22 በመሆኑም ንጉሥ ሰለሞን በብልጽግናና በጥበብ ምድር ላይ ካሉ ሌሎች ነገሥታት ሁሉ ይበልጥ ነበር።+ 23 የምድር ነገሥታትም ሁሉ እውነተኛው አምላክ በሰለሞን ልብ ውስጥ ያኖረውን ጥበብ ይሰሙ ዘንድ ከእሱ ጋር ለመገናኘት ይጓጉ ነበር።+ 24 ወደ እሱ የሚመጡትም ሰዎች በየዓመቱ የብር ዕቃዎች፣ የወርቅ ዕቃዎች፣ ልብሶች፣+ የጦር ትጥቆች፣ የበለሳን ዘይት፣ ፈረሶችና በቅሎዎች ስጦታ አድርገው ያመጡ ነበር።