1 ነገሥት 3:12, 13 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 12 የጠየቅከውን አደርግልሃለሁ።+ ከአንተ በፊት ማንም ሰው ያልነበረውን+ ከአንተ በኋላም ማንም ሰው የማያገኘውን ጥበበኛና አስተዋይ ልብ እሰጥሃለሁ።+ 13 በተጨማሪም በሕይወት ዘመንህ* ሁሉ ከነገሥታት መካከል አንተን የሚተካከል እንዳይኖር+ አንተ ያልጠየቅከውን+ ብልጽግናና ክብር+ እሰጥሃለሁ። 1 ነገሥት 4:29 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 29 አምላክም ለሰለሞን እጅግ ታላቅ ጥበብና ማስተዋል እንዲሁም በባሕር ዳርቻ ላይ እንዳለ አሸዋ፣ ሰፊ ልብ* ሰጠው።+ 1 ነገሥት 10:23-25 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 23 በመሆኑም ንጉሥ ሰለሞን በብልጽግናና+ በጥበብ+ ምድር ላይ ካሉ ሌሎች ነገሥታት ሁሉ ይበልጥ ነበር። 24 የምድር ሕዝቦችም ሁሉ አምላክ በሰለሞን ልብ ውስጥ ያኖረውን ጥበብ+ ይሰሙ ዘንድ ከእሱ ጋር ለመገናኘት ይጓጉ ነበር።* 25 ወደ እሱ የሚመጡትም ሰዎች በየዓመቱ የብር ዕቃዎች፣ የወርቅ ዕቃዎች፣ ልብሶች፣ የጦር ትጥቆች፣ የበለሳን ዘይት፣ ፈረሶችና በቅሎዎች ስጦታ አድርገው ያመጡ ነበር።
12 የጠየቅከውን አደርግልሃለሁ።+ ከአንተ በፊት ማንም ሰው ያልነበረውን+ ከአንተ በኋላም ማንም ሰው የማያገኘውን ጥበበኛና አስተዋይ ልብ እሰጥሃለሁ።+ 13 በተጨማሪም በሕይወት ዘመንህ* ሁሉ ከነገሥታት መካከል አንተን የሚተካከል እንዳይኖር+ አንተ ያልጠየቅከውን+ ብልጽግናና ክብር+ እሰጥሃለሁ።
23 በመሆኑም ንጉሥ ሰለሞን በብልጽግናና+ በጥበብ+ ምድር ላይ ካሉ ሌሎች ነገሥታት ሁሉ ይበልጥ ነበር። 24 የምድር ሕዝቦችም ሁሉ አምላክ በሰለሞን ልብ ውስጥ ያኖረውን ጥበብ+ ይሰሙ ዘንድ ከእሱ ጋር ለመገናኘት ይጓጉ ነበር።* 25 ወደ እሱ የሚመጡትም ሰዎች በየዓመቱ የብር ዕቃዎች፣ የወርቅ ዕቃዎች፣ ልብሶች፣ የጦር ትጥቆች፣ የበለሳን ዘይት፣ ፈረሶችና በቅሎዎች ስጦታ አድርገው ያመጡ ነበር።