ኤርምያስ 2:11 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 11 አማልክቱን፣ አማልክት ባልሆኑት ለውጦ የሚያውቅ ብሔር አለ? የገዛ ሕዝቤ ግን ክብሬን ምንም ጥቅም በሌለው ነገር ለውጧል።+ ሆሴዕ 10:2 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 2 ልባቸው ግብዝ* ነው፤በመሆኑም በደለኞች ናቸው። መሠዊያዎቻቸውን የሚሰባብር፣ ዓምዶቻቸውንም የሚያፈራርስ አለ። ማቴዎስ 12:30 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 30 ከእኔ ጎን ያልቆመ ሁሉ ይቃወመኛል፤ ከእኔ ጋር የማይሰበስብም ሁሉ ይበትናል።+ 1 ቆሮንቶስ 10:21 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 21 የይሖዋን* ጽዋና የአጋንንትን ጽዋ መጠጣት አትችሉም፤ “ከይሖዋ* ማዕድ”+ እና ከአጋንንት ማዕድ መካፈል አትችሉም። 2 ቆሮንቶስ 6:14, 15 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 14 ከማያምኑ ጋር አቻ ባልሆነ መንገድ አትጠመዱ።*+ ጽድቅ ከዓመፅ ጋር ምን ኅብረት አለው?+ ወይስ ብርሃን ከጨለማ ጋር ምን ያገናኘዋል?+ 15 በተጨማሪም በክርስቶስና በቤልሆር* መካከል ምን ስምምነት አለ?+ ወይስ የሚያምን ከማያምን ጋር ምን ድርሻ አለው?+
14 ከማያምኑ ጋር አቻ ባልሆነ መንገድ አትጠመዱ።*+ ጽድቅ ከዓመፅ ጋር ምን ኅብረት አለው?+ ወይስ ብርሃን ከጨለማ ጋር ምን ያገናኘዋል?+ 15 በተጨማሪም በክርስቶስና በቤልሆር* መካከል ምን ስምምነት አለ?+ ወይስ የሚያምን ከማያምን ጋር ምን ድርሻ አለው?+