈጽምለት።