ዘፀአት 14:21, 22 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 21 ሙሴም እጁን በባሕሩ ላይ ሰነዘረ፤+ ይሖዋም ሌሊቱን ሙሉ ኃይለኛ የምሥራቅ ነፋስ በማምጣት ባሕሩ ወደ ኋላ እንዲመለስ አደረገ፤ የባሕሩንም ወለል ወደ ደረቅ መሬት ለወጠው፤+ ውኃውም ተከፈለ።+ 22 በመሆኑም እስራኤላውያን ውኃው በቀኛቸውና በግራቸው እንደ ግድግዳ ቆሞ+ በባሕሩ መሃል በደረቅ መሬት ተሻገሩ።+ ኢያሱ 3:17 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 17 እስራኤላውያን በሙሉ በደረቅ መሬት እስኪሻገሩ+ ይኸውም መላው ብሔር ዮርዳኖስን ተሻግሮ እስኪያበቃ ድረስ የይሖዋን የቃል ኪዳን ታቦት የተሸከሙት ካህናት በዮርዳኖስ መካከል በደረቅ መሬት ላይ ባሉበት ቆመው ነበር።+ 2 ነገሥት 2:13, 14 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 13 ከዚያም ከኤልያስ ላይ የወደቀውን የነቢይ ልብስ+ አነሳ፤ ተመልሶም በዮርዳኖስ ዳርቻ ቆመ። 14 እሱም ከኤልያስ ላይ በወደቀው የነቢይ ልብስ ውኃውን መታና እንዲህ አለ፦ “የኤልያስ አምላክ ይሖዋ የት አለ?” ውኃውንም ሲመታው ግራና ቀኝ ተከፈለ፤ ኤልሳዕም ተሻገረ።+
21 ሙሴም እጁን በባሕሩ ላይ ሰነዘረ፤+ ይሖዋም ሌሊቱን ሙሉ ኃይለኛ የምሥራቅ ነፋስ በማምጣት ባሕሩ ወደ ኋላ እንዲመለስ አደረገ፤ የባሕሩንም ወለል ወደ ደረቅ መሬት ለወጠው፤+ ውኃውም ተከፈለ።+ 22 በመሆኑም እስራኤላውያን ውኃው በቀኛቸውና በግራቸው እንደ ግድግዳ ቆሞ+ በባሕሩ መሃል በደረቅ መሬት ተሻገሩ።+
17 እስራኤላውያን በሙሉ በደረቅ መሬት እስኪሻገሩ+ ይኸውም መላው ብሔር ዮርዳኖስን ተሻግሮ እስኪያበቃ ድረስ የይሖዋን የቃል ኪዳን ታቦት የተሸከሙት ካህናት በዮርዳኖስ መካከል በደረቅ መሬት ላይ ባሉበት ቆመው ነበር።+
13 ከዚያም ከኤልያስ ላይ የወደቀውን የነቢይ ልብስ+ አነሳ፤ ተመልሶም በዮርዳኖስ ዳርቻ ቆመ። 14 እሱም ከኤልያስ ላይ በወደቀው የነቢይ ልብስ ውኃውን መታና እንዲህ አለ፦ “የኤልያስ አምላክ ይሖዋ የት አለ?” ውኃውንም ሲመታው ግራና ቀኝ ተከፈለ፤ ኤልሳዕም ተሻገረ።+